Monday, August 12, 2013

የፖለቲካ ጋብቻ ከሃይማኖቶች ጋር ለመፈጸም የሚዳራው ወያኔ ኢህኣዴግ ነው!!! የስልጣን ጥምን ማርካት ወይንስ የፖለቲካ እውቀት ማነስ?



ምንሊክ ሳልሳዊ

መካሪ ቄስ/ፓስተር ያጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ
ጠ/ሚሩ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚያራምዱት ኢፍትሃዊ አቋም የፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያናቸውም ነጸብራቅ ውጤት ነው::በተለጣፊነት የሃገሪቱ የበላይ አካል ሆኖ አገለግላለው የሚለው ሃዋሪያዊው ሃይለማርያም ደሳለኝ ምነው መካሪ አጣ:: እኛ እኮ የጠበቅነው በሕወሓት ትእዛዝ የኢድን በኣል ለማክበር የወጡ ዜጎች በፖሊስ ሲጨፈጨፉ ጎመን በጤና ብሎ ስልጣኑን በገዛ ፍቃዱ ይለቃል ብለን ነበር::

ሆኖም ይባስ ብሎ የረባ አማርኛ እንኳን በማትችል ጋዜጠኛ ጥያቄ መሰል መልስ ተጠይቆ የመለሰው ነገር መንግስታዊ ጂልነት የተንጸባረቀበት ነው:: ምነው እነዚህ የሃዋርያት ፓስተሮች ምን ዋጣቸው ?ምእመናቸውን አይመክሩም እንዴ ? የጠሚያችንን ስልጣን ተገን አድርገው በሙስና ከመዘፈቅ መንፈሳዊ ምክርንም መለገስ አለባቸው:: ይህ አይነት አብዮታዊ ሃዋርያነት የትም አያደርስም::

በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በየጊዜው እየተቀያየር የመጣው ወንጀል ማንም ሰው ሊቀበልው አለመፈለጉን እና ኢተአማኒነቱ እየጎላ መምጣቱን የተገነዘበው ወያኔ አሁንም የፖለቲካ ጋብቻ በሚል ሰበብ ፈጥሮ ቀሪውን ዜጋ ለማጥቃት እያቆበቆበ ነው:: የፖለቲካ ጋብቻ እና መዳራት እየፈጠረ ያለው የወያኔው ጁንታ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም::ህገመንግስት እስካለ ድረስ የሙስሊሙ ጥያቄ ህግን መሰረት አድርገው መዳኘት እንዳለበት መንግስት በሃይማኖት እጁን ጣልቃ ማስገባቱ በይፋ እየመሰከረ መሆኑን እኛ ሳንሆን ባለስልጣናቱ የሚናገሩት ተደጋጋሚ ጉዳይ ነው::ሃይማኖት የለኝም የሚለው ሶሻሊስታዊው ደርግ ያልፈጸመውን ማፍያዊ ድርጊት ይህ የወያኔ ጁንታ እየፈጸመው መሆኑን ሁላችንም እንዳሳሰብን ስንገልጽ ብንቆይም እስከዛረ ሰላማዊው ትግል ወደ ጸብ ይቀየራል በሚል የዋህነት አይሉት ጸብኣጫሪነት ጎስት ወያኔ ጥርሶቹን አሹሎ ዜጎችን እያሸበረ ነው::

የፖለቲካ ጋብቻ የተፈጸመው በወያኔ መንግስት መሆኑ ብዙ ሳንርቅ ካደራጀው መጅሊስ ጋር ያለው መዳራት ከአህበሽ ጋር ወያኔ የሚፈጽመው እርኩስት እንዲሁም ስብሰባዎች ዝግጅቶች በጀቶች በራሳቸው ብዙ ሳንጓዝ ምስክሮች ናቸው :;አሁንም የሰላም ጉባዬ በሚል አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሃይማኖቶች ላይ የበላይነትን እንዲይዝ የሚደረግ የመዳራት ሩጫ በራሱ ምስክር ነው::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካለ አማካሪ በትእዛዝ የተናገሩት ነገር ነገ ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውንም የሚከተሉትን ሃይማኖትንም ከተጠያቂነት አያተርፍም:: የሚከተሉት ቤተክርስቲያም የተዘፈቀበት መንግስታዊ ሙስና አላላውስ ስላለው አስፈላጊውን መንፈሳዊ ኦረንቴሽን ለምእመኑ ባለስልጣን ሊሰጥ አለመቻሉ በሚያመልከው በሰማያዊው ብቻ ሳይሆን በምድራዊውም ህግ እንደሚጠየቅ ማወቅ አለበት::ጠ/ሚሩ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚያራምዱት ኢፍትሃዊ አቋም የፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያናቸውም ነጸብራቅ ውጤት መሆኑን ለመናገር እፈልጋለሁ::
ምንሊክ ሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment