Wednesday, January 30, 2013

በሃገራችን ውስጥ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ እለት ከእለት እያየለ መምጣቱና ሃገራችን ኢትዮጵያ የግለሰቦች መላገጫ ሆና መቅረቷም ዘወትር ህመምዋ ህመማችን ሆኖ እንዲሰማን ያስፈልጋል ያለበለዚያ አንዱ ለአንዱ ስንጠቋቀም ከእጃችን አምልጣ የታሪክ ተወቃሾች እንዳንሆን መጠነቀቅ ያስፈልጋል ።

ሁልጊዜ ስለሃገሬ ሳስብ ያመኛል ስለዚህ ለምን ጫርጫር አላረግም ብዬ ይህንን ብሶቴን አወጣሁት እስቲ አንብቡት ።
እስክንድር አሰፋ ከኖርዌይ 
  31,01,2013
                                           ህመሙ አመመኝ

ህመሙ አመመኝ

ውስጤን አቃጠለኝ

የ 21 አመቱ የወገኔ እሮሮ

 ውስጤን አሳርሮ

ብእር እንዳነሳ 

አረገኝ ዘንድሮ የወገኔ አበሳ

ለ 21 አመታት ወገኔን የገዛ

ኢትዮጵያዊ አልለው ክፋቱ የበዛ

በዘር ከፋፍሎ ሃገርን የገዛ

መሪት አሳልፎ የሚሸጥ ለባዳ

ለ 21 አመታት የሆነብን ባንዳ

ልንለው ይገባል ህመሙ አመመኝ

የወገኔ ብሶት ውስጤን አቃጠለኝ
ምሽግ መሽግ አለኝ
ብረር ጫካ ግባ ሀገር አድን አለኝ
የወገኔ እሮሮ ስላንገበገበኝ
                                

                        ኢትዮጵያ ተከብራ ለዘላለም ትኑር  

No comments:

Post a Comment