Saturday, August 31, 2013

How Can We be Free? (Henoke Yeshetlla’s Poet, Part I)


August 30, 2013
by HENOKE YESHETLLA
How can we be free if we are shackled by the despondency of silence, even at the stake of the most dismissive, improbable and fatiguing house hold compliancy.
How can we be free, if we are keenly scrutinized by our self generated fear, if we are dwarfed by our tear, if we are mitigated by our delusional prosperity? How can we be free if we are pushed to the calamites of the cynical power and become the proponent of that power? History is secular and obscure for us, we don’t know that we have an inverted and diminished sense of view to what we clamed we knew, basking in the ambiance of self contradiction and having a contra positive personality is a well known yet calculated decisions for us, an amenable day to day life, a life that we endorse and die to live for…Who we are, what are we…? How can we be free?How Can We be Free (Henoke Yeshetlla
Our forefathers believed in God and lived not in the state of self exultation, nor we inherited this care free personality from them but we exhausted their hope and exulted in our failures. How can we be free, if we still believe in ignorance, in-sensitiveness, negligence and absurdity? How can we be free while being the power house of delinquency, blasphemy, an alien to the glimpse of fertility, phobic to an incessant struggle, and inferior to our own moral values and principles?
How can we be free, if we are silenced when the judge irrationally persecute and prosecute the innocence, the police arresting the teenagers and the elderly , the army kills the religious…how can we be free?
How can we be free, with a fluctuating self representation of ours to a palpitating incident ray of an un- free voices?
We are a feeble to our existence, always marching but to recede, always fighting but to surrender, always, fighting but to die, always grouping but to crack down, always standing but to fall! We have no objective nor values to die for, we have no stamina to the cause we believed is right, we are insufficient of our own sufficiency, we stick to what is called hit and run; we are truly a geek for our own calamity, a virus to our own flesh, and an assurance to our own disgrace! How can one be free?

Ethiopia arrests high-profile Intelligence official over corruption

Ethiopian police have arrested high-ranking intelligence official on allegations of corruption.
The Federal Ethics and Anti-corruption Commission said Woldeselasie Woldemichael, 
senior official of the nation’s spy agency was arrested on graft charges. Read more
Ali Suleyman, Commissioner of the Federal Ethics and Anti-Corruption Commission

Thursday, August 29, 2013

በፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰ ድብደባ

በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው እንግልትና ድብደባ ብሎም ግድያ  እየተባባሰ መምጣቱ እውነት ከልማቱ ጋር አብሮ እያደገ የመጣው የወያኔ እርአይ ውጤት  መሆኑ ነው  ልማታዊው ወያኔ ሐይ ባይ በማጣቱ  እያደረሰ ያለው መረን ያጣ ውንብድናና እረገጣ እጅ እጅ እያለ መጥቷል ስለዚህም  ወገን ስለ ሐገሪ ስለወገኔ ይሰማኛል ያገባኛል የምትል ወግን ሁሉ የአምባ ገነኑ የወያኔ  ገዢ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ መወገድ እንዲኖርበት የየራሳችንን አስተዋጽዎ ማድረግ ይኖርብና  ለዚህም  ምርጫችን አንድና አንድ ነው  እሱም  ወያኔ በቃህ በቃህ በማለትና እንዲሁም  በግንባር ግሮሮ ለግሮሮ እተናነቀዋለሁ ሕይወቴን ለሐገሬ መስዋት አድርጌ  እገብራለሁ  ብለው ለተነሱት ወገኖቻችንን ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሐይል ደጀን በመሆን አለንላችሁ ከናተ ጋር ነን በማለት እነሱ የተከበረ ሕይወታቸውን መስዋት ለማድረግ ሲወስኑ እኛስ ለነሱ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛው ተገቢ አስፈላጊ ነገሮችን የማቅረብ የውዴታ ግዴታ አለብን በማለት  አጋርነታችንን ማሳየት  ያስፈልጋል ።

ሐገራችን ኢትዮጵያ ለ3000 አመታት ተከብራና ተፈርታ የቆየችውን ያህል አሁን በ22 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ተናግረውት የማይጨርሱ ሐገራዊ ክብሯ የተዋረደበትና ሕዝቦቿ ኢ ስብአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው ሐገር ለቀው በመሰደድና እንዲሁም በተቃዋሚ ጎራ ውስጥ ተሰልፈው እንታገላለን የሚሉትን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራና ስቃይ የምናውቀው የምናየው ስለሆነ በዚህም ከቀጠለ መጨረሻው ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም ።

በቅርቡ በፍቼ ከተማ ለቅስቀሳ  ከተጓዙት የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል  መራሹ የወያኔ መንግስት ያደረሰባቸውን ኢ ሰብአዊ ድርጊት  በማውገዝ የተሰማኝ ስሜትና በሐገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን አረመኔያዊው አገዛዝ ከስር ከመሰረቱ ለማፍረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን  እንድ በመሆን በኖርዌ ኦስሎ ከተማ  ሴብቴምበር 28 በሚደረገው ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሐይሉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ የየራሳችንን  ሐገራዊ ግዳጃችንን  እንድንወጣ ያስፈልጋል በማለት መልእክቴን አስተላልፋለሁ  ። የወያኔ አገዛዝ በቃህ በቃህ  ማለት ያስፈልጋል   ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵ ቸር ያሰማን።

ኢትዮጵያ ለዘልአለም ተከብራ ትኑር

እስክንድር አሰፋ
ኦስሎ ኖርዌ

ፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰው ድብደባ ከተጠቂዎቹ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ  ይመልከቱ




Wednesday, August 28, 2013

KIF kvinner i Fokus KVINNEKONFRERANSE 24 AUGUST 2013 PART ONE AND TWO

KIF KVINNEKONFRERANSE 24 AUGUST 2013 
"vår stemme , vår makt " hvor står  
minoritetskvinner i Norge i 2013?


SE  PÅ YOUTUBE,    PART ONE  , https://www.youtube.com/watch?v=4sjFAbc5RWk



KIF KVINNEKONFRERANSE 24 AUGUST 2013 PART TWO

PART TWO , https://www.youtube.com/watch?v=bWMSga-DcUc



Tuesday, August 27, 2013

Must-Watch] ETV Debate - EPRDF, UDJ, Semayawi Party, Medrek & EDP debate Anti-Terrorism Law - Part 2 | August 27, 2013

በኛ ሐገር በተወካዩች ምክር ቤት ይወከላል በሌሎች ሐገር ግን በአስፈጻሚ ዎች አካል እንሚፈተሙ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ ስለዚህ በተወካዩች ምክር ቤቶች እንዲሰየም የሆነበት ወይም አዋጁ ይህን ነሰረት ሲያደርግ ፍላጎቱ ምን ስለሆነ ነው ?

መልስ . አቶ ሽመልስ ከማልhttp://www.ethiotube.net/video/27470/Must-Watch-ETV-Debate--EPRDF-UDJ-Semayawi-Party-Medrek--EDP-debate-Anti-Terrorism-Law--Part-2--August-27-2013


 ሽብርተኞችን አንድን ድርጅት በሽብር ተግባር ውስጥ ስራዩ ብሎ የሚያከናውን መሆን ካለበት መሰየም አለበት መሰየም የመሰየም ዋንኛ አላማ በሽብር ስራው ውስጥ ተሰባስቦ ተገራጅቶ የሚንቀሳቀስ ወገን ማንኛውንም አይነት ማህበራዊ  ትብብር  ድጋፍ እንዳያገኝ ማድረግ ነው ዋንኛ ው ነገር ለ ሶስተኛ ወገኑች ይህን ድርጅት ማንነቱን ሳያውቁ በተለያየ መንገድ ለድርጅቱ የፋይናስ በሰው ሐይል ምልመላ ማቴሪያል ና ሎጆስቲክ ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ ግለሰቦችን ለማስጠንቀቅ ነው በዚህም አሸባሪዋች ይህችን ምድር የማትመች የማትመቻቸው ሲኦል እንዲሆንባቸው እንዲነጠሉ ለማድረግ ነው ሁሉም ሐገር proscription ወይም የስያሚ አካሄድና አሰራር አለ .............

4 ለ 3 በጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ላይ የተደረገ ክርክር

አንድነት ፓርቲ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን በህዝብ ድጋፍና ጥያቄ ለማሰረዝ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ የሚፈለገውን ግብ ለመምታቱ በገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ኢቴቪ በአዋጁ ዙሪያ የፓርቲዎችን አቋም የሚያንጸባርቅ መድረክ ማዘጋጀቱ ማሳያ ነው፡፡ኢህአዴግ ካድሬዎቹ አዋጁን በማንበብ አንድነቶች ለሚያነሱት መከራከሪያ ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ ትዕዛዝ ማውረዱም ሌላኛው የአደባባይ ድል ነው፡፡
በነቢብ የህዝብ በገቢር የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ኢቴቪ በአዋጁ ላይ ያላቸውን አቋም እንዲያንጸባርቁ የጋበዛቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ በአቶ በቀለ ነጋዓ፣አንድነት በሃብታሙ አያሌው፣ኢዴፓ በሙሼ ሰሙ፣ሰማያዊ በይልቃል ጌትነት፣ ኢህአዴግ በሽመልስ ከማል፣በጌታቸው ረዳና በኢቴቪው ጋዜጠኛ ተወክለዋል፡፡
ክርክሩ በተራ መቀስ የተቆራረጠ መሆኑ
ኢህአዴግ ከምርጫ 1997 በኋላ በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት የሚተላለፉ ክርክሮች ፎብያ የተጠናወተው በመሆኑ live debate አይመቸውም፡፡እናም ክርክሩ በቀጥታ አለመተላለፉ ለባለ መቀሶቹ ጥቅሙ ከፍ ያለ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው፡፡በሁለት ክፍል የተላለፈው ክርክር በተራ መቀስ መቆረጡን ለመመስከር ሶስተኛ አይን የማያስፈልግበትን አንድ ሁለት ነጥብ ልጥቀስ፡፡ከመሬት ተነስተው የኢህአዴጉ ተወካይ ተቃዋሚዎችን‹‹እንዴት ድራማ ነው ትላላችሁ››በማለት ይወርፏቸው ጀመር፡፡ክርክሩን ስራዬ ብሎ የተከታተለ ሰው እኚህ ሰው ለምን ያልተጻፈ ያነባሉ ብሎ ሊፈላሰፍ ይችላል፡፡ነገሩ ግን መዛባቱን የፈጠረው የሽመልስ ንግግር ሳይሆን ኢቴቪ ነው፡፡ ማለቴ መቀሱ፡፡
ጌታቸው ከዚህ በፊት አብሮኝ በአንድ መድረክ ሰርቷል ያሉትንና አሁን የአሰላለፍ ለውጥ በማድረጉ አንድነትን የተቀላቀለውን ሃብታሙን በነገር ወጋ ሲያደርጉት ታዝቢያለሁ፣ሃብታሙ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ የሚለው ነገር እንደሚኖር መጠርጠሬ አልቀረምና ተራው ደርሶ የሚለውን ለማድመጥ ጆሮዬን ቀሰርኩ ነገር ግን የሃብታሙ ንግግር ከመሃል እንደጀመረ በሚያሳብቅ መልኩ ለጌቾ ይሰጠዋል ብዬ የጠበቅኩት ምላሽ ሳይቀርብ ቀረ፡፡ሴኮ ቱሬ ክርክሮችን በመቆራረጥ ጥበብ የተካኑ እንደነበሩ በአንድ ወቅት የድሮው ልደቱ (አዲስ ልደቱ እንዳሉ ስለማምን የቀድሞው ለማለት ተገድጃለሁ)ተናግረው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ሴኮ አሁን ስለሌሉ የኢቴቪ አዲሱ መቀስ ብዙም በቆረጣ ባለመካኑ ቆረጣው አይን ያወጣ ሆኖበታልና አልተሳካም፡፡
ያልተጠየቀ ‹‹መመለስ›› የጆሮ ህመም ይሆን?
ተቃዋሚዎች በአንድነት በሚባል መልኩ አዋጁ ከህገ መንግስቱ እንደሚጋጭ በመግለጽ ጭብጥ ለማስያዝ ሞክረዋል፡፡ሽመልስ እሳት ለብሰውና ከአንድ የህግ ባለሞያ በማይጠበቅ መልኩ እየደጋገሙ‹‹እንትን››እያሉ በሰጡት መልስ ‹‹ተቃዋሚዎች የእኛ አዋጅ የአሜሪካንን ወይም የአውሮፓን ስለማይመስል ህግ ለመሰኘት ብቁ አይደለም ይላሉ››ብለዋል፡፡አዋጁ የሰብዓዊ መብትን ይጋፋል ሲባሉም አራምባ በመርገጥ ‹‹ ለሽብርተኞች በሩን በመዝጋቱ የእኛ ህግ ከሁሉም የተሻለ ነው››ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ያልሰማ ጆሮ የሚሰጠውን መልስ ለማወቅ የሽመልስንና የጌታቸውን ንግግሮች ማድመጥ አቻ የሚገኝለት አይመስለኝም፡፡ለነገሩ በዋናነት የኢህአዴግ ዋነኛ ችግር ምላስ እንጂ ጆሮ የሌለው መሆኑ አይደል፡፡ተቃዋሚዎቹ አዋጁን በተመለከተ ለሚያነሷቸው ውሃ የሚያነሱ መከራከሪያዎች ኢህአዴጋዊያኑ ከተነሳው ሃሳብ ጋር ተያያዥነት የሌለውን ምላሽ መስጠታቸው ሟቹን መለስን በብዙ ነገር እንዳስታውስ አድርጎኝ ነገሩ የወል ችግራቸው መሆኑን ደመደምኩ፡፡
በዚህ አይነት በፖለቲካ ውሳኔ እንዳንረሸን ሰጋሁ
ሽብርተኞችን የመፈረጅ ስልጣን ፓርላማው አልተሰጠውም የሚለው መከራከሪያ በአቶ ሽመልስ አስደንጋጭ መልስ ተሰጥቶታል፡፡ፓርላማው ህግ የማውጣት እንጂ ህግ የመተርጎም ስልጣን የፍርድ ቤቶች በመሆኑ የፍርድ ቤቶችን ስራ ለፍርድ ቤቶች መስጠት ሲገባው ያወጣውን ህግ ለመተርጎም መሄዱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ነው ሲባል ሽመልስ ‹‹ይህ የፖለቲካ ውሳኔ ነው››ብለው አረፉት፡፡በእኛ አገር የፖለቲካ ፣የውድብ፣የቡድን ውሳኔ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡በፓርላማው ካሉት 547 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 545 በመውሰድ ቤቱን ተቆጣጥሯል፡፡በዚህ የአንድ ፓርቲ ጉባዔ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላለፈ ማለት ምን አይነት ትርጉም እንደሚኖረው ለታዛቢ እንተወው፡፡ደግሞስ የማስረጃ፣የምስክርናየህግ ድንጋጌን የሚፈልግ ትልቅ ጉዳይ እንዴት ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲይዝ ይደረጋል?ከዚህ በላይ ፍትህን መስቀል ከወዴት ይገኛል?
አወያይ ጋዜጠኛ ወይስ ኳስ አቀባይ?
የኢቴቪው ጋዜጠኛ ስሙን ከኢህአዴግ ተወካዮች ተራ አለማስመዝገቡ ብስጭቴን እንዳናረው መሸሸግ አይኖርብኝም፡፡ከመነሻው ‹‹ኢትዮጵያን የሽብር ስጋት ያሰጋታል ወይስ አያሰጋትም››የሚል ጥያቄ አንስቶ በአገሪቱ የደረሱ ጥቃቶችን በፊልም ማሳየት ምን ሊባል ይችላል?ይህንን ፊልም የሚመለከቱ ሰዎች ከመነሻው የጥያቄው መነሳት አስፈላጊነት ላይታያቸው እንደሚችል መገመት ባይከብድም አወያዮ ፊልሙን ጋብዟል፡፡
ፓርላማው ድርጅቶችን መፈረጁን በተመለከተ ፓርቲዎቹ ሲወያዮ የጋዜጠኛ ማልያ ያጠለቀው አወያይ ጣልቃ ገብቶ ‹‹የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስታወስ ያህል ፓርላማው የፈረጀው አልቃይዳ፣አልሻባብ፣ኦነግ፣ኦብነግንና ግንቦት ሰባትን ነው››ብሏል፡፡እንኳን ይህችን ያለ ሰፈሯ የመጣችን ዝንብ ለምናውቅ ሰዎች የጋዜጠኛው ማስታወሻ ግልጽ ናት‹‹ተቃዋሚዎች የሚከራከሩት ለአልቃይዳ ነው››ለማለት ነው፡፡ክርክሩ ግን ፓርላማው ከስልጣኑ ውጪ እየተጓዘ በመሆኑ ነገ ሌሎች ሰላማዊ ፓርቲዎችን ሽብርተኛ በማለት ሊፈርጅ ይችላል የሚል ነበር፡፡አወያዮ ልክ የኢህአዴግ ተወካዮች አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ሲሰማውና የማርያም መንገድ ሲያጡ ዘው ብሎ በመግባት መውጫ መንገድ ያመቻቻል፡፡ኳሷ በተቃዋሚዎች እጅ በኢህአዴግ ሜዳ እየተንከባለለች ወደ ጎል ስትደርስ ጋዜጠኛው ፊሽካ ነፍቶ ኳሷ እንድትመለስ ያደርጋል፡፡
በእስካሁኑ ክርክር ለበቀለና ለሃብታሙ ኮፊያዬን አወልቃለሁ     
ክርክሩ ነገ ምሽት እንደሚለጥቅ ኢቴቪ ቃል ገብቷል፡፡የመጨረሻው ክርክር ቀርቦ ፋይሉ ከመዘጋቱ በፊት በግሌ ባደረግኩት ዳሰሳ የመጀመሪያው ምሽት የክርክር ኮከብ አቶ በቀለ ነግዓ የሁለተኛው ምሽት ፈርጥ ደግሞ ሃብታሙ አያሌው ነበር፡፡ሙሼ ረጋ ብሎ የሚያነሳቸው ነጥቦች ቦታ ሊሰጣቸው የሚገባቸው እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡
በቀለ ዘና እና ረጋ ብለው የሚወረውሯቸው ቃላቶች ድንጋይ ሆነው  በኢህአዴግ ላይ የሚያርፉ ቢሆኑ አቶ በረከት ስምኦን በሁለት ምርጫዎች ወግ እንደጠቀሰው ናዳ ሆነው ኢህአዴግን ከመንበሩ ባፈናቀሉት ነበር፡፡ ሃብታሙ ታሊባንን እንደ አገር በመውሰድና የጸረ ሽብርተኝነትን የምንቃወመው››በማለት ከመናገሩ ውጪ ነጥብ በነጥብ ያነሳቸው ሃሳቦች የሚጣል ነገር አልነበራቸውም፡፡ እንግዲህ ደግሞ ለነገው የነገ ሰው ይበለን፡፡

Ginbot7 Popular force fundraising Advertisemnt in Oslo Sep 28, 2013



Thursday, August 22, 2013

በኖርዌይ “የግንቦት 7 ሕዝባዊኃይል” ድጋፍ አሰባሳቢ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መግለጫ


ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም።በአሁኑ ወቅት አገሪቱና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል።
የትጥቅ ትግልም በኢትዮጵያ የወቅቱ የፖለቲካ ሁናቴ እንደ አንድ ምናልባትም እንደ ብቸኛ የትግል አማራጭ እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል።
“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የወያኔ ግፍና በደል በአንገፈገፋቸው በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና በተለያዩ ዜጎች የተመሰረተ ድርጅት ነው። የዚህ ኃይል ራዕይ ደግሞ ሕዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን፣የዜጎች መብቶች፣አገራዊ አንድነት፣ደህንነትንና ጥቅም እንዲከበሩና ጠንካራ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትገነባ መስዋዕትነትን በመክፈል አስተዋጾ ማድረግ ነው።
“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ወያኔን በኃይል ለማስወገድ ፣ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር ማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግስታዊ የመከላከያ፣ የፖሊስ፣የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዎ ማድረግን እንደ  አንድ ግብ ይዞ የተነሳ ኃይል ነው።
“በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ውስጥ የተመቻቸ ኑሮአቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እና የሚወዱትን አገርና የሰለጠኑበትን ሙያ እርግፍ አድርገው በመተው ትእግስትን የሚፈታተን መከራና እንግልት የሚበዛበትን የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ በርካታ ምሁራን ይገኙበታል። ይህም ከዚህ በፊት በስፋት የሚታወቀውን “ያልተማረውን ዜጋ ወደ ጦር ግንባር” የመላክና የመስክ ላይ ትግሉም በትምህርት ላይ የተመሰረተ አመራር የማጣት ችግርን የቀረፈ እና ታጋዩ ህብረተሰብ በዕውቀት ላይ በመመርኮዝ “ለምንና ለማን ነው የምታገለውና የምሰዋው” ጥያቄን በሚገባና በጥልቀት የተገነዘበ ኃይል ነው።
ይህንን ለኢትዮጵያና ሕዝቧ መልካም ራዕይ አንግቦ የተነሳ ሠራዊት በተቻለ ሁሉ መደገፍና ደጀንነታችንን ማረጋገጥ የውዴታ ግዴታችን መሆኑን የተገነዘብን በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን አንድ ግዜያዊ  የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረኃይል በማቋቋም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ጀምረናል።
በግብረኃይሉ መርሃግብር መሰረት መስከረም 28 ቀን 2013 (እ.ኤ.አ) “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” አመራር ተወካዮች በሚገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦስሎ ከተማ ተዘጋጅቷል።
በፕሮግራሙ ላይ ውይይት፣ የገቢ ማሰባሰቢያና የመዝናኛ መርሃግብሮች ተካተዋል። በመሆኑም ነፃነት ለኢትዮጵያ ሃገራችንና ለሕዝቧ ከዚያም በላይ ለእኔ ስብዕና ያስፈልገኛል ብለን የምናምን ሁሉ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ደጀንነታችንን “ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል”  እንድናሳይ ጥሪያችንን በትህትና እናቀርባለን።
ነፃነት፣ ፍትህ፣እኩልነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች !!!
በኖርዌይ “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል”  ድጋፍ አሰባሳቢ ግዜያዊ ኮሚቴ
ኦገስት 14፣ 2013 ኖርዌይ፣ ኦስሎ

33ቱ የተቃዋሚ ፓርቲ ስብስብ ሰማያዊ ፓርቲን አባረናል አሉ

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ለጋዜጦች የሰጧቸው አስተያየቶች “…ለሌሎች ፓርቲዎች ክብርና ዕውቅና የነፈገ ነው…” ሲሉ የሰላሣ ሦስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ቅሬታውን ገልጿል።
አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
በዚህም ምክንያት ፓርቲው ከተቃዋሚዎች ስብስብ እንዲሰናበት መወሰኑን ገልጿል።
“አቶ ይልቃል በበኩላቸው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃል የሰጠሁት አስተያየትና ያንፀባረቅኹት ሃሣብ አዲስ አይደለም፣ እውነትም ነው” ብለዋል።
ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡

ከገዢው ፓርቲ ጋር በቅርበት በመስራት በአሁኑ ሰዓት ገዢውን ፓርቲ እየታገለ የሚገኘውን ሃብታሙ አያሌው

by MINILIK SALSAWI » Today, 09:59



አቶ ሃብታሙ አያሌው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባልና ምክትል የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነው፡፡ወደ ፖለቲካው ዓለም የገባው በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት በማስተማር አገልግሎት ተጠምዶ ሳለ አንድ ችግር ይነሳና ቤተክርስቲያኑ በሚገኝበት ቀበሌ በአስተዳደሩ ይጠራል፡፡በቀበሌው የተገኘው ሃብታሙ የተፈጠረውን ችግር ያብራራበት መንገድ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን የሆኑ ግለሰብን ይማርካል፡፡ግለሰቡ ከስብሰባው በኋላ ሃብታሙን በመቅረብ በቅርቡ የሚመሰረት አንድ ነጻ የወጣት ማህበር ስላለ በዚያ የምስረታ በዓል ላይ እንዲገኝ ያግባባዋል፡፡መንፈሳዊው ሃብታሙም በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አጀንዳውን መንፈሳዊ ህይወት ባላደረገ ማህበር ምስረታ ላይ ይታደማል፣በዚያው ዕለትም ስሙ ተጠቁሞ ይመረጣል፡፡ዳዊት ሰለሞን ከገዢው ፓርቲ ጋር በቅርበት በመስራት በአሁኑ ሰዓት ገዢውን ፓርቲ እየታገለ የሚገኘውን ሃብታሙን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዩች አነጋግሮታል፡፡


ላይፍ --- አምላክን ከማገልገል ህይወት ወደ ፖለቲካ የመምጣት ውሳኔን ማሳለፍ ምን ያህል አስቸጋሪ ነበር ?

ሃብታሙ---ፖለቲካ እውቀት ብቻ ሳይሆን ስብዕናን ይፈልጋል፡፡ፖለቲካን ከሃይማኖት የሚለየው ምድራዊ መሆኑ ነው፡፡ሃይማኖት ለመንፈሳዊ በረከት የምትሰራበት ከሞት በኋላ ስላለ ህይወት በአብዛኛው የምትኖረው ነው፡፡ሃይማኖት የሚፈልገው ስብዕና ይህ ስብዕና ውሸትን መጠየፍ፣እውነትን መከተልና ለተበደለው መጮህን የሚይዝ ነው፡፡ፖለቲካውም ይህንን ይፈልጋል፡፡እርግጥ ነው ፖለቲካው ከስብዕና በተጨማሪ እውቀትን ይፈልጋል፡፡ነገር ግን ይህንን ክፍተት መሙላት ይቻላል፡፡በሃይማኖት ቤቶች ፖለቲካውን የአለማዊ ሰው መገለጫ በማድረግ የመመልከት አዝማሚያ አለ ይህ ግን መለወጥ መቻል አለበት፡፡ፈሪሃ እግዚአብሄር ያላቸው ሰዎች ወደ ፖለቲካው መምጣት እንደሚገባቸው አምናለሁ፡፡

ላይፍ -- ወደ ማህበሩ ከመጣህና በአመራርነት ከተመረጥክ በኋላ ምን ተፈጠረ ?

ሃብታሙ -- የአዲስ አበባ ፎረም ሲመሰረት የሄድኩት ከአንድ ጓደኞዬ ጋር ነበር፡፡አንድ የማላውቀው ሰው ስሜን ጠርቶ በአመራርነት እንድመረጥ ጠቆመኝ፡፡እኔ ግን ምንም ልምድ እንደሌለኝ በመግለጽ ጥቆማውን ለመቃውም ሞከርኩ፡፡መጀመሪያ የጠቆመኝን ሰው ከአመታት በኋላ አግኝቼው ካድሬዎች እኔን እንዲጠቁም ስላዘዙት እንደጠቆመኝ ነግሮኛል፡፡ጥቆማውን እንድቀበል በዚያ የነበሩ ሰዎች ግፊት ስላሳደሩብኝም ተመረጥኩ፡፡ከዚያም የማህበሩ የክፍለ ከተማው ምክትል ሰብሳቢ ሆኚ ተመረጥኩ ብዙም ሳይቆይ የአዲስ አበባ የፎረም ሰብሳቢ ተደረግኩ፡፡በመለጠቅም ዘጠኝ አደረጃጀቶች ማለትም የአዲስ አበባ ወጣት ፎረም፣የኢህአዴግ ሊግና ሌሎች ማህበራት የመሰረቱት ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት ሆኜ ተመረጥኩ፡፡ከመንግስት በደረሰኝ ደብዳቤም የሕዝብ ግኑኝነት ሆኜ እንድሰራ ተደረግኩ፡፡ነገር ግን በዚህ መንገድ ከሁለት አመት በላይ መቀጠል አልቻልኩም፡፡

ላይፍ -- ምንድን ነው በዚህ መንገድ እንዳትቀጥል ያደረገህ?

ሃብታሙ -- ፌደሬሽኑም ሆነ የወጣቶች ፎረም ሲመሰረት ኢህአዴግ በነጻነታቸው ዙሪያ ምንም ጥያቄ አላነሳም፡፡ነገር ግን ቀስ በቀስ ማህበራቱን በካድሬ ትዕዛዝ ለመምራት መንቀሳቀስ ተጀመረ፡፡በዚህ ላይ ማህበራቱ መቶ በመቶ በጀታቸውን የሚያኙት በመንግሰት መሆኑም በነጻነታቸው ዙሪያ ጥያቄ ያስነሳል፡፡የሲቪክ ማህበራት በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርጋቸው የህግ ድንጋጌ ቢኖርም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ ወጣ ያለ ነው፡፡እኔም ሆንኩ ሌሎች ወጣቶች አንዲህ መሆኑን በግልጽ ስንቃወም ቆይተናል፡፡በመጨረሻ ግን የነበረውን ነገር በውስጥ ትግል መለወጥ እንደማይቻል ስገነዘብ ለቅቄ ወጥቻለሁ፡፡

ላይፍ -- በፎረምና በፌደሬሽኑ ውስጥ የነበረህን ከፍተኛ ሃላፊነት ከለቀቅክ በኋላ ባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበርን መስርተሃል፡፡ማህበሩን ለመመስረት መነሻ የሆነ ምክንያት ምንድን ነው?

ሃብታሙ -- አንድ ነገር ማስታወስ እፈልጋለሁ በሃላፊነት በነበርኩባቸው ወቅቶች ዘወትር ይነሱ የነበሩ ክርክሮች ‹‹አንተ ከኢህአዴግ ጋር እየሰራህ እንዴት ማህበራት ነጻ መሆን አለባቸው ትላለህ? ይህንን የምትለው በኢህአዴግ ስለማታምን ነው ይሉኝ ነበር፡፡ሃሳቤን ለማስለወጥም ብዙዎች ሽምግልና እስከመቀመጥ ደርሰው ነበር፡፡ባለ ራዕይ ማህበርን ለመመስረት ያበቃን በኢትዩጵያ ውስጥ ለማንም ወገንተኛ ያልሆነ ሲቪክ ማህበር መኖር አለበት የሚል አቋም ያለን ወጣቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች መገናኘት በመቻላችን ነው፡፡

ላይፍ -- ከገዢው ፓርቲ በመለየትና ታገኘው የነበረን ጥቅማ ጥቅም በመተው ‹‹በቃኝ ››የሚል ውሳኔን መሳለፍ ከባድ ምርጫ አልነበረም ?

ሃብታሙ -- ኢህአዴግ ቤት እያለሁ ወፍራም ደሞዝ ነበረኝ ፣መኪና ተመድቦልኝ የተለያዩ አበሎች ይከፈሉኝ ነበር፡፡ስልጣን በራሱ የሚፈጥረው ወዳጅም አለ፡፡በሆድ ለሚያስብ ሰው እኔ ከነበርኩበት ሁኔታ መውጣት አስቸጋሪ ነው፡፡እኔ ግን ህሊናዬ ላልፈቀደው ነገር በሆዴ እየተደለልኩ መኖር የምችል ሰው ባለመሆኔ የምመራውን ህይወት በህሊና ለመለወጥ አልተቸገርኩም፡፡ በርካታ ዜጎች በችግር እየተቆራመዱ ለስደት ሲጋለጡ እያየሁ እኔን ተመችቶኛልና ስለ ሌላው ምንም አያገባኝም ለማለት አልደፈርኩም፡፡ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ምን እንደሚያስብም አውቃለሁ ነገር ግን ያንን ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎቹ ያዘጋጀውን ጽዋ መጠጣት ለእኔ ክብር እንደሆነ በማሰቤም በቃኝ ለማለት እንዳልቸገር አድርጎኛል፡፡
Image
ላይፍ -- ወደ ተቃዋሚው ጎራ ስትመጣ በዚያ ያሉ ሰዎች ከኢህአዴግ ጋር የነበረኝን ቆይታ ስለሚያውቁ ሊያምኑኝ አይችሉም የሚል ስጋት አላደረብህም ?

ሃብታሙ -- በእርግጥ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚገኝበት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ነገሮች አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ከገዢው ፓርቲም ሆነ ከተቃዋሚነት ወደ ኢህአዴግነት ለሚሄዱ ሰዎች ሁኔታዎች ቀላል አይሆኑም፡፡በሁሉም ወገን በጥርጣሬ የመታየት ዕድል ሰፊ ነው፡፡በእኛ አገር የአንድ ፓርቲ አባል ከሆንክ እስከ ዕለተ ሞትህ የዛ ፓርቲ ወይም አስተሳሰብ አካል እንደሆንክ እንደምትቀጥል ይጠበቃል፡፡ለምሳሌ ኢህአዴግ ቤት ሃሳብ በመሸጥ መቀጠል አይቻልም፡፡በኢህአዴግ ውስጥ ኢህአዴግን በሃሳብ መታገል አይቻልም፡፡ፖለቲካውን የሚመራው በዕዝ ነው እንጂ በሃሳብ የበላይነት አይደለም፡፡በእንዲህ አይነት በዕዝ ሰንሰለት በሚመራ ድርጅት ውስጥ መቆየት ደግሞ የማይታሰብ በመሆኑ የተቃውሞውን ጎራ ለመቀላቀል አብቅቶኛል፡

ላይፍ -- ኢህአዴግ ቤት በነበርክባቸው ወቅቶች ያፈራሃቸው ጓደኞች አሁን የቀድሞውን መስመር ስትቃወም ሲመለከቱ ምን ይሉሃል?



ሃብታሙ -- እኔ ወደ ህዝብ የምሄደው እኔን ብቻ አድምጠኝ ለማለት አይደለም፡፡በግሌ በፊትም ይሁን በቀጣይ የሚኖሩኝ ወይም የነበሩኝ ጓደኞች አቋም እንዳለው ሰው እንዲያስቡኝ እፈልጋለሁ፡፡እስካሁንም ያለው ነገር ይህ ነው፡፡ኢህአዴግን የተውኩትና አንድነትን የተቀላቀልኩትም የአቋም ልዩነት ነው፡፡በአንድነት ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎችን በማግኘቴ ለውጥ እናመጣለን የሚል እምነት በመሰነቄ እየታገል እገኛለሁ፡፡

ላይፍ -- ተቃዋሚዎችን በመቀላቀልህና ኢህአዴግን በመታገልህ የደረሰብህ ችግር የለም?

ሃብታሙ -- እውነቱን ለመናገር ችግር የለም ማለት አይቻልም፡፡ችግር ብቻ ሳይሆን የተከተልኩት መስመር የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር የሚጠይቅ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ገዢው ፓርቲ የምበላውን አጥቼ እንድንበረከክ በመፈለግ ያሸነፍኳቸውን ጨረታዎች እንኳን እንዳላገኝና በዜግነቴ ሰርቼ እንዳልኖር እያደረገ ይገኛል፡፡ይህንን የሚያደርገው ግን ኢትዩጵያዊያንን ካለማወቅ በመሆኑ አልገረምም፡፡ኢትዩጵያዊ ክብሩን የሚጠብቅና ለፍርፋሬ ሲል ማተቡን የማይበጥስ ነው፡፡

ላይፍ -- ወደ ፓርቲው ህዝባዊ ንቅናቄ እንምጣ ፣አንድነት እያደረገው የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ ሌላ ፓርቲ በቅርቡ ማድረጉን ተከትሎ በኩረጃ መልክ እየተደረገ የሚገኝ ነው ወይስ በጥናት ነው?

ሃብታሙ --- ማንንም አልኮረጅንም ፣እያደረግነው የምንገኘው እንቅስቃሴ በስትራቴጂክ መጽሀፋችን ቀደም ብሎ የሰፈረ ነው፡፡ስለዚህ እየሰራን የምንገኘው በእቅዳችን መሰረት ነው፡፡ዞሮ ዞሮ ማንም አደረገው ማን የተደረገው ነገር የአገሪቱን ፖለቲካ አንድ እርምጃ ከገፋው ጥቅሙ የሁላችን በመሆኑ ጀማሪው እከሌ ነው አይደለም የሚለው ነገር አስጨናቂ አይሆንም፡፡አንድነት በዚህች አገር ለውጥ እንዲመጣ ያቅማቸውን ላበረከቱና እያበረከቱ ለሚገኙ ሁሉ እውቅና ይሰጣል፡፡በደፈናው ባለፉት አርባ አመታት ምንም አስተዋእጾ አልተበረከተም የሚል ድምዳሜ ላይ ፓርቲያችን አይደርስም፡፡እነ ፕሮፌሰር አስራትን ጨምሮ በዙ ሺህዎች ለዚህች አገር የህይወት መስዋዕትነትን ከፍለዋል፡፡ለዚህ እውቅና መቸር ይገባናል፡፡እውንት ለመናገር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የህዝብን አይን የገፈፉት በታዲዩስ ታንቱ የሚመራው የአገር ወዳድ ኢትዩጵያዊያን ማህበር ነው፡፡ለግራዚያኒ ሃውልት እንዲቆምለት መወሰኑን በመቃወም ሰልፍ እንዲጠራ ያነሳሱት እን ታዲዩስ ናቸው፡፡ለዚህ ተገቢውን አክብሮት ሊቸራቸው የሚገባ ቢሆንም ሌሎች መድረኩን በመቆጣጠር የማይገባቸውን ውዳሴ ለመሸመት ተንቀሳቅሰውበታል፡፡በሃይል በተቀለበሰው ሰላማዊ ሰልፍ ከአርባ በላይ አባላቶቹ የታሰሩበት ባለ ራዕይ ማህበርም ከሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጆች አንዱ ነበር፡

ላይፍ -- መስከረም አምስት አንድነት በአዲስ አበባ ለማድረግ ያቀደውን ሰልፍ የአንድ ፓርቲ ሊቀመንበር‹‹አንድነት ይህንን ሰልፍ የጠራው እነ አንዷለም የታሰሩበትን ቀን ለማክበር ነው፣እኛ ግን ሰልፍ የምንወጣው እነ አንዷለም እንዲፈቱ ነው ››ብለዋል፡፡እስኪ የሰልፉን አላማ ንገረኝ?

ሃብታሙ -- (ረዥም ሳቅ)ፖለቲካ እንግዲህ እንደተርጓሚው ነው፡፡ይህ አስተሳሰብ ተገቢ ባይሆንም አስተሳሰቡ ግን የመደመጥ ዕድል ማግኘት እንደሚገባው ይሰማኛል፡፡ግለሰቡ እንዲህ የሚያስቡ ከሆነ ማድረግ የሚጠበቅብን አስተሳሰባቸውን እንዲያሳድጉ መርዳት ነው፡፡ለኢትዩጵያ ፖለቲካ የሚጠቅም አስተሳሰብ ባለመሆኑም የራስን ገጽታ ለመገንባት የሌሎችን መልክ ማቆሸሽ ቅንነት የጎደለው ድርጊት ነው፡፡በግሌ ይህንን የተናገሩት አቶይልቃል አንድ ሰልፍ በመጥራት ስማቸው በየቦታው መነሳት በመጀመሩ ስካር ውስጥ የገቡ ይመስለኛል፡፡ኢትዩጵያ ውስጥ ፓርቲ አለ ብዬ አላምንም ማለትና በመድረክና በአንድነት ውስጥ ለጊዜው ተፈጠረ የተባለውን ልዮነት በማራገብ እየተባሉ ነው ማለት እንዴት አይነት ፖለቲካ እንደሆነ አይገባኝም፡፡እዚህ አገር ፓርቲ የለም ብሎ የሚያምን ፓርቲ በምን ስሌት ከሰላሳ ሶስት ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት መፈራረሙ አስገራሚ ነው፡፡የሉም ካሉ እንዴት አብረው ሊሰሩ ፈረሙ፡፡ኢህአዴግም እኮ የሚለው ይህንኑ ነው አኔ ከሌለው ይህች አገር ትጠፋለች የሚለው ፓርቲዎች አሉ በማለት ስለማያምን ነው፡፡ይህንን ጥያቄ ስላነሳህው ልመልሰው እንጂ ዝሆን የሚያባርር ለወፍ ድንጋይ አይወረውርም፡፡እኛን እንቅልፍ የሚነሳን የአገራችን ጉዳይ ነው፡፡እንዴት ይህንን አምባገነን ስርዓት እንለውጣለን የሚለው ያስጨንቀናል እንጂ የቃላት እሰጥ ገባ ውስጥ በመግባት ጊዜ ማባከን አንፈልግም፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ፍርዱን እንደሚሰጥ በግሌ አምናለሁ፡፡

ላይፍ --ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተሯሯጡ ነው፡፡እነዚህ የፖለቲካ ሃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው ካልተቆጠቡ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ዝተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስም ባይጠሩም ይህ ማስጠንቀቂያ በዋናነት አንድነትን የሚመለከት አይመስልህም?

ሃብታሙ --ኢህአዴግ ሲጨነቅ የሚናገራቸው ነገሮች ፍጹም የማይገናኙ ናቸው፡፡አቶ ሃይለማርያም በምንና እንዴት መታገል እንደሚገባን ሊያዙን ወይም የምንታገልባቸውን ነገሮች እየቆነጠሩ ሊሰጡን አይችሉም፡፡እኛንና እሳቸውን የሚዳኘን የአገሪቱ ህግ ነው፡፡ስልጣን ስለያዙ ለህገ መንግስቱ ቅርብ ናቸው አያስብልም፡፡እኛም የህገ መንግስት ጥሰት እየተፈጸመ ነው በማለት እየከሰስን ነው፡፡ነጻ የፍትህ ስርዓት ቢኖር ማን ህጉን እንደጣሰም በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ለማንኛውም ግን ሙስሊም ወገኖቻችን ያነሱት ጥያቄ የሃይል ሳይሆን ስልጡን ምላሽ እንዲሰጠው ከመጠየቅ ወደ ኋላ አንልም፡፡በማስፈራሪያው በመሸማቀቅ ለወገኖቻችን አጋርነታችንን ከማሳየት እንደማንቦዝንም መታወቅ አለበት፡፡

Wednesday, August 21, 2013

ወ/ት ሐዲያ ሙሀመድ ከሳምንታት የእስር ቤት ስቃይ በሁዋላ ተፈታች

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራር የሆነቸው ወ/ት አዲያ አህመድ ከሀምሌ 22 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ  ስቃይ እስር ቤት ውስጥ ከደረሰባት በሁዋላ በዛሬው እለት በዋስ ተፈታለች።
ወ/ት ሐዲያ እንዳለችው መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ያዋሉዋት አንድነት ፓርቲ ሀምሌ 28 በሶዶ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በተመለከተ የቅስቀሳ ወረቀቶችን መበተኑዋን ተከትሎ ነው።
ፖሊሶቹ በሀድያ ጉዳይ አንድነትን ከድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ ለመወንጀል ቢፈልጉም፣ ሀድያ ባሳየችው ያቋም ጽናት ሳይሳካለቸው ቀርቷል።
መርማሪ ፖሊሶች ” ገልብጠን እንገርፍሻለን፣ አንገትንሽን ጠምዝዘን ገደል እንወረውረዋለን፣ ቀደም ሲል የታሰሩ እስረኞች እንዳወቁበት እወቂ” የሚሉና ሌሎችንም የማስፈራሪያ ቃላት በመጠቀም እነሱ አዘጋጅተው ባመጡት ወረቀት ላይ እንድትፈርም ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሀድያ ለማስፈራሪያው ልትንበረከክ አለመቻሉን ተናግራለች ( )
በታሰረችበት እስር ቤት መጸዳጃ ቤቱ ሞልቶ በምኝታቸው ላይ ይፈስ እንደነበር የምትለው ሐድያ፣ የወላይታ እስር ቤት የምድር ሲኦል ነው በማለት በእስር ቤቱ ውስጥ ያየችውን በዝርዝር ለኢሳት ተናግራለች። ከወ/ት ሀድያ ሙሀመድ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ ሰሞኑን እናቀርባለን ።
በዚህ አጋጣሚ ወ/ት ሀድያ ወደ ፍርድ ቤት ስትሄድ በመቆያነት ታስራበት የነበረውን ጊዜያዊ እስር ቤት ከፊል ገጽታ በፎቶ በማንሳት ላካፈለን የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ ከፍተኛ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

Tuesday, August 20, 2013

[Must Watch] "Funny" Ethiopian Priest Speaks at The Memorial Service Of Late PM Meles Zenawi

 ቄሶ ክበበው ገዳ የባለ ራእዩ  የ3 billion  ዶላር የሙስና  ባላአባት የሆነውን መለስ ዜናዊ  የሙት አመት ቀን መታሰቢያ በማድረግ  የተዘጋጀለትን የአየር ሰአት  በመጠቀም ታዳሚዎቹን በሳቅ ሲያስፈለቀልቃቸው በመመልከት እርማችሁን አውጡ ቀላጁ  ለሚያቃጥለው ሰው  ማለቴ ነው የ ETV ባለስልጣን ዘመድ  ነው መሰለኝ የአቶ መለስን ዝናን ደጋግመው እንደሚያዳምጡም በቀልዳቸው ላይ ጠቀስ አድርጎታል ሰው ዩው  ለማንኛውም  ምስሉን ይመልከቱት 

ውይ ውይ ውይ ውይ ጉድ ጉድ  እንደዚህ አይነት ቄስ አለ እንዴ በምድረ ኢትዮጵያ ውስጥ  ከአምላካችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር እኩል  አድርጎ እውነት አቶ መለስ ነው ብሎ  አረመኔውን መለሰ ዜናዊን ሲክበው ብትሰሙት ሃይማኖታችሁን ለመቀየር  ትወስናላችሁ ብዩ እገምታለሁ እኔ እንደሚገባይኝ ከሆነ በቄስ ስም የገባ አግአዚ መሆን አለበት እንጂ እውነት እንደዚህ  አይነት የዳቢሎስ መልእክተኛ ቄስ  ቤተ ክህነቷን መቀለጃ አያደርጋትም ነበር ።

ለማንኛውም እስቲ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀልደኛውን ቄስ ተብዬ ሰላይ ቀልዱን ስሙትና የምትሉትን በሉት አሳፋሪ ለሆዱ ያደረ  ወራዳ አጭበርባሪ በቄስ ስም የገባ 666 መሆኑን ካነጋገሩ ቄስ ክበበው ገዳ መሆኑን ታውቁበታላችሁ። 

 እውነት ነው TPLF is  devil  የተባለውለ ካስ በዋልድባ ገዳም እንዲሁም በሌሎች ቤት ክሪስቲያን  እየተላኩ  እውነተኛ አባቶችን በመሰለል የፖለቲካ ስራቸውን በመስራት መንፈሳዊ አባቶችን  ቁም ስቅል እያሳዩአቸው ያሉት እንደነዚህ አይነት የዘመኑ ጉግ ማን ጉጎች ናቸው እውነት አምላክ በእንደነዚህ የሐይማኖት ጠላቶች  ላይ በቅርቡ የሆነ ተአምር ካላሳየን በስተቀር  ሐገራችን ኢትዮጵያ በምን አይነት አዚምና ምትሓት ተወታትባ እንዳለች ማወቅ አያዳግትም ስለዚህ እውነት  ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው ብሎ ለሚያምን የክርስቶስ ቤተሰብ ለሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንደነዚህ አይነት ተኩላዎች ከቤተ ክሪስቲያናችን አምላክ መንቅሎ እንዲያሶጣልን ጠንክሮ ወደ አምላኩ መጮህ ይገባዋል ያለበለዚያ ችላ ብሎ ካለፈው   እራሱንን መመርመር  ያስፈልገዋል  ብዬ ምክር እሰጠዋለሁ።

  ሐይማኖታችን  ምን ያህል አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ እንዳለች  የሚያሳይ ዜና ስለሆነ  በጣም ደንግጪ ነው የጻፍኩት የመጻፍም ልምድ ኖሮኝ አይደለም የቃላት ግድፈት ካለው እያረማችሁት አንብቡት  

አምላክ ያቺን የሐገር መሪ የሐይማኖት መሪ ያጣችውን ሐገራችንን በቸርነትቶ ይጠብቃት  
   አሜን  አሜን አሜን 
   


 እስክንድር  አሰፋ 
     ከኖርዌ
ነሐሴ 15. 2005 ዓም 

Friday, August 16, 2013

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ



በዛሬው እለት Aug 16.2013   በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በኖርዌይ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት  የኢትዮጵያ ስደተኛ ማህበር በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበረሰብ የተገኙ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ  ከየድርጅቶቻቸው ተወክለው የተገኞት ተወካዮቻቸውም  ንግግር አድርገዋል ። 

የሰላማዊው ሰልፎ ዋና አላማ  ሃገራችንን ኢትዮጵያ ለሐሃያ ሁለት አመታት በዘረኛውና ከፋፋዮ ወያኔ ገዢ መንግስት ያደረሰባትን የዘር ማጥፋት፣ ከትውልድ ቄያቸው በግዳጅ ማፈናቀል ፣የሐይማኖት ነጻነት አለመኖር  ህዝቦቿም ወደ ማይወጡት ችግር ውስጥ በማስገባት ለስደትና ለመከራ በመዳረግ ከዛም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋና ግድያ እንዴሁም በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የሚያደርሰውን እስር፤ ድብደባ ፤ እንግልት በመቃወምና  የኖርዌ መንግስት ከአምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ጋር የምታደርገውን  ግኑኝነትና የምትሰጠውን እርዳታ እንድትመረምር  የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር።

በፕሮግራሞ ላይም ከኖርዌይ ፖለቲከኞች የተለያዩ ፓርቲዎች ተጋበዥ ሲሆን ሓገራቸው በአሁን ሰአት የምርጫ ጊዜ ስለሆነ ጥቂቶቹ ሊገኙ ስላልቻሉ በቴሎፎን ድጋፋቸውን ገልጸዋል  ከመሐከላቸውም  ከቬንስትረ ፓርቲ ወኪላቸውን በመላክ በኢትዮጵያ መንግስት ያላቸውን ተቃውሞና ለሰላማዊ ሰልፈኛው ድጋፋቸውን  በላኩት መልእክተኛ አስነብበዋል በመጨረሻም ከዲቬሎፕመት ፈንድ ተወካይ የመጣው ባለስልጣን አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላ መልእክታችንን ተቀብለዋል። 

በመዝጊያውም  የተለያዩ መፈክሮች ከተሰሙ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ እንደ ሐገራችን  መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኛውን በድብደባና የገባበት ገብቶ ለመያዝ በማሳዳድ  ሳይሆን በዲሞክራሲ መብታችን የፈለግነውን ተናግረንና ተቃውመን በሰላም ተጠናቋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይም ከተሰሙት መፈክሮች በጥቂቱ,TPLF is evil, There is apartheid in Ethiopia, Don't remove indigenous people from their livelihood, We need freedom of religion., Regime change is needed in Ethiopia now, We need freedom of speech, ድምጻችን ይሰማ እኛ ሙስሊም ክሪስቲያን ኢትዮጵያኑች አንድ ነን አንለያይም , ሞት ለወያኔ  በሚሉ መፈክሮች ያሸበረቀና ሌሎችንም መፈክሮች ያካተተ ነበር። ሰላማዊ ሰልፉም በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ kl 13; 00 ተጀምሮ በ 14፡30 ተጠናቋል  ቸር ያሰማን


ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር

እስክንድር አሰፋ

ከኖርዌይ
16.08.2013

Thursday, August 15, 2013

ነግ በኔ አለማለት በወረፋ ለመጠቃት መዘጋጀት ነው!

የወያኔ ጉጅሌ የህዝባችንን መሰረታዊ መብቶች ነጥቆና ረግጦ ለመግዛት ከወሰነ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ህዝቡ ብሶቱ እየገነፈለ አደባባይ መውጣቱ አርበትብቶታል። ወያኔ የህዝብን ጥያቄና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የህዝብን ደም በግፍ የሚያፈሰውም ከዚህ መርበትበትና ብረገጋው ጋር በተያያዘ ነው።

ከአላንዳች ህዘባዊ መሰረት በጠመንጃ እና በፖሊስ ሃይል ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ቁም ስቅላችንን የሚያሳየን ወያኔ ከህዝብ የበለጠ ሃይል ኖሮት አይደለም። የወያኔ ጉልበትና ግፍ የፀናብን ተከፋፍለን በየተራ ለመቀጥቀጥ ስለፈቀድንለት ብቻ ነው። ወያኔን ያጎለበተው በአንዱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ መዐት ሲወርድ ሌሎቻችን ወረፋችን እስኪደርስ ቆመን በመመልከታችን ነው ። ባለፈው ሳምንት የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የ ክቡር በዓላቸውን በሚያከብሩበት ቅዱስ ቀን በደም ያጠመቃቸው ክርስቲያኑና ሌላው ተመልካች ይሆናል ብሎ ስላመነ ነው። የኦሮሞው ጥቃት ለአማራው ምንም እንዳልሆነ፣ የአማራው ጥቃት ለኦሮሞው፣ ለደቡቡና ለትግሬው ምኑም እንዳልሆነ፣ የደቡቡ ጥቃት ሌሎችን የማያገባና የማይመለከት ነዉ ብለን ስለምናምን ለወያኔ ጥቃት ተመችተነዋል። በአጠቃላይ “ነግ በኔ” ማለት ትተናል። በወረፋ ለማጥቃት ወያኔ አመቻችቶናል። እኛም ተመቻችተናል። የኢድ አልፈጥር እለት እናቶችን፣ ሽማግሌዎችንና ህጻነትን ሳይመርጥ እንደእባብ በዱላ ሲቀጠቅጥ የዋለው የወያኔ ልዩ ሃይል የተማመነው “ነገ በኔ” የሚል ህዝብ ይኖራል ብሎ አለማሰቡና፣ የመከፋፈያ ሴራዪ ሰርቶልኛል ብሎ በማመኑ ነው። ነገሩ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነው። ሁላችንንም ባይንቀን ኖሮ ጥቂቶቻችንን አይደፍረንም ነበር።
ዛሬ የወያኔ ጥቃት ሰለባ ያልሆነ፣ በወረፋው ያልተመታ፣ ያልተገደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልተሰደደ፣ ከመኖሪያው ያልተፈናቀለ፣ ከስራው ያልተባረረ የህብረተሰብ ክፍል የለም። ሰራተኛ፣ ምሁራን፣ ገበሬዎች፣ የብሄር ብሄረሰብ ስብስብ፣ ተማሪ፣ መመህር ወዘተ የጥቃት ወረፋ ያልደረሰው የለም።
ጥያቄው ለምን በወረፋ እንደበደባለን? እስከመቼስ ነው ወያኔ የአንዳንዶቻችንን ጥየቄ የሌሎቻችን ማስፈራሪያ እንዲያደርገውና የጥቃት እርምጃውን በየተራ እንዲያፈራረቅብን የምንፈቅድለት? የሚለው ነው ።
ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ ወያኔ በሙስሊሙ ወገኖቻችን ላይ የከፈተው የጥቃት ዘመቻ በጋራ መመከት ካልተቻለ ነገ በክርስቲያኑ ወይም በሌላው እምነት ተከታይ ላይ ላለመደገሙ ማረጋገጫ የለም ብሎ ያምናል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ከቀን ወደቀን ለነጻነቱና ለማንነቱ ሲል የሚያደርገው ትግልና እንቅስቃሴ እንቅልፍ የነሳቸው እና የእግር ዉስጥ እሳት የሆነባቸው ህወሃቶች፤ የሀገራችንን አንድነት ህልውና እና ማንነት ለማጥፋት፣ ዜጎች ስለመብታቸው እንዳይጠይቁ እየነጣጠሉ እና እየከፋፈሉ በደም የተጨማለቀ እጃቸውን እንደገና በደም እያለቀለቁ ስለሃይማኖታቸው ነጻነት፣ ስለፍትህ እጦት፣ ስለዲሞክራሲ መስፈን በጮኹ አንደበቶች፤ አንደበታቸውን በጥይት ሲዘጉ ማየት በወያኔ ጎራ በእነ ኢቲቪ መንደር የእነ አስረሽ ምችው ድለቃ የተለመደ ነው። ስለዚህ የማንኛውም ዜጋ የእኩልነት፣ የፍትህ፣ የነጻነት ጥያቄ ምላሹ ሞትና መታሰር ከሆነ እስከ መቼ ተራ እንጠብቃለን?
ተቻችለንና ተከባብረን የኖርን ኢትዮጵያውያን ለወያኔ ከፋፍለህ ግዛ እና አጥቃ ፖሊሲ መመቸት የለብንም። በደስታና በሀዘን ሳንለያይ የዘለቀውን አንድነታችን አሁን በዚህ አስከፊና ጨካኝ ወያኔያዊ ድርጊት አዝነን ከንፈራችንን ለሞቱት እና ለታሰሩት በመምጠጥ አይደለም ቁጭታችንና ሀዘናችን መግለጽ ያለብን። ለተጠቁ ወገኖቻችን መከታ ጋሻ ሆነናቸው ቁስላቸው ቁስላችን፣ ደማቸው ደማችን፣ ሀዘናቸው ሀዘናችን፣ ሆኖ ነገ በኔ በሚል ዛሬ ሁሉንም የትግል ስልቶች ተጠቅመን አለንላችሁ በሚል አንድ ላይ ሆነን ስንታገል ብቻ ነው።ቋንቋና ሃይማኖት ቢለያየንም በወያኔ ግፍ ግን ሁላችንም አንድ መሆናችንን ለአፍታ እንኳን መዘንጋት በወረፋ ለመቀጥቀጥ መዘጋጀት ነውና በወያኔ ላይ በአንድነት እንነሳ!!
ግንቦት 7 ንቅናቄ የሀገራችን ህልውናን ለማዳን፣ የሁሉም ዜጋ የእምነት ነጻነት፣ እኩልነት፣ የሰው ልጆች መሰረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ዛሬም በቆራጥ ልጆቹ መሰዋእትነት የወያኔን ዘረኛ አክራሪነት ለመታገል ቃል ኪዳኑን ያድሳል። መላው የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡ የነጻነት ጥያቄ ድምፃችሁ፣ ድምጻችን ነው። የጥቃት ወላፈኑ አቃጥሎ ሳይጨርሰን፣ ዳር ሆነን ላንመለከት ወያኔን በማናቸውም መንገድ ታግለን ልንጥለው፣ ልናስወግደው ትግሉን ጀምረናል፡፡ ያለውን ሰቆቃ በማስቆም በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ ኢትዮጵያችን የሁሉም እምነት ተከታዮች ተከባብረውና ተፋቅረው በነጻነት የሚኖሩበት አገር ትሆን ዘንድ እንታገል:: ኑ ተቀላቀሉን! ዳር ሆኖ መመልከቱ ይብቃ! በቃ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Wednesday, August 14, 2013

Press release: Ginbot 7 Popular Force fundraising task-force in Norway

 August 14, 2013
Ethiopia and its citizens have never been endangered and humiliated as under the rule of the woyane junta. The current problem of the country and its people is not only a question of lack of basic human rights, but it is a matter of life and death to the people and existence of Ethiopia as a sovereign country.
Ginbot 7 Popular Force fundraising
To fight the enemy which is responsible for the aforementioned situation and avert the danger, Ethiopians are wedging armed struggle and this is increasingly becoming the only and appropriate alternative.
Hence, Ginbot 7 Popular Force (G7PF) is established by freedom-loving Ethiopians, comprising youngsters, intellectuals and others. The main objectives of this force, as described on its website, are contributing to make the Ethiopian people owner of political power and establishing strong, sovereign and democratic Ethiopia. G7PF is working to remove TPLF by force and to create a peaceful transition period enabling establishment of non-partisan and constitutional defense, police, security, judiciary, etc. institutions which are crucial for a healthy playground for different political parties aspiring power in the country.
Among the current G7PF members are many intellectuals who joined this force abandoning their relatively comfortable living, families and professional jobs. This is one of the advantages of the G7PF compared to traditional armed struggles in Ethiopia where mainly farmers and other non-intellectuals are the main components of foot soldiers. Thus, the struggle of Ginbot 7 Popular Force gets skillful leadership on the ground and its members at the front properly understand why and whom they are fighting for and paying sacrifices.
Appreciating the efforts and the good intentions of G7PF, we Ethiopians in Norway have decided to support the force and established ad hoc committee (taskforce) mandated to coordinate a one-time fundraising in Oslo. As from the date of its establishment the taskforce is working on various activities and scheduled 28th of September, 2013 the date for the grand fundraising event in Oslo.
During this event, on 28 of Sep., 2013, representatives of the G7PF leadership will be present and the program of the event comprises, discussions, fundraising and entertaining activities.
Therefore, the taskforce herewith kindly invite all Ethiopians and other nationals both from Norway and neighboring countries to take part in this event and support G7PF.

http://www.youtube.com/watch?v=5-2nx34uGW0


Tuesday, August 13, 2013

ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ክ5500 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ኤርትራ ተሰደዋል::


ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ክ5500 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ኤርትራ ተሰደዋል::

ከ5500 በላይ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸን እና ቤተሰቦቻቸውን አስከትለው ድንበር አቋርጠው ወደ ጎረቤት ኤርትራ መግባታቸውን አስመራ የሚገኙ ምንጮች ለDurame በስልክ አስታውቀዋል:: 

በአማካኝ በየቀኑ 180 የሚሆኑ እድሜያቸው ከ30 አመት በታች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ኤርትራ ይገባሉ:: እንደምንጮቹ ዘገባ ከሆነ አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሚመጡት ከምእራብ እና ደቡብ ትግራይ ሲሆን እንዲሁም ከጎንደር ናቸው::

በመቀሌ የኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረው የ23 አመቱ ግርማይ ሃብቴ እንዳለው የወያኔ መንግስት ህዝቡን እየጨቆነ እንደሆነ እና ልንታገልው ይገባል ሲል ተናግሯል:: ሁሉም ነገር አለኝ.....በኢትዮጵያ ግን ተስፋዬ የጨለመ ነው:: ኢትዮጵያ ትልቅ እስር ቤት ሆናብኝ ነበር ብሏል::በየአመቱ ወደ 350.00ኦ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሃገሪቷን ለቀው ይሰደዳሉ :: በአፍሪካ ከፍተኛ የስደተኞች ላኪ አገር ኢትዮጵያ ሆናለች::

 source Minilik Salsawi

Monday, August 12, 2013

የሚሊዮኖች ለነጻነት ግብረ ኃይል በዳያስፖራ አስተባባሪ ኮሚቴ በሰሜን አሜሪካ

አገርን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች የሚወስኗቸው ዉሳኔዎች፣  አገርን በማልማትም ሆነ በማጥፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። ብዙዎች በአፋቸው «ፖለቲካን አንፈልግም። ፖለቲካ ውስጥ የለንበትም» ቢሉም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን፣ የፖለቲካዉ አካል ናቸው። ፖለቲካዉ የማይነካዉ ማንም ዜጋ የለም። የፖለቲካ ስልጣን የያዙ በሙስና ከተጨማለቁ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ሊያገኝ የሚገባዉን አገልግሎት በሚገባ አያገኝም። ፖለቲካዉ ዜጎችን  በዘር ከፋፍሎ ፣ «የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ነህ» በሚል የሥራ እድል የሚነፍገው፣ እንዲፈናቀልና እንዲባረር የሚደረገዉ «ፖለቲከኛ» ያልሆነው ዜጋ ነዉ። የፖለቲካ ዉሳኔ ያመጣዉ የኑሮ ወድነት ቀንበር እየከበደው ያለ፣ «ፖለቲከኛ» ያልሆነዉ ዜጋ ነዉ።
ለሃያ አመታት፣  ብዙዎቻችን፣  ፖለቲካ ወለዶቹ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣን፣ የኑሮ ዉድነትን፣ የዘር መከፋፈልን ፣ በመንግስት ባለስልጣናት የሚደርሱትን እንግለትና ወከባን ስናማርር ቆይተናል።  ነገር ግን ለችግሩ መፍትሄ ማምጣቱ ላይ ብዙ ሳናተኩር፣ ባይመቸንም ያለዉን ሁኔታ አሜን ብለን መኖሩን መርጠናል። ነገር ግን ይሄ መቀየር ይኖርበታል። የፖለቲክዉ ችግር የሚፈታዉ በፖለቲካ ትግል ነዉ። ወደድንም ጠላንም፣  ፖለቲካዉ በእያንዳንዳችን ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ካልቀረ፣ ፖለቲካዉ ህዝብን የሚጎዳ ሳይሆን ህዝብን የሚጠቅም እንዲሆን ማቅናቱ፣ ብቸኛ የተሻለ አማራጭ ነዉ። ፖለቲካዉ እንዲቀየርም የሰለጠነ፣ ሁሉንም የሚያሰባስብ፣ በጥላቻ ላይ ያልተመስረተ፣ ከዚህ በፊት ከተሰሩ ስህተቶች የተማረ፣  የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካን ማራመድ ያስፈልጋል። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል፣ የአንድነት ፓርቲ ላለፉት በርካታ ሳምንታት ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች ተመልክተናል። ገዢው ፓርቲ እንቅስቃሴዉን የነፍጠኞች ወይንም የሙስሊም አክራሪዎች እንቅስቃሴ እንደሆነ አደርጎ ለማጥላላት እየሞከረ ነዉ። በደሴ በርካታ ሙስሊሞች እንደመኖራቸው ፣ እንደ ኢትዮጵያዉያን ከሌሎች አምነት ተከታዮች ጋር ሙስሊሞች የአንድነትን ጥሪ ተቀብለው የነጻነት ድምጽ አሰምተዋል። በጂንካና በአርባ ምንጭ ብዛት ያላቸው ፕሮቴስታንቶች፣ በባህር ዳርና ጎንደር ብዛት ያላቸው ኦሮቶዶክሶች፣  ከሌሎች እምነቶች ጋር በመሆን ተመሳሳይ ድምጽ አሰምተዋል። የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ፣  ኦሮቶዶኮሱን፣ ፕሮቴስታንቱን፣ ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩን እንዲሁም ሌሎች እምነቶች የሚከተሉትን ኢትዮጵያውያኖችን ሁሉ ያቀፈ ነዉ። «አንድነት የነፍጠኞች ቡድን ነው» የሚል ያረጀበት ፕሮፖጋንዳ አገዛዙ ቢረጭም፣ አንድነት በጂንካ፣ በመቀሌ (ሰልፉ በመጨረሻ ሰዓት እንዲራዘም ቢደረግም) ፣ በአርባ ምንጭ በወላይታ፣ በደሴ፣ በጎንደርና በባህር ዳር እንዳሳየው፣ በኢትዮጵያ ባሉ ግዛቶች ያሉ ብሄረሰቦችን ሁሉ ያቀፈ ፣ አገራዊና  ሰላማዊ እንቅስቃሴ መሆኑንም በግልጽ እያሳየ ነዉ። ይህ የሰለጠነና ሁሉንም ያቀፈ ፖለቲካ ለአገራችን የሚጠቅም ፖለቲካ ነዉ። ጥሩና መልካም ጅማሬ ነዉ። ይሄ እንቅስቃሴ በአጭሩ ከተቀጨ፣  ነገ ተመሳሳይ እንቅስቅሴ እስኪመጣ አመታት ሊፈጁ ይችላሉ። በመሆኑም ይሄ እንቅስቃሴ በሃሳብም በሰው ኃይል በገንዘብ እንዲጠናከር ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነዉ። ይሄ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ይሄ አገርን የማዳን፣ አገርን ወደፊት የማስኬድ ጉዳይ ነዉ። ይህ የሰባአዊ መብት ጉዳይ ነዉ። ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ እንቅስቅሴዎች በጋምቤላ፣ በአዳማ፣ በፍቼ፣ በወሊሶ፣ በባሌ፣ በአዲስ አበባ ይኖራሉ። የተላለፈው የመቀሌዉ ሰልፍ በተጠናከረ ሁኔታ ይደረጋል። ለዚህ ሁሉ፣  ብዙ ወጭ ያስፈልጋል። በሚከተለው ድህረ ገጽ በመሄድ፣ የገንዘብ እርዳታ እናድርግ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! በመላዉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ድምጻቸውን እያሰሙ ካሉ ወገኖቻችን ጋር እንቁም !
  1. በኦንላይን እርዳታ ለማድረግ ለምትፈልጉ በፔይፓል (pay pal secure payment) ከሚከተሉት አንዱ ድህረ ገጾችን ይጎብኙ
http://www.fnotenetsanet.com/?p=5337

የፖለቲካ ጋብቻ ከሃይማኖቶች ጋር ለመፈጸም የሚዳራው ወያኔ ኢህኣዴግ ነው!!! የስልጣን ጥምን ማርካት ወይንስ የፖለቲካ እውቀት ማነስ?



ምንሊክ ሳልሳዊ

መካሪ ቄስ/ፓስተር ያጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ
ጠ/ሚሩ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚያራምዱት ኢፍትሃዊ አቋም የፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያናቸውም ነጸብራቅ ውጤት ነው::በተለጣፊነት የሃገሪቱ የበላይ አካል ሆኖ አገለግላለው የሚለው ሃዋሪያዊው ሃይለማርያም ደሳለኝ ምነው መካሪ አጣ:: እኛ እኮ የጠበቅነው በሕወሓት ትእዛዝ የኢድን በኣል ለማክበር የወጡ ዜጎች በፖሊስ ሲጨፈጨፉ ጎመን በጤና ብሎ ስልጣኑን በገዛ ፍቃዱ ይለቃል ብለን ነበር::

ሆኖም ይባስ ብሎ የረባ አማርኛ እንኳን በማትችል ጋዜጠኛ ጥያቄ መሰል መልስ ተጠይቆ የመለሰው ነገር መንግስታዊ ጂልነት የተንጸባረቀበት ነው:: ምነው እነዚህ የሃዋርያት ፓስተሮች ምን ዋጣቸው ?ምእመናቸውን አይመክሩም እንዴ ? የጠሚያችንን ስልጣን ተገን አድርገው በሙስና ከመዘፈቅ መንፈሳዊ ምክርንም መለገስ አለባቸው:: ይህ አይነት አብዮታዊ ሃዋርያነት የትም አያደርስም::

በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በየጊዜው እየተቀያየር የመጣው ወንጀል ማንም ሰው ሊቀበልው አለመፈለጉን እና ኢተአማኒነቱ እየጎላ መምጣቱን የተገነዘበው ወያኔ አሁንም የፖለቲካ ጋብቻ በሚል ሰበብ ፈጥሮ ቀሪውን ዜጋ ለማጥቃት እያቆበቆበ ነው:: የፖለቲካ ጋብቻ እና መዳራት እየፈጠረ ያለው የወያኔው ጁንታ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም::ህገመንግስት እስካለ ድረስ የሙስሊሙ ጥያቄ ህግን መሰረት አድርገው መዳኘት እንዳለበት መንግስት በሃይማኖት እጁን ጣልቃ ማስገባቱ በይፋ እየመሰከረ መሆኑን እኛ ሳንሆን ባለስልጣናቱ የሚናገሩት ተደጋጋሚ ጉዳይ ነው::ሃይማኖት የለኝም የሚለው ሶሻሊስታዊው ደርግ ያልፈጸመውን ማፍያዊ ድርጊት ይህ የወያኔ ጁንታ እየፈጸመው መሆኑን ሁላችንም እንዳሳሰብን ስንገልጽ ብንቆይም እስከዛረ ሰላማዊው ትግል ወደ ጸብ ይቀየራል በሚል የዋህነት አይሉት ጸብኣጫሪነት ጎስት ወያኔ ጥርሶቹን አሹሎ ዜጎችን እያሸበረ ነው::

የፖለቲካ ጋብቻ የተፈጸመው በወያኔ መንግስት መሆኑ ብዙ ሳንርቅ ካደራጀው መጅሊስ ጋር ያለው መዳራት ከአህበሽ ጋር ወያኔ የሚፈጽመው እርኩስት እንዲሁም ስብሰባዎች ዝግጅቶች በጀቶች በራሳቸው ብዙ ሳንጓዝ ምስክሮች ናቸው :;አሁንም የሰላም ጉባዬ በሚል አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሃይማኖቶች ላይ የበላይነትን እንዲይዝ የሚደረግ የመዳራት ሩጫ በራሱ ምስክር ነው::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካለ አማካሪ በትእዛዝ የተናገሩት ነገር ነገ ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውንም የሚከተሉትን ሃይማኖትንም ከተጠያቂነት አያተርፍም:: የሚከተሉት ቤተክርስቲያም የተዘፈቀበት መንግስታዊ ሙስና አላላውስ ስላለው አስፈላጊውን መንፈሳዊ ኦረንቴሽን ለምእመኑ ባለስልጣን ሊሰጥ አለመቻሉ በሚያመልከው በሰማያዊው ብቻ ሳይሆን በምድራዊውም ህግ እንደሚጠየቅ ማወቅ አለበት::ጠ/ሚሩ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚያራምዱት ኢፍትሃዊ አቋም የፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያናቸውም ነጸብራቅ ውጤት መሆኑን ለመናገር እፈልጋለሁ::
ምንሊክ ሳልሳዊ

Lelise Wodajo, an Oromo Journalist, finally free

Do you remember an Oromo female journalist arrested only for being only Oromo in 2008? Yes, Lelise Wodajo is our heroine. She is finally free and rejoined her family in Australia.

The case of Mrs. Lelise Wodajo, a mother of three dependent children and wife of former ETV journalist Mr. Dhabasa Wakjira was arrested after her husband fled the country to escape further persecutions after three years in prison without trial. She was sentenced for 10 years without parole.
While we are rejoicing Lelise’s freedom, let us remember also thousands and thousands of Oromo languishing in every Tigre prisons around the Empire for similar reason.
Below is background information about Lelise Wodajo:
183153_197148860303512_4124982_n
Lelise Wodajo and two of her three children


source. http://ayyaantuu.com/horn-of-africa-news/oromia/lelise-wodajo-an-oromo-journalist-finally-free/

TILAHUN GESESSE FOR ETHIOPIA


Sunday, August 11, 2013

Tirunesh Dibaba wins women’s 10,000m – AFP

MOSCOW: Ethiopian Tirunesh Dibaba produced an effortless masterclass in middle-distance running to win a third world 10,000m title at theWorld Athletics Championships on Sunday.

Dibaba clocked 30min 43.37sec, with Gladys Cherono of Kenya taking silver (30:45.17), and Ethiopia’s Belaynesh Oljira claiming bronze (30:46.98).
Dibaba can rightly be lauded as queen of the 10km event, having also won two Olympic golds over the distance.
The 27-year-old missed the Daegu worlds in 2011 because of injury but has never lost in her 10 outings over 25 laps of the track.
The self-proclaimed “baby-faced destroyer”, a nickname she professes to adore, comes in the mould of male compatriots Haile Gebrselassie and Kenenisa Bekele.
Four world golds (5,000m in 2003 and 2005, 10,000m in 2005 and 2007), three Olympic golds (the double in 2008 and 10,000m gold in 2012) as well as two 5,000m Olympic bronzes (2004 and 2012) is testimony to her dominance.
She also has four golds and two silvers from the world cross-country championships.
The race itself played directly into Dibaba’s hands, American Shalane Flanagan taking up the early running, followed by Japan’s Hitomi Niiya, with Oljira and Dibaba close on their tails.
The Kenyan trio did not feature the 2011 world champion Vivian Cheruiyot, who is on maternity leave from the sport, but Emily Chebet, Cherono and Sally Chepyego were a powerful threesome on the track all the same.
After five laps, a 10-strong pack had developed with the field strung out, lightning flashes and peels of thunder ripping over the Luzhniki Stadium.
Flanagan, the 2008 Olympic bronze medallist, took them through the 3km mark in 9:20.85 as the rain began to fall before Niiya hit out on her own.
She was soon reeled in by the pack, the 32-year-old Flanagan falling off the pace and Dibaba sitting on the Japanese runner’s shoulder through the halfway marker.
Although the pace was anything but electrifying, the pack was now cut to Niiya leading Dibaba and Oljira, the Kenyan trio and Bahrain’s Ethiopian-born Shitaye Eshete.
Chepyego and Eshete were next to fall off the Japanese’s pace-setting, Dibaba looking completely untroubled.
The rain eased off as the storm worked its way around the stadium and with two laps to go Niiya still had the lead.
At 600 metres, Dibaba and Oljira briefly communicated and on the bell, the former bolted.
She was chased down the back stretch by Cherono, the 2012 African champion over both 5000m and 10,000m making her debut at a global championship at the age of 30, but to no avail as the Ethiopian held out for a very comfortable win.

Updated news) Arabsat to continue broadcasting ETV after negotiation

EMF – Arabsat took Ethiopian’s propaganda machine ETV off air on Friday next day after Ethiopian Federal Police brutal act against Ethiopian Muslims. According to our source; Arab Sat promised to start broadcasting ETV after holding discussion with Ethiopian diplomats yesterday.
Ethiopian activists reached out to Arabsat and asked ETV to be removed from platform, alleging ETV broadcasting hatred and false accusation against oppositions and Ethiopian Muslims. Source told to EMF, Arabsat asked Ethiopian government to give reasonable explanation why Police brutally attacked peaceful Ethiopians in Addis Ababa and other cities of the country.  According to EMF source, Arabsat will restart Ethiopian TV soon.
Activist told to EMF, “We need to come together and demand Arasat to stand with its previous decision and stop broadcasting EPRDF’s propaganda machine, ETV signals until it gets reasonable explanation on police’s hostility against Ethiopians”.

Ethiopia has been a land of absolute military dictatorship before and after the death of the late Meles Zenawi. It is believed that the current Ethiopian prime minister, Hailemariam Desalegn has no-say on actions taken by the military and security forces.
The move by Arabsat may give the opportunity to ESAT and other Ethiopian Media to gain control of covering events unfolding in Ethiopia. Ethiopian opposition Media accused the current Ethiopian regime for the killing of hundreds and violation of Human Rights in the country.
Following Thursday’s violation, Amnesty International released a statement calling on the Ethiopian government to end “repressive tactics against demonstrators”.
Recently, Arabsat stopped the broadcasting Syrian, Libya and other dictatorial regime, government Television channels including Press TV.