Tuesday, May 15, 2012

የኔቶ ተቃውሞ ተሰላፊዎች ሳይጀመር ዘብጥያ መውረድ ጀመሩ ፣ቺካጎ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገች ነው ::


Share in top social networks!
በዚህ ቀጣይ ሳምን የሚከናወን የኔቶ አለማቀፍ ስብሰባን አስመልክቶ ከመላው አለም ጉዞአቸውን ያደረጉት የኔቶ ተቃዋሚ ተወካይ ማህበረሰቦች በዛሬው እለት እና በትላንትናው እለት በተካሄደው አጭር የኔቶ ስብሰባ ፕሮግራም መሰናዶ ላይ ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ የነበሩ 26 ከተለያዩ አለማት የመጡ ተቃዋሚዎች እና 2 ከቺካጎ መታሰራቸውን በቺካጎ የሚገኙ ሚዲያዎች ገለጹ ። በተለይም ኤቢሲ ኒውስ ከኔቶ ስብሰባ ማእከል ከሚገኝበት ቦታ በመገኘት ዘገባውን ያለቀረ ሲሆን አብዛኞቹ ህገወጥ ስራ ከመስራታቸውም በላይ ፍቃድ ያልተሰጣቸውም ናቸው ሲል ክስ በፖሊስ እንደተመሰረተባቸው ጠቁሞአል ። የቺካጎ ከተማ መጭውን የኔቶ ፕሮግራም ለማስተናገድ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ የነበረች ሲሆን ባለፉት ወራቶች የፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ አማካይነት ወደ ካምፕ ዴቪድ የተለወጠው የጂ8 ስብሰባም በዚሁ ከተማ ይከናወናል ተብሎ ታቅዶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል ። ይህ በእንዲህ እንዳለም በመጭው ሳምንት የሚከናወነውን የዚህ የኔቶን ስብሰባ አስመልክቶ የቺካጎ ከንቲባ ራህም ኢማኑኤል ረብሻ ከተፈጠረ በማለት ትልልቅ የማረሚያ እስርቤቶችን ማዘጋጀታቸውን እና የፖሊስ ሰራዊቶቻቸው በንቃት ጥበቃቸውን እንዲያካሂዱ ጥሪ ሲያቀርቡ ከነገ ጠዋት ጀምሮ የመንገድ እና ትራንስፖርት አገልግሎት ሰአት ከቀድሞው የሚያገለግሉበት ሰአት በታም በተወሰነ መልኩ የተቀነሰ ከመሆኑም በላይ የባቡር መስመር ከሰሜን ቺካጎ ሃዋርድ ተነስቶ ወደ 95 ደቡብ አቅጣጫ የሚጓዘው ሬድ ላይን ወይንም ቀይ መስመር የተሰመረበት ባቡር አግልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ተገልጾአል ፣ማናቸውም የግል መኪኖች በመንገድ ላይ የሚያደርጉትም የመኪና ማቆም ለአንድ ሳምንት እስከ አምስት ብሎክ ርቀት ድረስ የተከለከለ ሲሆን በስራ ሰአት የሚደረጉ ጉዞ መስመሮች ሁሉም በተለያዩ አቅጣቻዎች ሲቀየሩ ማናቸውም ትራንስፖርቶች ከደቡብ ሲርማክ ተነስተው ወደ ሰሜን ሌክ ሹር ይሚጓዙ በሙሉ መንገዱ ዝግ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል ። በዚህ ሳምንት የሚደረገውን ስብሰባ ከስፍራው በመሄድ በመከታተል የምንዘግብ መሆንኑን እንገልጻለን ።

No comments:

Post a Comment