ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዲግ በሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ባለፉት ሐያ-ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረቱን፥ ፍትሕና ርትዕት መስረጹን አስታዉቋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት
የቀድሞዉ አማፂ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሐዴግ) የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስግዶ ሥልጣን የያዘበት ሃያ-ሁለተኛ ዓመት ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ዛሬ እየተከበረ ነዉ።ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዲግ በሚቆጣረቻዉ መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ባለፉት ሐያ-ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረቱን፥ ፍትሕና ርትዕት መሥረጹን አስታዉቋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የሰወስት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የሃያ-ሁለት ዓመቱ ጉዞ የዴሞክራሲዊ ሥርዓት የተጓደለበት፥ ሙስና የሠፈነበት እና የኢሕአዴግ ባለሥልጣናትና ካድሬዎች የተጠቀሙበት ነዉ።ዝርዝሩን እነሆ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ዘገባውን ለማዳመጥ ቁልፉን ይክፈቱት
http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_16843945_mediaId_16843774
No comments:
Post a Comment