Friday, January 25, 2013

በሙስሊም ወንድሞቻችን እየደረሰ ያለውን እንግልትና እስራት እንዲሁም መሪዎቻችን ይፈቱልን በሚል የሚደረገው ተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ቀጥሎ ውሎአል።

እስክንድር አሰፋ ከኖርዌይ
25.01.2013

በሙስሊም ወንድሞቻችን እየደረሰ ያለውን እንግልትና እስራት እንዲሁም መሪዎቻችን ይፈቱልን በሚል የሚደረገው ተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ቀጥሎ ውሎአል።በ29ኛው አፍሪካ ዋንጫ እግር ኳስ ጨዋታ ላይም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያኑች በተገኘው አጋጣሚ     የወንድሞቻቸውን የትግል አጋርነት ለመግለጽ በተላያየ መፈክሮች በማሳየት ላይ ይገኛሉ ። 



በመቶ ሺ (100.000 ) ዎች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዛሬም በመዲናችን አዲስ አበባ  ምሬትና ሃይለቃል በተሞላ መፈክሮችን  ሲያሰሙ ውለዋል ። ከመፈክሮቹም  መሃል እንዲህ የሚሉ ይገኙበታል ፡-በቃላችን እንጸናለንኮሚቲዎቻችን ይፈቱሰለቸን ውሸት አሸባሪ አይደለንም ፤ አንለያይም የሚል ነበር መንግስት በግዜ ብዛት ሲደክማቸው ያቆማሉ በማለት  በተሳሳተ አስተሳሰብ ለችግሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ህዝብን በሃገሩ ላይ የሃይማኖት ነጻነቱ እንዳይከበር በእስልምናውና በክርስትናው ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ በመግባት  ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ከዚህ እረግጠህ ግዛ  አካሄዱ  ልንገነዘብ እንችላለን።

 በስተመጨረሻም   ለዚህ ሁሎ እረብሻ ና የህዝብ  ነጻነት አለመከበር   በዋናነት ተጠያቄ ሊሆን የሚገባው  በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት ነው ስለዚህም በውጭም ሆነ በውስጥ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ነን የሚሉ ኢትዮጵያዊያን  ሁሉ የታሪክ ተወቃሽ ከመሆናቸው በፊት ልዩነታቸውን ለሌላ ጊዜ ተወት አድርገው እጅ ለእጅ ተያይዘው ሃገራቸውን  ከወደቀችበት አዝቅት ውስጥ ቢያወጧት መልካም ነው  እላለሁ።

  ያለበለዚያ እነሱም ከተወቃሽነት አይድኑም ፤ ጅብ በቀደደው እንደሚባለው ሁሉ ሙስሊም ወንድሞቻችን በጀመሩት ሰላማዊ  ትግል ላይ እኛም የሃገሪ ጉዳይ ያገባኛል የምንል ዜጎች ሁሎ ጊዜው ሳይረፍድብን አንድ ሆነን በህብረት  እንነሳ ።

 ድል በገዢዎች እጅ ተጨቁኖና ተረግጡ ለሚኖረው ለኢትዮጵያ  ህዝብ

      ኢትዮጵያ ለዘልአለም  ተከብራ ትኑር

                 
    

No comments:

Post a Comment