Thursday, May 30, 2013

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ


የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደ በኋላ ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ዉሳኔዎችን ካሳለፈ በኋለ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄዉ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄዉ ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸዉን መንገዶች፤ ያቀዳቸዉን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪዉ የትግል ወቅት የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዘዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸዉን አበይት ዉሳኔዎች አሳልፏል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የንቅናቄዉን የአለፉት አምስት አመታት ጉዞና በዚህ በአራተኛዉ ጉበኤ ላይ የስልጣን ዘመናቸዉን የጨረሱት የንቅናቄዉ ምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ዕቅድና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ በጉባኤዉ ላይ አዲስ ለተመረጡ የአመራር አባላት ንቅናቄዉ የታሰበበትን ግብ እንዳይመታ አንቀዉ የያዙትን እንቅፋቶች እንዲያስወግድና እንዲሁም የንቅነቁዉ ጥንካሬ በታየባቸዉ መስኮች አቅሙን አጣናክሮ በይበልጥ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ ከንቅናቄዉ የሚጠብቀዉን የታሪክ አደራ እንዲወጣ አሳስቧል። በጉባኤዉ ወቅት አባላት ያደረጉት አመራሩን የመንቀፍ፤አቅጣጫ የማሳየት፤ ሀሳብ የማመንጨትና በአጠቃላይ በእያንዳንዱ የጉባአዉ ስብሰባ ላይ ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ ንቅናቄዉ በህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት ዘርፎች ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍም እያደገ መምጣቱን አሳይተዋል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲሁም የስነ ስርአትና የግልግል ኮሚቴ ሪፖርቶችን አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ ሪፖርቶቹን አጽድቋል። ከዚህ በተጨማሪ የንቅናቄዉን እስትራቴጂና ይህንኑ እስትራቴጂ ተሸክሞ በተግባር የሚተረጉመዉን መዋቅር በአጽንኦት ከፈተሸ በኋላ በስትራቴጂዉ ላይ መጠነኛ ለዉጥ በማድረግ የእስትራቴጂዉንና የመዋቅር ለዉጡን ተቀብሎ አጽድቋል። ይህ የንቅናቁዉ አራተኛ ጉባዜ ንቅናቄዉን ላለፉት ሁለት አመታት የመሩትንና ያገለገሉትን የምክር ቤት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ የስነ ስርአትና ግልግልና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ በማሰናበት በምትካቸዉ ንቅናቄዉን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤት አባላት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር ከቃኘ በኋላ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ዉጊያ የተያያዘዉ አገር ዉስጥና በዉጭ አገሮችም ስለሆነ ወያኔን በእነዚህ ሁለት የትግል መስኮች እንደአመጣጡ ከገጠምነዉ የሚሸነፍ ድርጅት መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመቀበል አባላቱ ባሉበት ቦታ ሁሉ የሚሰሩት ስራ ወያኔን በማስወገድ ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል። ከአለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የግንቦት ሰባት አባላትን ያሰባሰበዉ አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ የትግል ቃል ኪዳን የታደሰበት፤የመስዋዕትነት ዝግጅት የታየበትና አባላት የትግልና የስራ ልምድ የተላዋወጡበት ከምን ግዜዉም ባላይ የተሳካና የተዋጣለት ጉባኤ ነበር። በመጨረሻ ጉባኤዉ የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ለአባላቱና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ የትግል ጥሪ በማስተላለፍ ደማቅ በሆነ ስነሰርአት ተፍጽሟል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

Tuesday, May 28, 2013

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋሁን ቤንሻንጉል-ጉምዝ ውስጥ ታስሯል

“ኢትዮ-ምኅዳር” ለሚባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ከአማራ ክልል ሲዘግብ የቆየው ሙሉቀን ተስፋሁን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ፖሊስ መያዙን የጋዜጣው ምንጮች አስታወቁ።


ኢትዮ-ምኅዳር” ለሚባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ከአማራ ክልል ሲዘግብ የቆየው ሙሉቀን ተስፋሁን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ፖሊስ መያዙን የጋዜጣው ምንጮች አስታወቁ።
የቤንሻንጉል-ጉምዝ ወረዳዎች


የቤንሻንጉል-ጉምዝ ወረዳዎች


ቤንሻንጉል-ጉምዝ
x
ቤንሻንጉል-ጉምዝ

“ኢትዮ-ምኅዳር” ለሚባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ከአማራ ክልል ሲዘግብ የቆየው ሙሉቀን ተስፋሁን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ፖሊስ መያዙን የጋዜጣው ምንጮች አስታወቁ።

ስለጋዜጠኛው እሥራት ከአካባቢው ፖሊስ መልስ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሣካም።

ሙሉቀን ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረበም የቅርብ ዘመዶቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት “የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው” ሲል በአንቀፅ 19 ንዑስ አንቀፅ 3፤ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሣቡን የመግለፅ ነፃነት አለው፤ ይህ ነፃነት በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንሃውም የማሠራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሣብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሠራጨት ነፃነቶችን ያካትታል” ሲል በአንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 2 ያረጋግጣል፡፡ እንዲሁም በአንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 3 እና ንዑስ አንቀፅ 3/ለ የሚከተለው ሠፍሯል “3. … የፕሬስ ነፃነት የሚከተሉትን ሕጎች ያጠቃልላል…፤ …ለ/ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን”

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋሁን ዓርብ ግንቦት 16/2005 ዓ.ም ጀምሮ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል ዶቢ በምትባል የገጠር መንደር ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ መቆየቱንና እስከዛሬም ማክሰኞ ግንቦት 20/2005 ዓ.ም ፍርድ ቤት አለመቅረቡን ቅርበት ያላቸውና ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በዶቢ ቀበሌ እሥር ቤት ውስጥ ሣለ ሙሉቀንን ባለቤቱና ወንድሙ ሄደው የጎበኙት ሲሆን ማክሰኞ፣ ግንቦት 20/2005 ዓ.ም ጠዋት ግልገል በለስ በተባለ ሥፍራ ወደሚገኘው የዞኑ እሥር ቤት መወሰዱን ምንጩ ጠቁመዋል፡፡

ሙሉቀን ለላከው “ኢትዮ-ምኅዳር” ጋዜጣ መረጃ በመሰብሰብ ላይ እያለ ፖሊሶቹ ጋዜጠኛ ለመሆኑ ማስረጃ እንዲያቀርብ ጠይቀውት ማሣየቱንና “በፖለቲካ ነው የምንፈልግህ” ብለው እንደወሰዱት፤ በአካባቢው የነበሩት ሰዎች “ለምን ትወስዱታላችሁ?” ብለው ሲጠይቁም “እናንተንም እናስራችኋለን” ብለው ያስፈራሯቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አመሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡






የግንቦት ሐያ በዓልና የተቃዋሚዎች ቅሬታ


ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዲግ በሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ባለፉት ሐያ-ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረቱን፥ ፍትሕና ርትዕት መስረጹን አስታዉቋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት
***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** 
DW-Grafik: Per Sander
2011_03_10_Laender_Prio_A_B

የቀድሞዉ አማፂ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሐዴግ) የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስግዶ ሥልጣን የያዘበት ሃያ-ሁለተኛ ዓመት ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ዛሬ እየተከበረ ነዉ።ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዲግ በሚቆጣረቻዉ መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ባለፉት ሐያ-ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረቱን፥ ፍትሕና ርትዕት መሥረጹን አስታዉቋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የሰወስት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የሃያ-ሁለት ዓመቱ ጉዞ የዴሞክራሲዊ ሥርዓት የተጓደለበት፥ ሙስና የሠፈነበት እና የኢሕአዴግ ባለሥልጣናትና ካድሬዎች የተጠቀሙበት ነዉ።ዝርዝሩን እነሆ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ
ዘገባውን ለማዳመጥ ቁልፉን ይክፈቱት 
http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_16843945_mediaId_16843774

Sunday, May 26, 2013

የታሰረው ሦስት ትውልድ


ትላንት ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ሲል የአውራምባ ልጆች (እኔ፣ አቤል አለማየሁ እና ኤልያስ ገብሩ) ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተገኘን፡- ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ለመጠየቅ፡፡ ርዕዮትን ከሰኞ እስከአርብ ለ10 ደቂቃ መጠየቅ ይቻላል፡፡ በዚያች 10 ደቂቃ ከሴቶች ክልል ለጥየቃ የሚወጡት ሁለት እስረኞች ብቻ ናቸው፡፡ ርዕዮት ዓለሙ እና ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ፡፡ እናም ታሳሪዎቹ ከውስጥ ወደ መጠየቂያው አጥር መጡ፡፡ በተወሰነ ርቀት ቆመው ጠያቂዮቻቸውን ያነጋግሩ ጀመር፡፡

Photoከርዕዮት ዓለሙ በስተግራ በኩል ፈንጠር ብለው ጠያቂዎቻቸውን የሚያነጋግሩት ወ/ሮ እማዋሽ “ከግንቦት 7 ፓርቲ ጋር በመመሳጠር ሕገ-መንግስታዊውን ሥርዓት ለመናድ” አሲረዋል ከተባሉት የኢህአዴግ ጄኔራሉች ጋር የተከሰሱ ናቸው፡፡ በዚህ ክስ የተነሳ ነው ሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓም የ25 ዓምት እስር የተፈረደባቸው፡፡

እናም ትናንትም የዘወትር ጠያቂዎቻዋው ከፊት ለፊታቸው ቆመዋል፡፡ አንደኛዋ ጠያቂያቸው እማሆይ ናቸው፤ የመነኩሴ ቆብ አድርገዋል፣ ነጠላቸውን እንደነገሩ አጣፍተዋል፣ መቋሚያ ተመርኩዘዋል፡፡ በግምት ዕድሜያቸው ወደ 90 ዓመት ይጠጋል፡፡

 የታሳሪዋ የወ/ሮ እማዋይሽ ወላጅ እናት ናቸው፡፡ ከእሳቸው ጎን “የወርቅ ፍልቃቂ” የምትመስል ለጋ ወጣት ቆማለች፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን ትባላለች፡፡ (ፎቶዋን ይመልከቱ፡፡) እማሆይ እና ናርዶስ ያለቅሳሉ፡፡ ታሳሪዋ ወ/ሮ እማዋይሽ እንባቸውን ወደውስጥ እያመቁ እነሱን ያፅናናሉ፡፡፡፡ እናት፣ ልጅ እና የልጅ ልጅ በቃሊቲ ቅጥር ግቢ በዚህ መልኩ ማዶ ለማዶ ቆመው ሲላቀሱ ማየት ልብ ያደማል፡፡ እናም ሃዘናቸውን እያየሁ ለራሴ “እነዚህ ሰዎች የታሰረው ሦስት ትውልድ ተምሳሌት ናቸው” አልኩ፡፡ ( በወቅቱ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ በሌላ ቀን “የታሰረው ሦስት ትውልድ” በሚል ርዕስ በዝርዝር ተርከዋለሁ- አሁን ወደ ተነሳሁበት ዋንኛ ጉዳይ ላምራ)

ከላይ እንደነገርኳችሁ የተመደበልን የጥየቃ ደቂቃ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂያ ያህል ሲቀር የ25 ዓመቷ ፍርደኛ ወ/ሮ እማዋይሽ፣ ለልጃቸው ናርዶስ ሙሉጌታ የጆሮ ጌጥ በስጦታ አበረከቱላት፡፡ እናም “መልካም ልደት!” አሏት፡፡ ናርዶስ ስጦታዋን ተቀብላ እንባዋን እንደጅረት ለቀቀችው፡፡ አ…..ህ!! ከዚህ በኋላ የተሰማኝን ስሜት ለመናገር ቃል ያጥረኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ትናንት ግንቦት 16 ቀን 2005 ናርዶስ 19ኛ ዓመት የልደት በዓሏን የምታከብርበት ቀን ነበረ፡፡ እሷ ግን “መልካም ልደት” የማይባልበት ቃሊቲ ናት፤ እያለቀሰች፡፡

እናም ለዚህች ለጋ ወጣት ምንድነው የሚባለው!? መልካም ልደት!?….እን…ጃ!? ከዚህ በኋላ ስንት ልደት ይሆን በዚህ መልኩ የምታከብረው?! አላውቅም! ማንም አያውቅም!…እናም ለዚች ልጅ ልደት ምንድነው!? ወዘተ…. ይኼ ለራሴ ያቀረብኩት ጥያቄ ነው፡፡ ለማንኛውም ወግ ነውና “መልካም ልደት!” ማለት ነው የሚሻለው!!

(በነገራችን ላይ በትናንትናው ዕለት በመብራት መጥፋት ምክንያት ይህንን ማስታወሻ ልፅፍ አልቻልኩም ነበር፡፡ ፎቶዋን ብቻ ነበር በሞባይል ፖስት ያደረኩት፡፡ እናም ፎቶዋን ብቻ አይታችሁ ለናርዲ መልካም ልደት ለተመኛችኋላት የፌስቡክ ሸሪኮቼ ሁሉ በእሷ ስም ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡) መ – ል – ካ – ም ልደት ናርዲ!!!!

የሚቀጥሉት ዓመታት የደስታ ልደት በዓል የምታከብሪበት ይሆኑልሽ ዘንድ በፅኑ እመኝልሻለሁ!!

የሰማያዊ ፓርቲ ሁለት አባላቱ ለምን ጥቁር ልብስ ለበሳቹ ተብለው ታሰሩ


ሰማያዊ ፓርቲ ከግንቦት 15 እስከ 17 /2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ የመልበስና ግንቦት 17/2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ጥቁር ልብስ ለምን ለበሳችሁ በማለት የፓርቲው የኦዲትና ኢንስፒክሽን አባል የሆነው ወጣት ሀብታሙ ደመቀና በነጋታው እርሱን ለመጠየቅ የሄደው ወጣት ራቅሊስ ካሣ መታሰራቸውን ፓርቲው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የፓርቲው አመራር እና አባላት በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመገኘት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን በቀጣይ የታሰሩ አባሎቻችን አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ የሚሰጠው መግለጫ ይኖራል፡፡

Friday, May 24, 2013

ዋናው ጤና ነው

ረሃብን ለማስወገድ በሚደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት ውስጥ የጥንዚዛ፣ የአባጨጓሬ፣ የንብ፣ የተርብና የጉንዳን ዘሮችን ለምግብነት መጠቀም እጅግ ጠቃሚ ሚና ሊጫወት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የግብርና ድርጅት - ኤፍኤኦ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ አሁን እነዚህን ነፍሣት የዕለት ምግባቸው አድርገው የሚኖሩ ከሁለት ቢሊየን በላይ ሰዎች መኖራቸውን አመልክቶ በገንቢና አልሚ ምግቦች የከበሩ፣ በቅባት፣ በበረትና ሌሎችም ማዕድናትና ንጥረነገሮች የበለፀጉ ናቸው ብሏል፡፡

ነገ-ነፍሣትነገ-ነፍሣት
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም ጠቃሚ ናቸውና በመላው ዓለም መለመድ ያለባቸው የምግብ ዓይነቶች መሆን አለባቸው ሲል ኤፍኤኦ ሃሣብ አቅርቧል፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ በአስም ለሚንገላታ በዓለም ዙሪያ ከሦስት መቶ ሚሊየን በላይ ለሚሆን ሰው መጠነኛም ቢሆን እፎይታን ሊያስገኝ ይችላል የሚል ጥናት በዝንጅብል ላይ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህ ድንቅ የሥራ ሥር ውጤት ውስጥ - አሉ የረዥም ጊዜ ክትትል ሲያደርጉ የቆዩት የኒው ዮርኩ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች - የመተንፈሻ አካላትን ጡንቻዎች የሚያዝናና ኃይል ያለው ንጥረ ነገር አለ፡፡ ያንን ንጥረ ነገርም ነጥለው አውጥተው በመድኃኒቶቹ ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉባቸውን መንገዶች እያሰቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሌላ ዘገባ እንደሚናገረው ደግሞ ተዋናይት እና የተባበሩት መንግሥታት የበጎ ፍቃድ አምባሣደር አንጀሊና ጆሊ ‘…አንድ ቀን …ወደፊት .. ልጋለጥ እችል ይሆናል’ በሚል ሁለቱንም ጡቶቿን ማስወገዷ የሰሞኑ የመገናኛ ብዙኃን አጀንዳ እና የካንሠር መከላከያ ቀዶ-ሕክምናም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
http://amharic.voanews.com/content/health-05-21-13/1664923.html

የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የስራ መመሪያ ተቀበሉ!

ቅዳሜ ግንቦት 17/ 2005 በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያስተባብሩ የተለያየየ ስራ ዘርፍ አባላት ዛሬ ግንቦት 15 ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በፓርቲው ጽ/ቤት በኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀመንበርየስራ መመሪያና አጠቃላይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ለማስታወሻነትም በጋራ የፎቶግራፍ መነሳት ስነስርዓትተከናውኗል።

semayawi party members in Addis Ababa

blue party members picture, addis ababa

Thursday, May 23, 2013

Amnesty International 2013 Report: Ethiopia


Freedom of expression Human rights defenders Torture and other ill-treatment Arbitrary arrests and detentions Excessive use of force Conflict in the Somali region Forced evictions

Amnesty International 2013 Report: Ethiopia
The state stifled freedom of expression, severely restricting the activities of the independent media, political opposition parties and human rights organizations. Dissent was not tolerated in any sphere. The authorities imprisoned actual and perceived opponents of the government. Peaceful protests were suppressed. Arbitrary arrests and detention were common, and torture and other ill-treatment in detention centres were rife. Forced evictions were reported on a vast scale around the country.

Background
In August, the authorities announced the death of Prime Minister Zenawi, who had ruled Ethiopia for 21 years. Hailemariam Desalegn was appointed as his successor, and three deputy prime ministers were appointed to include representation of all ethnic-based parties in the ruling coalition.
The government continued to offer large tracts of land for lease to foreign investors. Often this coincided with the “villagization” programme of resettling hundreds of thousands of people. Both actions were frequently accompanied by numerous allegations of large-scale forced evictions.
Skirmishes continued to take place between the Ethiopian army and armed rebel groups in several parts of the country – including the Somali, Oromia and Afar regions.
Ethiopian forces continued to conduct military operations in Somalia. There were reports of extrajudicial executions, arbitrary detention, and torture and other ill-treatment carried out by Ethiopian troops and militias allied to the Somali government.
In March, Ethiopian forces made two incursions into Eritrea, later reporting that they had attacked camps where they claimed Ethiopian rebel groups trained (see Eritrea entry). Ethiopia blamed Eritrea for backing a rebel group that attacked European tourists in the Afar region in January.
Freedom of expression
A number of journalists and political opposition members were sentenced to lengthy prison terms on terrorism charges for calling for reform, criticizing the government, or for links with peaceful protest movements. Much of the evidence used against these individuals consisted of examples of them exercising their rights to freedom of expression and association.
The trials were marred by serious irregularities, including a failure to investigate allegations of torture; denial of, or restrictions on, access to legal counsel; and use of confessions extracted under coercion as admissible evidence.
  • In January, journalists Reyot Alemu, Woubshet Taye and Elias Kifle, opposition party leader Zerihun Gebre-Egziabher, and former opposition supporter Hirut Kifle, were convicted of terrorism offences.
  • In June, journalist Eskinder Nega, opposition leader Andualem Arage, and other dissidents, were given prison sentences ranging from eight years to life in prison on terrorism charges.
  • In December, opposition leaders Bekele Gerba and Olbana Lelisa were sentenced to eight and 13 years’ imprisonment respectively, for “provocation of crimes against the state”.
Between July and November, hundreds of Muslims were arrested during a series of protests against alleged government restrictions on freedom of religion, across the country. While many of those arrested were subsequently released, large numbers remained in detention at the end of the year, including key figures of the protest movement. The government made significant efforts to quash the movement and stifle reporting on the protests.
  • In October, 29 leading figures of the protest movement, including members of a committee appointed by the community to represent their grievances to the government, and at least one journalist, were charged under the Anti-Terrorism Proclamation.
  • In both May and October, Voice of America correspondents were temporarily detained and interrogated over interviews they had conducted with protesters.
The few remaining vestiges of the independent media were subjected to even further restrictions.
  • In April, Temesgen Desalegn, the editor of Feteh, one of the last remaining independent publications, was fined for contempt of court for “biased coverage” of the trial of Eskinder Nega and others. Feteh had published statements from some of the defendants. In August, he was charged with criminal offences for articles he had written or published that were deemed critical of the government, or that called for peaceful protests against government repression. He was released after a few days’ detention and the charges were dropped.
In May, the authorities issued a directive requiring printing houses to remove any content which could be defined as “illegal” by the government from any publications they printed. The unduly broad provisions of the Anti-Terrorism Proclamation meant that much legitimate content could be deemed illegal.
  • In July, an edition of Feteh was impounded after state authorities objected to one cover story on the Muslim protests and another speculating about the Prime Minister’s health. Subsequently, state-run printer Berhanena Selam refused to print Feteh or Finote Netsanet, the publication of the largest opposition party, Unity for Democracy and Justice. In November, the party announced that the government had imposed a total ban on Finote Netsanet.
A large number of news, politics and human rights websites were blocked.
In July, Parliament passed the Telecom Fraud Offences Proclamation, which obstructs the provision and use of various internet and telecommunications technologies.
Human rights defenders
The Charities and Societies Proclamation, along with related directives, continued to significantly restrict the work of human rights defenders, particularly by denying them access to essential funding.
  • In October, the Supreme Court upheld a decision to freeze around US$1 million in assets of the country’s two leading human rights organizations: the Human Rights Council and the Ethiopian Women Lawyers Association. The accounts had been frozen in 2009 after the law was passed.
  • In August, the Human Rights Council, the country’s oldest human rights NGO, was denied permission for proposed national fundraising activities by the government’s Charities and Societies Agency.
It was reported that the Agency began enforcing a provision in the law requiring NGO work to be overseen by a relevant government body, severely compromising the independence of NGOs.
Torture and other ill-treatment
Torture and other ill-treatment of prisoners were widespread, particularly during interrogation in pre-trial police detention. Typically, prisoners might be punched, slapped, beaten with sticks and other objects, handcuffed and suspended from the wall or ceiling, denied sleep and left in solitary confinement for long periods. Electrocution, mock-drowning and hanging weights from genitalia were reported in some cases. Many prisoners were forced to sign confessions. Prisoners were used to mete out physical punishment against other prisoners.
Allegations of torture made by detainees, including in court, were not investigated.
Prison conditions were harsh. Food and water were scarce and sanitation was very poor. Medical treatment was inadequate, and was sometimes withheld from prisoners. Deaths in detention were reported.
  • In February, jailed opposition leader, Andualem Arage, was severely beaten by a fellow prisoner who had been moved into his cell a few days earlier. Later in the year, another opposition leader, Olbana Lelisa was reportedly subjected to the same treatment.
  • In September, two Swedish journalists, sentenced in 2011 to 11 years’ imprisonment on terrorism charges, were pardoned. After their release, the two men reported that they were forced to incriminate themselves and had been subjected to mock execution before they were allowed access to their embassy or a lawyer.
Arbitrary arrests and detentions
The authorities arrested members of political opposition parties, and other perceived or actual political opponents. Arbitrary detention was widespread.
According to relatives, some people disappeared after arrest. The authorities targeted families of suspects, detaining and interrogating them. The use of unofficial places of detention was reported.
  • In January the All Ethiopian Unity Party called for the release of 112 party members who, the party reported, were arrested in the Southern Nations, Nationalities and Peoples (SNNP) region during one week in January.
Hundreds of Oromos were arrested, accused of supporting the Oromo Liberation Front.
  • In September, over 100 people were reportedly arrested during the Oromo festival of Irreechaa.
Large numbers of civilians were reportedly arrested and arbitrarily detained in the Somali region on suspicion of supporting the Ogaden National Liberation Front (ONLF).
  • The authorities continued to arbitrarily detain UN employee, Yusuf Mohammed, in Jijiga. His detention, since 2010, was reportedly an attempt to get his brother, who was suspected of links with the ONLF, to return from exile.
Between June and August, a large number of ethnic Sidama were arrested in the SNNP region. This was reportedly in response to further calls for separate regional statehood for the Sidama. A number of arrests took place in August around the celebration of Fichee, the Sidama New Year. Many of those arrested were detained briefly, then released. But a number of leading community figures remained in detention and were charged with crimes against the state.
There were reports of people being arrested for taking part in peaceful protests and publicly opposing certain “development projects”.
Excessive use of force
In several incidents, the police were accused of using excessive force when responding to the Muslim protest movement. Two incidents in Addis Ababa in July ended in violence, and allegations included police firing live ammunition and beating protesters in the street and in detention, resulting in many injuries. In at least two other protest-related incidents elsewhere in the country, police fired live ammunition, killing and injuring several people. None of these incidents was investigated.
  • In April, the police reportedly shot dead at least four people in Asasa, Oromia region. Reports from witnesses and the government conflicted.
  • In October, police fired on local residents in Gerba town, Amhara region, killing at least three people and injuring others. The authorities said protesters started the violence; the protesters reported that police fired live ammunition at unarmed people.
Security forces were alleged to have carried out extrajudicial executions in the Gambella, Afar and Somali regions.
Conflict in the Somali region
In September, the government and the ONLF briefly entered into peace talks with a view to ending the two-decade long conflict in the Somali region. However, the talks stalled in October.
The army, and its proxy militia, the Liyu police, faced repeated allegations of human rights violations, including arbitrary detention, extrajudicial executions, and rape. Torture and other ill-treatment of detainees were widely reported. None of the allegations was investigated and access to the region remained severely restricted.
  • In June, UN employee Abdirahman Sheikh Hassan was found guilty of terrorism offences over alleged links to the ONLF, and sentenced to seven years and eight months’ imprisonment. He was arrested in July 2011 after negotiating with the ONLF over the release of two abducted UN World Food Programme workers.
Forced evictions
“Villagization”, a programme involving the resettlement of hundreds of thousands of people, took place in the Gambella, Benishangul-Gumuz, Somali, Afar and SNNP regions. The programme, ostensibly to increase access to basic services, was meant to be voluntary. However, there were reports that many of the removals constituted forced evictions.
Large-scale population displacement, sometimes accompanied by allegations of forced evictions, was reported in relation to the leasing of huge areas of land to foreign investors and dam building projects.
Construction continued on large dam projects which were marred by serious concerns about lack of consultation, displacement of local populations without adequate safeguards in place, and negative environmental impact

Wednesday, May 22, 2013

የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር ከፍተኛ አመራር ታሰረ


Birhanu Tekele Yared
በኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ወጣቶች ስም በተመሰረቱ ማህበራቶችና ፎረሞች ውስጥ ተደራጅተው ከነበሩ ወጣቶች መካከል የተወሰኑት የሚገኙባቸው ማህበራት ‹‹ነጻነት››የማይጨበጥ ሲሆንባቸው ‹‹የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበርን››መሰረቱ፡፡ከመስራቾቹ አንዱም ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ነው፡፡ብርሃኑ ማህበሩን በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንትነትና በህዝብ ግኑኝነት በማገልገል ላይ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ በተለያዮ የህትመት ውጤቶች አማካኝነት ሀሳብን የመግለጽ መብቱን ይጠቀማል፡፡



ማህበሩ በየጊዜው የሚያነሳቸው የመብት ጥያቄዎችና አገራዊ አጀንዳዎች ያላስደሰተው አካል የእነ ብርሃኑን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በአይነ ቁራኛ ሲከታተል ቆይቷል፡፡ወጣቱ የመብት ታጋይ ዛሬ ማለዳ ከሚኖርበት ወረዳ 11 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ከሰዓት በኋላ ለደቂቃዎች በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ የተደረገው ብርሃኑ ‹‹ያሰሩኝ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት አስባችኋል ብለውኛል ፡፡

 ነገር ግን እኛ (ባለ ራዕይ ማህበር)ሰላማዊ ሰልፍ አልጠራንም ሰልፉን የጠሩት ሰማያዊ ፓርቲዎች ናቸው ስላቸው ይህንን ወረቀት ታዲያ ለምን በተንክ ብለው ከዚህ በፊት ተመልክቼው የማላውቀውን ወረቀት አሳዮኝ እኛ ሰልፍ ብንጠራ በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ እንደምናደርገው ነግሬያቸዋለሁ፡፡››በማለት የእስሩን ምክንያት ተናግሯል፡፡ 

የመኖሪያ ቤቱ መፈተሹን የጠቆሙት የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ፖሊሶች ግንቦት 7/2005 ተበትኗል ያሉትን ወረቀት ‹‹ የኤርትራ ጉዳይ ›› በተሰኘ የዘውዴ ረታ መጽኀፍ ውስጥ አገኘን ማለታቸውንና ብርሃኑም ተገኘ የተባለው ወረቀት ቤት ፈታሾቹ ሆን ብለው ያስቀመጡት ካልሆነ በቀር እርሱ እንዳላስቀመጠው በመግለጽ ፖሊሶች ‹‹የእኔ ነው ብለህ ፈርም ሲሉት›› እምቢ ማለቱን በኋላም አሁን ፈርምና ፍርድ ቤት በምትቀርብበት ወቅት የአንተ አለመሆኑን ትናገራለህ በሚል ማግባቢያ ቤተሰቦቹን ማስጨነቅ ባለመፈለጉ መፈረሙን ምንጮቻችን ፡፡ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣብያ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

Tuesday, May 21, 2013

BBC’s George Alagiah Show at African Union (AU) in Addis Ababa



by Tedla Asfaw
GMT BBC World News of this morning, May 20, 2013, from 7am to 8am ET devoted 15 minutes of its time on George Alagiah or George, one of its correspondents on mission to cover the 50th anniversary of OAU/AU in Addis Ababa. The Headlines News on BBC tells its listeners that Ethiopia is one of the fastest growing economy in the world. The small shoe factory, the coffee bean exporter who promised to bring British financed machinery to export the finished coffee product to the world market was the success story to support the claim.

George Alagiah/BBC’s PHOTO
George Alagiah/BBC's PHOTO
George was honored by ringing the bell on the floor of Ethiopian Commodity Exchange, the first of its kind in Africa according to BBC. These “economic miracles” and similar “owned” by the very few minority ethnicity are what the BBC Headlines declared the fastest growing economy of Ethiopia. Prime Minster Hailemariam Desalegn who was interviewed on the program was boasting of converting Ethiopia to manufacturing or industrialized country in the coming decade. However, China will not be happy mentioning Taiwan as one of the models for Ethiopia. Hailemariam is not as sharp as the late Meles Zenawi. Is Ethiopia doing business with both Taiwan and China?

George’s AU Show in the coming day or days will cover the roads and buildings in Addis Ababa to support the march to industrialization. If he travels to the outskirts of Addis Ababa flower farms which is bringing in hard currency for the ruling mafia are replacing food producing farm lands. If he goes far he will see the mechanized farm of Sheik Al Amoudi and similar huge tracts of land under the control of the foreign landlords and the government. All these “growth” are at the expense of small farmers and indigenous people. The British development agency and USAID are financing the land grab. Europe has its flower and America has its security, period!

George invited two students from university, two street dancers and one female architect to his show at AU Studio this morning. The street was very quiet looked like the Green Zone of America in Baghdad. We did not see the security forces but I can assure you that George Show was well protected not from ” terrorists” but from the wider public. If George wants to talk to the young people he could have gone to schools and colleges, why did he ask the school and college to come to him ? He went to Ethiopian Commodity Exchange floor why not go to the universities ? The truth is this. He is in total control by his hosts, the government cadres, because Ethiopia is run by armed group of minority clique which bans free assembly and speech throughout the country. Speech and Assembly are only allowed under the eye of security thugs or government picked paid agents.

The women Architect who informed us that she wants to stay in Ethiopia because construction is booming. If George goes around freely which he might not will find hundreds if not thousands of doctors leaving hospitals not because of lack of job but because of lack of basic freedom in Ethiopia. I challenge George to take his show to the people not bringing selected people to his studio at AU and feeding us tons of propaganda which the Ethiopian people are tired of.

The one minute talk about human rights with Hailemariam Desalegn is very shameful. For BBC what matters is “Food growth” not “Freedom”. I want to give tip to George before he finished his AU Show most likely at the end of this week to Visit the Anwar Mosque and Kaliti Jail in Addis. If you are Muslim you can pray if not wait and follow the prayer. Talk to the young female and male and ask them what “growth” means to them. The journalists and political leaders locked up at Kaliti will not be allowed to talk, some were shipped out not to spoil the AU Show, but why not try to talk to family members, mothers,fathers, wives,husbands and children, who are coming daily for year or years to see their loved ones
Last but not least I want George to cover the peaceful rally of May 25 organized by the newly formed Blue Party/Semayawi of Ethiopia (Blue). They will try to come out right where George is , BBC AU studio. I do not want to give you their Web address because it is blocked. One thing George should not forget to report in few days he enjoys life in Addis is the “growth” in Internet blocking. Ethiopia is the worst abuser of all but BBC does not matter much because its correspondents are blocking themselves. Go Blue Go!

Monday, May 20, 2013

ህዝባዊ ውይይት በኖርዌይ


በኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ በ18.05.13 ህዝባዊ ውይይት አደረጉ። ውይይቱ በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ፤ በእስር ለሚንገላቱና ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚሰቃዩና ለተሰደዱ ወገኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል። በርካታ ታዳሚዎችም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ ጥቁር ልብስ ለብሰው ተገኝተዋል።Ethiopians meeting in Norway
ውይይቱ የተጠራው በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል ሲሆን ያተኮረውም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ነበር፤
ሀ. በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚጫወተው ሚናና በሀገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲ ስለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
ለ. ሰላማዊና ሌሎች የትግል ስልቶች በኢትዮጵያ እና ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
ሐ. ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመገናኛ ብዙሀን፤ ከሰብአዊና ከዲሞክራሲ መብቶች አንጻር
መ. ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታና በሀገር ቤት ስለታቀደው የሰማያዊ ፓርቲ ተቃውሞ ሰልፍ
ሰ. የሀይማኖት ነጻነት በኢትዮጵያና ሰማያያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የሚሉት ይገኙበታል።
በነዚህ ወቅታዊና አንገብጋቢ ርዕሶች ላይ ለታዳሚዎች የመወያያ ሃሳቦችንና ገለጻዎችን ያቀረቡት በቅደም ተከተል አቶ አርጋው ያቆብ፤ አቶ ዳንኤል አበበ፤ አቶ ዳባ ጉተማ፤ አቶ ዳሂሎን ያሲን እንዲሁም አቶ ሙሀመድ ሲራጅ ሲሆኑ ዝግጅቱንና ውይይቱን የመሩት ደግሞ አቶ ዳዊት መኮንን ናቸው።
በውይይቱ ላይ በርካታና ዝርዝር ጉዳዮችና ሀሳቦች ተነስተዋል።
በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራው) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አቶ አርጋው በዝርዝ አቅርበዋል። በሚዲያና በቴክኖሎጂ በመደገፍ አገር ውስጥና ውጪ ካሉ ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር የመረጃ ልውውጦችንና ቅስቀሳዎችን በማድረግ፤ ለአለም አቀፍ ድርጅቶች አቤቱታን በማቅረብ፤ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ፤ በመዋጮ በቁሳቁስና በሞራል ተቃዋሚ ሀይሎችን በመደገፍ፤ ገዢው አካል አለም አቀፋዊ ድጋፍ እንዳያገኝ በማድረግ፤ በሲቪክ ማህበራት በመደራጀት ወዘተ ዲያስፖራው በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ጉልህና ትልቅ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አስረድተዋል። በአንፃሩ ደግሞ በሀገር ጉዳይ ላይ የተሳትፎ ማነስ፤ እኔ ምን አገባኝ የማለት፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አፍራሽ ዜናዎችን በማሰራጨትና የወያኔን ፖለቲካ በማራገብ፤ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ከትግሉ በማፈግፈግ፤ ለግል ጥቅም በመገዛት ከወያኔዎች ጋር በመተባበር ወዘተ ዲያስፖራው ትግሉን ሊያዳክመው እንደሚችል አስገንዝበው ይህን በተመለከታ ተቃዋሚ ሀይሎች ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።Ethiopian in the Diaspora, meeting in Norway
በሌላ በኩል ደግሞ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን በተመለከተ አቶ ዳንኤል እንዳብራሩት፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰላማዊ ትግል ማታገያ ስልቶች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋና የሆኑት ከሶስት እስከ አምስት የሚጠጉ ስልቶችን ጠቅሰዋል። ከነዚህም መካከል ትብብር መንፈግና ተፅዕኖ መፍጠር ይገኙበታል። በዚህ አጋጣሚ አሁን ያለውን ስርዓት ለመለወጥ ሁለገብ የትግል እንቅስቃሴን መደገፍ ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
አቶ ዳባ ጉተማ በበኩላቸው ስለዜጎች መፈናቀል፤ ገዢው ፓርቲ የሚቀሰቅሳቸው ፀብ አጫሪ ሁኔታዎች፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሰላማዊ መንገድ በሚታገሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ ስለሚደርሰው ግድያ፤ አፈና፤ እስር፤ እንግልትና ወከባ፤ በኑሮ ውድነትና በመሳሰሉት በገጠርና በከተማ በህዝቡ ላይ ስለሚደርስ ስቃይ፤ በአሁኑ ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሚሆኑት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መስዋዕት ለማድረግ የቆረጡ መሆናቸው በአጠቃላይ የፖለቲካ መህዳሩ የሚመች እንዳልሆነ፤ እስከዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ገዢ እንጂ መሪ አግኝቶ እንደማያውቅና ያሁኑ ግን ሲኦል እንደሆነበት በዝርዝርና በተጨባጭ ምሳሌዎች በጣም በርካታ ጉዳዮችን አንስተው ለተወያይ ታዳሚዎች አቅርበዋል። በተጨማሪም ትላንት ካልነበረ ዛሬ እንደሌለ ዛሬ ከሌለ ደግሞ ነገ እንደማይኖር የታወቀ ስለሆነ ለዛሬ በጣም እንድናስብበት አሳስበዋል።
እንዲሁም አቶ ዳሂሎን ያሲን በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ሰማያዊ ፓርቲ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍን አቶ ዳሂሎን እንደመነሻ የምርጫ 97 ሰላማዊ ሰልፍን ካነሱ በኋላ በአሁኑ ወቅት በይፋ ስለተጠራው ስለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሊኖሩት ስለሚችሉት አሉታዊና አዎንታዊ ገፅታዎች አብራርተዋል። በዋናነትም የሰላማዊ ሰልፉ መጠራት ቢሳካም ባይሳካም ያለውን ጠቀሜታና በንፅፅርም የሚታዩትን ስጋቶች ተንትነዋል።Ethiopians gathered in Norway to discuss current Ethiopian politics
በወቅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄዎችና በገዢ አካል ስለሚደረገው የሀይማኖት መብት ረገጣ በተጨማሪም አሁን ስላለው ችግር መንስኤ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ በአቶ ሙሀመድ ሲራጅ ቀርቧል።
ታዳሚዎችም በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳት ከፍተኛ ተሳትፎ የተደረገበት ውይይት አድርገዋል።
በመጨረሻም የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የተደረገበትን ተቃውሞ አንደኛ አመት በማስታወስ ነፃነት ነፃነት ነፃነት የሚለው መሪ ቃል በህብረት፣ በስብሰባው መክፈጫ ላይ ተብሎ እንደተጀመረ ሁሉ የእለቱ ስብሰባ ሲጠናቀቅም በተመሳሳይ መልኩ ተሰብሳቢዉ ከመቀመጫቸዉ ተነስተዉ በአንድ ድምፅ ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት! የሚለዉን ቃል አሰምተዋል።
በስብሰባዉ ማጠቃለያ ተሰብሳቢዉ በጋራ የተስማሙባቸዉን የሚከተሉትን ሦስት አበይት ሃሳቦች የስብሰባዉ የአቋም መግለጫ በማድረግ የእለቱን ስብሰባ አጠናቀዋል።
1ኛ.በኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት፣የፖለቲካና ሃይማኖት ነፃነት፣ እንዲከበር በተጨማሪ የንፁሃን ወገኖቻችንን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅለዉ ለሞት ያደረጓቸዉን ሰዋችና የመንግስት ባለስልጣናት፣የሃይማኖት መብት ጥያቄ ባቀረቡ ያሰሯቸዉና የገደሏቸዉን ባለሰልጣናት እነዲሁም በኢትዮጵያ በተለያየ ቦታ የፖለቲካ፣የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት አባላትና መሪዋችን ያሰሩና ደም ያፈሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
2ኛ.በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፉ በጋራ አቋም መግለጫቸዉ አረጋግጠዋል።በተጨማሪ ከአገር ዉጪና በአገር ቤት ያሉ የፖለቲካ፣የሲቪክ፣የሐይማኖት፣ የሴቶችና ወጣቶች መህበራት ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራዉ ሰልፍ በተመሳሳይ መልኩ ድጋፍ እንዲያርጉላቸዉ ተሰብሳቢዉ አክለዉ በአቋም መግለጫቸዉ አሳዉቀዋል።
3ኛ.በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እያንዳንዳቸዉ የፌስቡካቸዉን ፕሮፋይል በማጥቆርና ቀስቃሽ ድጋፍ ሰጪ ፅሑፎችን ለሌለዉ በማሰራጨት፣እንዲሁም በፓልቶክና በሎሎች ብዙሃን ማሰራጫ ድጋፋቸዉን እንደሚሰጡና ሌላዉም ኢትዮጵያዊ በተመሳሳይ ሁኔታ ድጋፉን በመስጠት ሁሉም የዜግነቱን ግዳጅ እንዲወጣ አሳስበዋል።
አንድነት ሃይል ነዉ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል

Friday, May 17, 2013

17 mai nationaldag fest i ås Norway 2013


| Millions of dollars found at the residence of late dictator Meles Zenawi’s close friend and confidant (video)

Elias Kifle | May 17th, 2013


Police seized millions of dollars from the private residence of Gebrewahid Woldegiorgis, a close friend and confidant of the late Ethiopian dictator Meles Zenawi this week.



If Gebrewahid has kept this much money in his residence, one can imagine how much money he has transferred out of the country, and how much his late boss Meles Zenawi and wife Azeb Mesfin have stolen. Gebrewahid is the latest fall-guy in the ongoing power struggle inside the ruling junta. 

He is no more corrupt than any of the other TPLF officials who have been sucking the life blood of Ethiopia during the past 20 years.

According to Ethiopian Review’s Intelligence Unit sources in Addis Ababa, the recent purges are being orchestrated by the deputy chief of security Isayas Woldegiorgis and close ally Bereket Simon, who is the minister of government communication.


Thursday, May 16, 2013

ባለ ራእዩ ወያኔ/ኢህአዴግ በሙስና ቅሌት እራሱን አጋለጠ

እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌይ
may 16.2013
ባለ ራእዩ የወያኔ  መንግስት ባልታወቀ ወይም ሆን ተብሎ በተሰራ የቴክኔክ ብልሽት በዚህ ሰሞን በአባላትና ጀሌዎቹ ላይ ለ22 አመታት ታይቶ በማይታወቅ የሙስና ቅሌት ሰበብ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እያጎሯቸው ይገኛል።  የሚገርመው ደጋፊዎቻቸው ከሐገር ቤት እስከ ዲያስፖራው  ብዙ ሲለፈልፉላቸው ይሰማ ነበር ልማታዊ  መንግስታችን፤ ልማታዊ ሚኒስትሮቻችን ፤ ልማታዊው መሪያችን  በማለት ከሰብአዊ መብት ጥበቃ በፊት መንገድ ስራና የአፓርታማ ግንባታ ይቅደም በማለት  መቆሚያና መቀመጫ አሳጥተውን ነበር አሁን ምን ይውጣቸው ይሆን?  እንደ ለመዱት ልማታዊ ሙስና ነው ብለው እንዳያስደነግጡን እንፈራለን።

haገራችንን ኢትዮጵያን ወያኔ /ኢህአዴግ ከተቆጣጠራት ጊዜ ጀምሮ ማለትም እ.ኤ.አ ከ1991 ዓ.ም ሐገሪቷንና ህዝቧን በመሳሪያ አግቶ በዘር በሃይማኖት ከፋፍለው  እንዲሁም ከቁጥጥር ውጪ  በሆነ የሰብአዊ መብት እረገጣ እና የኢኮኖሚ ቀውስ አድርሰውባታል አሁንም እያደረሱባትም ይገኛሉ።
 
ዝባችንም ከተወለደበት እና ካደገበት ቀዬው ሰላምን ፍለጋና ኑሮውን ለመምራት ሲል እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ ማያውቅበት ሐገር ለመኖር ሲሰደድ፤ በየበረሐው ሲደበደብ፤ እንዲሁም ሲገደል እና በህይወት እያለ ሰውነቱ እየተቀደደ የውስጥ አካሉ  ሲሸጥ  እያየንና እየሰማንም ነው።
 
ይህ ሁሉ በደል እና ስቃይ በህዝባችን እየደረሰ ባለበት ጊዜ ስልጣኑን ተቆጣጥረው ያሉት የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት እኛ እናውቅላችኋለን፤ እናስተዳድራችኋለን በማለት የባለ እራዩን የዘረኛውንና የገንጣዩን መለስ ዜናዊ አመራር  አላማ ለማስፈጸም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን በማለት በህግ ላይ ህግ በማውጣት ህዝቡ ቀና ብሎ  እንዳያያቸው በተበላሸና በከረፋ የህግ የበላይነት
ስም ህዝቡን በማፈን፤ ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ነገር ግን በአሸባሪነት ስም የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የእምነት ስርዓታችንንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን ምርጫ እምነታችን በሚፈቅደው መንገድ ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎችን በአሸባሪነት በመወንጀልና በመክሰስ እንዲሁም በዋልድባ ገዳም አባቶቻችንን በማሳደድና በመዝረፍ ሲያሰቃዩ  እነሱ ግን  በቅሌትና በሙስና የሀገሪቷን ሃብት እና ንብረት  ለግል ጥቅማቸው በማዋል እንዲሁም የሀገሪቷን ጥሬ ሃብትና ንብረት ወደ ውጪ በማሽሽ  በውጪ በሚገኙ ዘመዶቻቸው ስምና የነሱ ተባባሪ ወዳጅ መንግስታት ሐገሮች ባንክ ውስጥ በማስቀመጥ ሐገራችንን ኢትዮጵያን  በአለም ታይቶ በማይታወቅ የኑሮ እድገት  የኋልዮሽ እሽቅድምድም ውስጥ በማስገባት ለከፋ ችግር አጋልጠዋታል።
እውነት አሁን ወያኔ/ኢህአዴግ ሀገራችንን ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ አመታት ከግብረ አበሮቹና ከጀሌዎቹ ጋር በመተባበር  ሲያደማትና ሲበዘብዛት  ቆይቶ አሁን  በሙስና ቅሌት ያዝኳቸው በማለት ግብረ አበሮቹን በገሃድ ያጋለጠበትና አሳዶ  ወደ ወይኒ የወረወረበትን  ምክንያት እውነት ለሐገራች ተቆርቋሪነቱን ለማሳየት ይሆን ? ወይስ የማናውቀው መፍረክረክ ተፈጠረባቸው ? ይህንን ጥያቄ  እሱ እራሱ ባለጉዳዩ ይመልሰው ወይም እነሱ እንደ ጀመሩት እራስ በራሳቸው ተበላልተው ያልቁልናል ብለን ዝም ብለን እንመልከት?
እኔ እንደማስበው ወያኔ/ኢህአዴግ በአሁን ሰአት እያረጀ የመጣ ትልቅ የግራር ዛፍ ነው ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም ስርአቱ ውስጥ የመፍረክረክ ሁኔታና የመበስበስ ባህሪይ ማሳየቱ ከውስጡ ያሉት ሞተር የነበሩት እራሳቸውን ወደ ማግለል ደረጃ ላይ ደርሰው እያየናቸው ነው ስለዚህ የበሰበሰውን ስርአት በደንብ እንዲበሰብስ አድርጎ የመጣል ሐላፊነት ያለብን ይመስለኛል ለዛም ዋና መፍትሄ የሚሆነው ስርአቱን ፊት ለፊት እና በተለያየ መንገድ የሚታገሉትን ድርጅቶችን ሆነ ግለሰቦችን አንድ በማድረግ ልዩ ነታችንን ትተን በአንድነት መፋለም ያስፈልጋል ብዬ አምናለው ያለ በለዚያ ስርአቱ በሰበሰ አረጀ እራሱ ይወድቃል ብለን ቁጭ ብለን የምንጠብቅ ከሆነ እራሳችን በስብሰን ከዚህ በበለጠ በከፋ  አገዛዝ እንደምንገዛ ጥርጥር የለኝም።
                                 
መልክት ለወያኔ ደጋፊዎች
 
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የወያኔን ስርአት የምትደግፉ ወገኑቻችን  በአሁን ሰአት አለማችን በቴክኖሎጂ አድጋ  አንድ ሆናለች  የትም ሆናችሁ የትም ስለ ሃገራችሁም ሆነ ስለምትፈልጉት ነገር ቤት ቁጭ ብላችሁ ማየትም መስማትም ትችላላችሁ  ስለዚህ ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ሐገራችን ኢትዮጵያ ከየት ወዴት እንደምትሄድ እና በስርአቱ ውስጥ ምን ያህል እንዝላልነትና ሐላፊነት የጎደለው አገዛዝ እንዳለ ለናተም የተደበቀ ነገር ያለ አይመስለኝም እድሜ ለቴክኖሎጂ የለፈውን እንተወውና አሁን በቅርቡም በመገናኛ ቦዙሃን እንደሚደመጠው በሐገራች ላይ ምን ያህል ምዝበራና ዘረፋ እየተካሄደባትና ኢ ሰብአዊ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየደረሰ እንደሆን ለናተ መንገር  ለቀባሪው አረዱት ማለት ነው  ስለዚህ ጠንቅቃችሁ ታቁታላችሁ ። እግዚአብሄር በሰጣችሁ ጭንቅላት በመጠቀም ወደ ሰውኛ አስተሳሰብ ተመልሳችሁ ጊዜው  ሳይረፍድ ከጭቁኑ ኢትዮጵያዊ ጋር ጎን ለጎን በመቆም በአፓርታይድ አገዛዝ ስር የወደቀችውን ሐገራችንን ነጻ ለማውጣት እንታገል   በማለት ወንድማዊ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። 
መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለግንዛቤ ሰሞኑን ከወጡት ዜናዎች መካከል በጥቂቱ 
ቸር ያሰማን
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች
 ድል ለኢትዮጵያ ሞት ለወያኔ
 
 
 

Tuesday, May 14, 2013

ታላቅ ህዝባዊ ጥሪ በሰማያዊ ፓርቲ



ማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 2005 ዓም የአፍሪካ ህብረት የወርቅኢዮቤልዮ በአል በሚከበርበት ሰአት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል:: ድርጅቱ ይህንን ህዝባዊ ጥሪ ያቀረበበት ዋናው ምክንያት ከዚህ ቀደም ለመንግስት የተለያዩ ጥያቄዎቹን በተደጋጋሚ ያቀረበ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ መልስ ባለማግኘቱ አጋጣሚውን በመጠቀም ድምጹን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለማሰማት መሆኑን በመግለጫው አስፍሯል:: በተጨማሪም ዜጎች ህገመንግስቱ ያጎናፀፋቸው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ቢኖራቸውም፤ መንግስት በተደጋጋሚ የጅምላ ግድያ በመፈጸም ሃሳብን መግለጽ እና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዳይታሰብ ማድረጉ በመግለጫው አስቀምጧል:: 

ድርጅቱ ባቀረበው ጥያቄ ከጠቀሳቸው ነጥቦች መካከል ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ነገር ግን በአሸባሪነት ስም የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና፣ አባላት እንዲፈቱ ፤ የዜጎች ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ በታጠቁ ኃይሎች በማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፅሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስት ድጋፍ እንዲደረግላቸው ፤ መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን ምርጫ እምነታችን በሚፈቅደው መንገድ ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎችን በአሸባሪነት በመወንጀልና በመክሰስ ማሰሩንና በግፍ ማንገላታቱን እንዲያቆምና ያነሷቸውንም ጥያቄዎች በሠላማዊ መንገድ ፍትህ እንዲሰጣቸው ፤ እንዲሁም መንግስት የኑሮ ዉድነትን ፣ የሥራዓጥነትንና፣ በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን ትክክለኛ መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ የሚሉት ይገኙበታል:: 

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ህዝብ በኢኮኖሚ በልፅጎና ሙሉ ነፃነቱ ተጠብቆለት የሚኖርባት ሃገር ኢትዮጵያን ለመመስረት ፣ በኢትዮጵያ ማንኛውም የህዝብ መብቶች በእኩልነት እንዲከበሩና ፣ ለሁሉም እኩል የሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በሃገራችን ኢትዮጵያ ለመገንባት በፅናት የሚታገል ፣ በወጣቶች የተመሰረተና የሚመራ ፣ ህዝባዊ ንቅናቄ ነው:: 

ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው የጠቀሳቸው አራት ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ መልስ እንዲያገኙ ከሚታገልላቸው ዋና ዋና የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ውስጥ የሚገኙና ዘረኛው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በዘረጋው የጭቆናና የግፍ መረብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በግዴለሽነት በግልፅ በአደባባይ ከሚፈፅመው ስቃይ ፣ መከራና ፣ እንግልት ጥቂቶቹ በመሆናቸው ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበው ወቅታዊና ተገቢ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን ሙሉ ለሙሉ የተቀበለው መሆኑን በአፅንዎት ይገልፃል:: 

ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ህዝባዊ ጥሪ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ለማድረግ ቃል በመግባት ለተግባራዊነቱም በትጋት ከልብ የሚሰራ መሆኑን በጥብቅ ያረጋግጣል:: 

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ህዝባዊ በመሆኑ ፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥን የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው! 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ