ሰበር ዜና፤ ከመቀሌ
የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ አርአያ፣ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ፀሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀነ በመቀሌ ከነ መቀስቀሺያ ሞንታረቮአቸው ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሩ፡፡ አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና አቶ ክብሮም ብርሀነ ለሁለተኛ ጊዜ እንደታሰሩ ልብ በሉ!!! የመቀሌ ነዋሪዎች አመራሮቹን ለማስፈታት ከፖሊስ ጋር እየተከራከሩ ነው። የመቀሌ ነዋሪዎች በአንድነት ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡ የመቀሌ አንድነት አባላት ላይ የሚደርሰውን እስር እና ወከባ ፊት ለፊት በመቃወም ላይ ናቸው፡፡ የአንድነት አባላት ሲቀሰቅሱበት የነበረውን ሞንታርቦና ጄኔሬተር በፖሊስ ተነጥቀዋል።

ሰበር ዜና፤ ባህር ዳር
ነገ ሐምሌ 28 ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተጠናከረ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው፡፡ የባህር ዳር እና የአካባቢዋ ነዋሪዎችም በተቃውሞው ሰልፉ ላይ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢዎች ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግም የባህር ዳር ህዝብ ባሳየው ንቁ ተሳትፎ በመደናገጡ በተለያዩ ቤተ ክርስትያኖች ቅዳሴ ዘግይቶ እንዲጀምር ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ቀበሌዎችም የተለያዩ ስብሰባዎችን አስጠርቷል፡፡ ባህር ዳሮችም ነገ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድመቅ የተለያዩ መፈክሮችን በየቤታቸው በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡
ሰበር ዜና ከአርባምንጭ
በአንድነት ፓርቲ በሁለት መኪናዎች አርባምንጭን በቅስቀሳ አድምቋታል፡፡ በራሪ ወረቀቶች እየተበተኑ ነው ፖስተሮችም በብዛት እየተለጠፉ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች “ሰልፉ ላይ እንዳትወጡ” የሚል ቅስቀሳ ቢያደርጉም የአርባምንጭ ነዋሪዎች በሰልፍ ላይ ለመገኘት መወሰናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
ሰበር ዜና ከጅንካ
ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው፡፡ ከአጎራባች አካባቢዎች በሰልፉ ላይ የሚሳተፉ ዜጎች ወደ ጅንካ እየገቡ ነው፡፡ ከትላንት ጀምሮ ፖስተሮች እንዳይቀደዱ የአካባቢው ህዝብ እየጠበቀ ነው፡፡ በኢህአዴግ ካድሬዎች በ 1 ለ 5 መዋቅር ሰልፍ አትውጡ በሚል የጀመረው ቅስቀሳ ከሽፏል፡፡ #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
No comments:
Post a Comment