Published On: Mon, May 7th, 2012
በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እያካሄዱ ነው ፣ከፍተኛ ነውጥም ተነስቶአል ከ300 ተማሪዎች በላይ በአማራ ክልል ፖሊስ ታስረዋል።
በደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ የተማሪዎች የነውጥ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል በትላንትናው እለት የተጀመረው የተማሪዎች እረብሻ ዛሬ ረገብ ብሎ ቢዉልም መንግስት የምንፈልገውን እስካላስተካከለልን እንቀጥላለን በማለት ዉሳኔአቸውን ሲገልጹ ውለዋል ። የዚህ የተማሪዎች ነውጥ ጉዳይ የተነሳበትን መንስኤ በትምህርት ቤት ዉስጥ የሚገኘው የምግብ ጥራት ከፍተኛ የንጽህና ጉድለት ያለበት ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ተማሪዎች ለምግብ ወለድ በሽታ መጋለጣቸውን አንዳድንድ ተማሪዎች ጠቁመዋል ። መንግስት የትምህርት ቤቱችን ጥራት ፋሲሊቲ አሟልቻለሁ እያለ የሚደሰኩረው ውሸት ነው ምንም የተሟላ ነገር የለም በባዶ ነው ትምህርት ቤት ዉስጥ ጊዜአችንን የምናሳልፈው ይህ ደግሞ የእውቀት መገብያ እንጂ እድሜ ማሳለፊያ ወይንም መዝናኛ ክበብ አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ መስተካከል የሚገባቸውን ነገሮች ሳይፈታላቸው ሃሳባቸውን መለወጥ እንደማይፈልጉ ጠቁመዋል ። የማለዳታይምስ ዘጋቢ አቡጊዳ ከስፍራው እንደዘገበው ከሆነ በአሁን ሰአት የተወሰኑ ተማሪዎች ወደ ግቢ በሰላማዊ መንገድ ገብተዋል…..በርካታ በግምት ከ300 ተማሪዎች በላይ ታስረዋል….እጅግ በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል…..አንድ አንድ ተማሪዎች አምልጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደዋል…..ለተማሪዎቹ የትራንስፖርተ አገልግሎት ለመስጠት ሲሯሯጡ የነበሩ ደላላዎችም ታስረዋል….በሌላም በኩል ከባህርዳር ወደ ደብረማርቆስ የተላከው ልዩ እዝ የመከላከያ ወታደር እና የፖሊስ ሰራዊት ወደ ግቢው በመግባት ተማሪዎቹን አፍሶ እንደወሰደ የደረሰን ሪፖርት ያመለከታል ።ይህ የተማሪዎች ነውጥ በዚሁ ከቀጠለው ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እንዳይዛመት ተሰግቶአል ሆኖም ግን ከተዛመተ የገዢውን መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ ሊከተው እንደሚችል አንዳንድ ግለሰቦች ግልጸዋል ።በተለይም እስላም ክርስቲያን አማራ እየተባለ በተለያዩ ነገሮች ላይ ምንግስት ጸብ የጫረባቸው ነገሮች ሁሉ ከኑሮው ጋር ተደማምሮ ህዝቡን ለአመጽ እየገፋፋው እንደሆነ እና ህዝቡም አማራጭ አጥቶ ዝምታውን እንደመረጠ ስማቸው እንዳይገለጽ የፖለቲካ ተንታኝ ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment