እስክንድር አሰፋ ከኖርዌይ
10 02 2013 እ. አ
እንዲሁም ታዋቂው የሐገር ባህል ዘፈን አቀንቃኝ ዳምጠው አየለ ምሽቱን በተለያዩ ባህላዊ ዘፈኖች ሲያደምቅ ቆይቷል በመቀጠልም መልእክት አዘል ድራማ በኖርዌይ የሚኖሩ ስደተኞች አቅርበዋል በምሽቱ በጣም ፉክክር የታየበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ለጨረታ ቀርቦ ነበር ጨረታውንም ነዋሪነታቸው በኦስሎ የሆኑ ሐገር ወዳድ ተፉካካሪዎቻቸውን በመዘረር ምንም ሳይበረዝና ሳይጨመር የቁየውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከተወዳጁ ታማኝ በየነ ተረክበዋል።
10 02 2013 እ. አ
በአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በሚደረገው በሰባት የአውሮፓ ሐገሮች የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዛሬ FEB 10.2013 በኦስሎ ኖርዌይ ከተማ ቀጥሎ ውሎአል።
በኖርዌይ ውስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ቁጥር ማነስ የተነሳ ከሌሎቹ የአውሮፓ አገሮች ሲነጻጸር በብዛት ትንሽ ኢትዮጵያዊያን ይኑሩባታል ተብላ የሚነገርላት ሃገረ ኖርዌይ እነሱ ግን ለኢሳት ያላቸውን አጋርነታቸውንና ባለቤትነታቸዋን በተሳካ ሁኔታ ለጀግናው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አሳይተውታል።
በኖርዌይ ሰአት አቆጣጥ 16: 00 ተጀምሮ ከምሽቱ 01:00 ሲጠናቀቅ ህዝቡም ጥሪውን አክብሮ በተነገረው ቦታና ሰአት የተገኘ ሲሆን የኢሳትንም አጋርነቱን ባደረገው ድጋፍና እርብርብ ሲገልጽ አምሽቷል በዝግጅቱም ላይ ከተለያዩ ሲቪክ ማህበረሰቦችና ታላላቅ እንግዶች የተገኙ ሲሆን እንግዶቹም በተሰጣቸው የአየር ሰአት ኢሳትን እንዴት አድርገን በሁለት እግሩ እናቁመው በሚል ምክር አዘል ሲመክሮ ነበር።
በተያያዥነትም ሎተሪዎች ና በታወቁ የምግብ አዘጋጁች የተሰራ ምግብ እየተመገቡና መጠጦችን እየተጎነጩ ምሽቱን በታላቅ ደስታና ፍቅር በአንድነት ሆነው አሳልፈዋል ።
ቪዲዮውን በቅርቡ ይለቀቃል
ቪዲዮውን በቅርቡ ይለቀቃል
ኢሳት የኢትዮጵያኖች አይንና ጆሮ ነው
ኢትዮጵያ ተከብራ ለዘልአለም ትኑር
No comments:
Post a Comment