Monday, May 13, 2013

በሙስና ተጠርጣሪ ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ቀረቡ


ኢትዮጵያ

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የመንግስት ባለስልጣናት ዛሬ፥ ግንቦት 5 ቀን 2005 ዓም ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታወቀ። ፍርድ ቤቱ ለነገ ከሠዓት በኋላ ተጨማሪ ቀጠሮ መያዙም ተገልጿል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የጉምሩክ ኃላፊዎች የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ይገኑበታል

የፌዴራል የፀረ ሙስና እና ስነምግባር ኮሚሽን በሙስና ተጠርጥረዋል ብሎ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የጉምሩክ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው። የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ባለቤትም ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ ትናንት የቤት ካርታዎችንና ሠነዶችን ሲያሸሹ ተገኙ በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ገልጾዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_16810255_mediaId_16810259

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ

No comments:

Post a Comment