Wednesday, February 26, 2014

ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ (ምን አለሽ መቲ) እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሐ/ተወልድ ኦስሎ ገቡ

ቅዳሜ March 01, 2014  ኢሳት የኔ ነው ምሽት በኦስሎ ዝግጅት ላይ በእንግድነት የተጋበዙት ጋዜጠኛ መታሰቢ ቀጸላ(ምን አለሽ መቲ) ከለደን እና ደረጀ ሐ/ተወልድ ከአመስተርዳም ዛሬ እሮብ Feb 26,2014 Oslo ገብተዋል።ባሳለፍነው ቅዳሜ Feb 22,2014 በተመሳሳይ ፕሮግራም ሲዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተዘጋጀው ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በመገኘት ዝግጅታቸውን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁት  ወገኖቻችን የመጨረሻ ጉዞአቸውን ወደ ኖርዌይ በማቅናት ዛሬ ከሰአት በኋላ በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር 15;30 በሰላም ገብተዋል። የኖርዌ ኢሳት ኮሚቴ ተወካዩችም ተወዳጆቹን ጋዜጠኞች በሰአቱ አይሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመሄድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


  እስክንድር አሰፋ /ኖርዌ

Monday, February 24, 2014

(ዜና ድንቅ) የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት የጸረ ግብረሰዶም ህጉን ፈረሙበት!

የኡጋንዳ ፓርላማ ፣ አንዳንድ ግብረሰዶማዉያንን እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ እስራት ለመቅጣት ያሳለፈውን ህግ፣ ፕሬዚዳንት እንዳይፈርሙበት፣ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ከአንዳንድ የሰብ አዊ መብቶ ድርጅቶች ግፊት ቢደረግባቸውም፣ ዛሬ ፈርመውበታል።
አስቀድሞ ፓርላማው ግብረሰዶማዊ የሆነው ሰው ከህጻናት ጋር ሲፈጽም ከተገኘ ወይም ኤች አይ ቪ እንዳለበት እያወቀ ድርጊቱን ከፈጸመ በሞት ይቀጣ ሲል ህግ ቢያወጣም፣ ፕሬዚዳንቱ ፣ የሞት ቅጣቱ ካልቀረ አልፈርምም ሲሉ ቆይተዋል። በኋላ ቅጣቱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ተቀየረ። በዚህ መካከል የኡጋንዳ ሳይንቲስቶች “ግብረሰዶማዊነት የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፣ ወይም በፍላጎት የሚፈጸም?” የሚለውን አጥንተው እንዲነግሯቸው ፕሬዚዳንቱ አዘዙ። ሳይንቲስቶቹም “ምንም እንኳን ግብረሰዶም መፈጸም በሽታ ነው ማለት ባይቻልም፣ በተፈጥሮ የሚመጣ ሳይሆን ሰዎች ፈልገውና ተለማመደው የሚያደርጉት ነው” ሲሉ ነገሯቸው።
አሁን በቃ ልፈርም ነው ሲሉ በመናገራቸው ወዲያው ፕሬዚዳንት ኦባማ “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ” አይነት መልክት ላኩባቸው፣ እሳቸውም “እሺ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች፣ ነገሩ የተፈጥሮ ነው (ሰዎች ግብረሰዶማዊ ሆነው ነው የሚወለዱት) የሚለውን ነገር መጥተው ለኔና ለሳይንቲስቶቼ ያስረዱን” ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። ይህን ካሉ ቀናቶች አለፉ። እንግዲህ መጥቶ ያስረዳቸው የለም ማለት ነው። ዛሬ ህጉን ፈርመዋል። በኡጋንዳ ግብረሰዶማዊነት እስከ 10 ዓመት በ እስር ሲያስቀጣ፣ ነገሩ የተፈጸመው ከህጻን ጋር ከሆነ እስሩ እስከ ዕድሜ ልክ ይሆናል። በነገራችን ላይ በዚህ ህግ መሰረት ግብረሰዶም ፈጻሚዎች አይቶ ለፖሊስ ያልጠቆመም እንዲሁ እስር ይጠብቀዋል። (ዜናውን ዴይሊ ቢስትና አልጀዚራ ዛሬ አወሩት – ድንቅ መጽሔት ተረጎመው)

▶ Protests Against EPRDF In Bahir Dar Feb 2014

February 23, 2014 – UDJ and AEUP held a large protest rally this morning in the city of Bahir Dar. One of the messages the protesters voice is their outrage over the recent ethnic slur against the Amhara people by Alemnew Mekonnen, a senior official of the ruling EPRDF/TPLF junta.

መኢአድና አንድነት በጋራ የጠሩት የባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን በቅርቡ የአማራው ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋና ስድብ በመቃወም ነው ባህር ዳር ተቃውሞውን ያስተናገደችው



Tuesday, February 18, 2014

እኔና ወላጆቼ!

አብርሃ ደስታ


ዛሬ አንድ የዉስጥ መልእክት ደረሰኝ። ቁምነገሩ "ወላጆችህ ላንተ ብለው መስዋእት ከፈሉ፣ አስተማሩህ፣ ባጭሩ ለዚህ አበቁህ። አንተ ግን እነሱን ትቃወማለህ!" የሚል ነው።

አዎ! ወላጆቼ መስዋእት ከፍለዋል። ግዜው በሚፈቅደው መንገድ አምባገነኖችን ለማስወገድ ታግለዋል። ሲታገሉ ዓላማ ነበራቸው። ዓላማቸውም ነፃነት ነበር። መስዋእት የተከፈለበት ዓላማ አንድ አምባገነን (ደርግ) በሌላ አምባገነን (ኢህአዴግ) ለመቀየር አልነበረም።

አዎ! መስዋእት ከፍለዋል። የተከፈለው መስዋእት ለስልጣን አልነበረም፣ ለዴሞክራሲ እንጂ። ለስልጣን መስዋእት መክፈል አያስፈልግም። ምክንያቱም ከተሰዋህ፣ ከሞትክ ስልጣን የት ታገኘዋለህ? ዓላማህ ስልጣን መያዝ ከሆነ እስከ ሞት የሚደርስ መስዋእት መክፈል የለብህም። ምክንያቱም ከሞት በኋላ ስልጣን አይገኝም።

ወላጆጃችን ግን መስዋእት ከፈሉ። መስዋእት የሚከፈለው ለነፃነት ነው። የመስዋእት ዓላማ ነፃነት ነው። ወላጆቻችን መስዋእት ሲከፍሉ እኛ ልጆቻቸው በነፃነት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የፈለግነውን መደገፍ፣ ያልፈለግነውን ለመቃወም፣ ወይም በፈቃዳችን መሰረት መደገፍም መቃወምም ለመተው ነበር። በምርጫችን ስንኖር የሚደርሰንን በደል እንዳይኖር ነው። እኔ በዚሁ መሰረት ወላጆቼን በከፈልሉኝ መስዋእት መሰረት በነፃነት ለመኖር እየሞከርኩኝ ነው። 

በነፃነት ለመኖር ሲፈልግ መቃወም ሲፈልግ ደግሞ መደገፍ አለብኝ። ህወሓት ግን የኔን መቃወም ይቃወማል። ምርጫዬ ሁኖ መቃወም ሲፈልግ እንደ ጠላት ያየኛል፤ ከሃዲ ይለኛል። የትግራይ ወጣት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባል መሆን አለበት እያለ የፓርቲ አባል ያለመሆን ፍላጎቴንና መብቴ ይጥሳል። የህወሓት አባል ባለመሆኔ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እንዳላገኝ ያደርጋል። የተከፈለው መስዋእት ግን ለዚህ አይደለም። ስለዚህ ህወሓት የሰማእታትን አደራ አፍርሷል፤ የነፃነት ዓላማው በስልጣን ቀይሮታል።

እንዲህ ከሆነ ታድያ እንዴት ህወሓትን አልቃወምም? ህወሓትን በመቃወም የወላጆቼን የነፃነት ዓላማ ከግብ አደርሳለሁ። ወላጆቼ ለኔ ነፃነት ከታገሉ ያመጥሉኝን ነፃነት ብጠቀም ችግሩ ምንድነው? የወላጆቼን ዓላማ ለሚጠመዝዝ አካል ብቃወም ችግሩ ምንድነው? ስለዚህ ህወሓት መቃወሜ ትክክል ነው። ምክንያቱም መስዋእት የተከፈለበት ዓላማ መተግበር አለበት። የህወሓት ተግባር ፀረ ሰማእታት ዓላማ ነው።

.
.
.

ወላጆቼ የታገሉት ለራሳቸው ነው። (እላይ ከፃፍኩት የሚቃረን ይመስላል፣ ግን ሌላ መንገድ ነው)። ለኔ ሊሆን አይችልም። ወላጆቼ የራሳቸው የህይወት መንገድ አላቸው። የነሱ ጀግንነት ለራሳቸው ነው። ለኔ ሊሆን አይችልም። የወላጆቼን መንገድ መከተል ካለብኝ፣ የወላጆቼን አደራ መተግበር ካለብኝ ልክ እንደነሱ ጀግና መሆን አለብኝ። በወላጆቼ ጀግንነት መዋጥ ሳይሆን የራሴ የሆነ የጀግንነት ታሪክ ሊኖረን ይገባል። ወላጆቼ ገዢውን መደብ ተቃውሞው ለነፃነታቸው ታገሉ፣ ጀግንነት ፈፀሙ። እኔስ እንደነሱ ገዢውን መደብ በመቃወም ለነፃነቴ ብታገልና ጀግና ብሆን ችግሩ ምንድነው?

አባትህ ጀግና ስለነበረ ባባትህ ጀግንነት ኑር፣ የራስ ህ የጀግንነት ታሪክ ሊኖርህ አይገባም ያለ ማነው? ባባትህ ጀግንነት የምትኮራ ከሆነ ለምን አንተ ራስህ ጀግና ለምሆን አትሞክርም?

እመኑኝ! ወላጆቼ ታግለው ደርግን ባያባርሩ ኑሮ እኔው ራሴ በደርግን እታገለው ነበር። ወላጆቻችን ደርግን ስለታገሉ እኛ ልጆቻቸው ህወሓትን መታገል የለብንም ያለ ማነው? ማንም ይሁ ማን ፀረ ነፃነት የሆነ ስርዓት ካለ መቃወም አለብን።

አዎ! በህወሓት ዘመን ነው የተማርኩት። ግን በህወሓት ግዜ ስለተወለድኩ ብቻ ነው። በሌላ ስርዓት ብወለድ ኑሮ በሌላ ስርዓት እማር ነበር። ህወሓት ዜጎችን የማስተማር ግዴታ አለበት (በስልጣን እስካለድረስ)። ያስተማረንን ስርዓት መቃወም የለብንም የሚል ሎጂክ ካለ ግን የህወሓት መሪዎችም የሃይለስላሴና የደርግ ስርዓቶች መቃወም አለነበረባቸውም ማለት ነው። ምክንያቱም የህወሓት ባለስልጣናት የተማሩት በህወሓት አይደለም፣ በሃይለስላሴና በደርግ ስርዓቶች እንጂ።

እኔ የተማርኩት ሀገርንና ህዝብን ለመለወጥ እንጂ ታማኝ የገዢው መደብ አገልጋይ ለመሆን አይደለም። የተማርኩት ሀገርን የሚጠቅም ነገር ለመስራት እንጂ የፓርቲ ካድሬ ለመሆን አይደለም። ደግሞ የተማርኩት በመንግስት ሃብት (በህዝብ ሃብት) እንጂ በህወሓት (በፓርቲ) ሃብት አይደለም። ስለዚህ በሀገር ሃብት ከተማርኩ ለሀገር እድገት መስራት አለብኝ። ይህም እያደረግኩ ነው።

Ethiopian political refugee living in London alleges he was victim of 'unprecedented example of espionage on British soil'




National Crime Agency urged to investigate after discovery of surveillance software on a computer belonging to Tadesse Kersmo

The National Crime Agency has been asked to investigate the alleged use of computer software to spy on an Ethiopian political refugee living in London in an unprecedented example of espionage on British soil.

The charity Privacy International has made a criminal complaint to the agency’s National Cyber Crime Unit following the detection of the surveillance software FinSpy on a computer belonging to Tadesse Kersmo, who fled to Britain from Ethiopia in 2009.
FinSpy, a “Trojan” programme which was developed and produced by the British-German company Gamma International, allows a remote user to gain full access to a targeted computer and even to turn on functions such as microphones and cameras to record the computer’s owner without their knowledge.

Mr Kersmo, a university lecturer, claimed that he had been the victim of espionage by the Ethiopian Government because of his involvement with the political opposition group Ginbot 7. “I felt that the United Kingdom was a safe and free country but I was wrong and I feel very disappointed,” he said.

The FinSpy surveillance software first appeared on his computer in 2012 and was only detected after the issue was highlighted in a study by the Citizen Lab at the University of Toronto, which reported on a campaign to infect computers with FinSpy by sending a rogue email containing pictures of Ginbot 7 members.

Mark Scott, a lawyer with London firm Bhatt Murphy, said there was no legal justification for the software. “If your computer is in the UK and it’s intercepted and that’s without lawful authority then that is a crime. It’s very difficult to see what lawful authority.”
Mr Scott said he knew of no other similar incidents.

Mr Kersmo told a London press conference on Monday that documents and audio clips from Skype conversations involving him and other Ginbot 7 members had been published in doctored format online in order to discredit him. He said that the leaders of Ginbot 7 – a pro-democracy group formed from Ethiopian exiles in the United States and Europe – had feared they had a mole in their ranks. “The main purpose was probably to create suspicion among the executive committee members and it did to some extent.”

Calling on the NCA to investigate, he said: “It’s not only (about) my own personal liberty but also the UK’s interests and other Ethiopian citizens who live in the UK.”

Eric King, head of research for Privacy International, said: “Even when someone flees persecution in their own country, western-made surveillance technologies such as FinSpy can still be used by repressive regimes to monitor the moves of political activists anywhere around the world.”
The charity said that FinSpy was extremely difficult to detect. Trojan programmes are usually triggered by opening an email or download containing the invasive software.

According to the Citizen Lab research, command and control servers for FinSpy have been set up in 35 countries, including Ethiopia, Turkmenistan, Bahrain and Malaysia. Privacy International has asked HMRC to say whether Gamma International has an export licence for distributing the software to these regimes. Mr Scott said: “If the software needs to be exported to a country outside the European Union it requires an export licence. As far as the information we have, there has been no licence granted to Ethiopia or indeed any other country.”

John Campbell, a senior lecturer at the University of London’s SOAS, said the FinSpy case had “extensive implications” for the Home Office and could lead to more asylum claims if political opponents were being subjected to computer espionage. He said that scores of Ethiopian political dissidents had been arrested since the 2005 national elections and that some had been given life sentences.
Gamma International could not be reached for comment

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን ተላልፎ ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም።


ከፋሲል የኔአለም (ጋዜጠኛ)
Feb 18.2014

አንደኛ፣ ኢትዮጵያ የሞት ቅጣትን ተግባራዊ የምታደርግ አገር ናት። 
ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ጥሰት በአለም የምትታወቅ ናት።
ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ( extradition treaty) የላቸውም::
አራተኛ፣አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝም ብለው አይቀመጡም።

አምስተኛ፣ እንደሚባለው ጭንቀት ኖሮበት ድርጊቱን ከፈጸመም የበለጠ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለስ ያደርገዋል። ምክንያቱም በስደተኝነት ህግ የአእምሮ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች ጥገኝነት ለማግኘት ከፍተኛ እድል አላቸውና።
ስድስት፣ የአእምሮ ጭንቀቱ መንስኤ የቅርብና ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ ከሆነ ደግሞ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጉዳዩን ይበልጥ ያከብድለታል ምክንያቱም የአጎቱ ሞት መንስኤ እስካሁን እንቆቅልሽ እንደሆነ አለና። እህቱ የጻፈችውም ደብዳቤ የሃይለመድህንን ችግር ይበልጥ የሚያሳይ ነው ። "ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ፣ ስልኩን እንደጠለፉት እንደሚያስብ፤ በላፕቶፑ ካሜራ ሳይቀር ያዩኛል ብሎ ስለሚሰጋ ካሜራውን ሳይሸፍን እንደማይከፍት እንዲሁም፤ ወጥቶ እስኪገባ ቤቱን ሲበረብሩ የቆዩ ስለሚመስለው ካሜራ ጠምዶ መሄድ " መጀመሩን መግለጿ፣ የሃይለመድህ መሰረታዊ ችግር የደህንነት ዋስትና ማጣት መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የደህንነት እጦት (insecurity) የሚያሳይ ነው። በቤተሰቡ በተለይም በአባቱ ላይ ተከፍቶ የነበረው የማጥፋት ዘመቻም ለጭንቀቱ መንስኤ ሊሆን ይችላል።

የሃይለመድህን ድርጊት ባለሁለት ሰይፍ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በሁለቱም ሰይፍ መቆረጡ አይቀርም። ፓይለቱን የአእምሮ በሽተኛ አድርጎ ቢያቀርበው፣ ለአየር መንገዱ ትልቅ ኪሳራ ነው። መንገደኞች ከእንግዲህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጓዝ ድፍረቱ አይኖራቸውም፣ ለዚህም ይመስለኛል አቶ ሬድዋን ፓይለቱ ሙሉ ጤነኛ ነው ሲሉ መግለጫ የሰጡት። ወጣቱ ለስደት መጠየቂያ በማሰብ የወሰደው እርምጃ ነው ቢሉም፣ " በደህና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሰው እንዴት ስደትን ሊመርጥ ቻለ?"፣ ከስደት የከፋ ችግር ቢያጋጥመው ነው ተብሎ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ መነሳቱ አይቀሬ ነው። መንግስት ግራ ሲጋባ ይታየኛል።