Saturday, November 16, 2013

Crazy Photos Are Coming Out Of Saudi Arabia After Rain Leaves Capital Flooded Read more: http://www.businessinsider.com/ridayh-rain-floods-city-2013-11#ixzz2krEC7jrJ

Riyadh, the 5 million strong capital of Saudi Arabia, generally doesn't receive much rainfall over the year. One source says that, on average, just 0.2 inches of rain fall in November.
It's perhaps because of this that the city has been unable to handle around two hours of heavy rain today. Residents are in shock, with many Internet users are posting pictures of flooded streets.


Read more: http://www.businessinsider.com/ridayh-rain-floods-city-2013-11#ixzz2krESLFzf



View image on Twitter

Here are some images that appear to show the flooding:
View image on Twitter

View image on Twitter

View image on Twitter

View image on Twitter

Riyadh is now like the sea due to rain
View image on Twitter

View image on Twitter

Friday, November 15, 2013

Ethiopian police brutally beat, arrest demonstrators at the Saudi Embassy (Text+Video)

በሳውዲ ኢምባሲ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ፤ ከቀናት በፊት ከሳውዲ የተመለሰች ወጣት በሰልፉ ድብደባ ደርሶባታል
15 የፓርቲው አመራሮች ታስረዋል
አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – በቅርቡ የሳውዲ አረቢያ መንግስት በንጹሀን ኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸመውን ኢ-ሰብአዊና እንስሳዊና ድርጊት በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፤ ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ ተበተነ፡፡
ዛሬ አርብ፣ ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከአይቤክስ ሆቴል ፊለፊት በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ደጃፍ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ጋዜጠኞችና ከቀናት በፊት ከሳውዲ አረቢያ የተመለሱ ዜጎች የተሳተፉበት ነበር፡፡ ሆኖም ሰልፉ ለጥቂት ደቂቃዎች ከተካሄደ በኋላ ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን በወሰደው የሃይል እርምጃ በተወሰኑ ሰልፈኞች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ በስፍራው የተገኘው የአውራምባ ታይምስ ዘጋቢም የፖሊስ ዱላ ከመቅምስ አላመለጠም፡፡demo
ፖሊስ ክፉኛ ከደበደባቸው ሰልፈኞች መካከል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድጋፍ ባለፈው ረቡዕ ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎች ይገኙበታል፡፡ ከትናንት በስቲያ ወደ አገሯ መመለሷን ለአውራምባ ታይምስ የገለጸች አንድ ወጣት እንደገለጸችው ‹‹ሌሎች ያደረሱብ በደል አንሶ፤ በራሳችን ወገን በገዛ አገራችን እንዴት እንዲህ አይነት ድብደባ ይፈጸምብናል›› ብላለች፡፡
ሌላው ከሳውዲ የተመለሰ አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩሉ ‹‹እንኳን እዚህ እዛም የጭካኔ እርምጃቸውን ተቋቁመን በድፍረት ሰልፍ አካሂደናል፤ በአገራችን እንዴት ሰልፍ እንከላከላለን›› ሲል በግርምት ተናግሯል፡፡
ለአውራምባ ታይምስ ዘግይቶ በደረሰ መረጃ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ጨምሮ 15 አመራሮችና አባላት ከሰልፉ ጋር በተያያዘ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል ሰልፉ ፍቃድ ያልተሰጠው ህገወጥ ሰልፍ ነው ካሉ በኋላ ስለ ሰላማዊ ሰልፍ በተደነገገው አዋጅ ላይ ማንኛውም ሰልፍ ከእምነት ተቋማትና ኢምባሲዎች በ500 ሜትር ርቀት ላይ መካሄድ አለበት የሚለውን የአዋጁ ክፍል በመጣስ ህዝብና ህዝብ ሊያጋጩ የሚችሉ የጸረ-አረብ ስሜት የሚንጸባረቅባቸው ዘረኛ መፈክሮች በዚህ ህገወጥ ሰልፍ ሲስተጋቡ ፖሊስ ዝም ማለት አልነበረበትም፡፡ እርምጃውም ተገቢ ነበር ብለዋል፡፡
የፋሺሽት መፈክር አንግቦ በተጎሳቆሉ ዜጎች ስም የፖሊቲካ ትርፍ ለማግኘት መጣር ብሎም መንግስት በዜጎቹ ግዴለሽ እንደሆነ አስመስሎ ማቅረብ ኃላፊነት ይሰማኛል ከሚል የፖሊቲካ ድርጅት አይጠበቅም፤ ያሉት አቶ ሽመልስ ‹‹የሳውዲ መንግስት በአገሩ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት እርምጃ የመውሰድ ሉአላዊ መብት እንዳለው እንገነዘባለን፤ እኛ ደግሞ የሚመለሱ ዜጎቻችንን በአገራቸው አምራችና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በዘላቂነት ለማቋቋም በአገር ደረጃ ብሄራዊ ኮሚቴ አዋቅረን ስራ እየሰራን ነው፡፡›› ብለዋል


TPLF security attacks peaceful protesters at the Saudi Arabia embassy in Addis Ababa, Ethiopia


Today around 5:15 AM Ethiopia local time few protesters were out on the streets and we have witnessed federal police were attacking them. Among them there were old people. What’s even more heart breaking was the Saudi Embassy people were sitting on their roof tops and smiling when the TPLF federal police beat up their own people. The idea of coming together today was not about the current government. It’s about our people who are being brutalized in Saudi Arabia.

ዛሬ ማምሻውን ወያኔ እንደለመደው ያው "ሰልፉ ሌላ አላማ ነበረው!!" ብሎ ይወነጅላል በሽመልስ ከማል አንደበት:: ፖሊስ አሁንም ህዝቡን በማስፈራራት ላይ ነው ::ወሎ ሰፈር በሚገኘው ሳኡድኣረቢያ ኤምባሲ የተቃውሞ ድምጾች ለማሰማት የወጡ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበዋል:: በርካቶች ታስረዋል:: ሰልፉም በፖሊስ ቆመጥ እና አላስፈላጊ እርምጃ ተበትኗል::


Image

Image

Image

Image

Image

Image

Image

Image

Thursday, November 14, 2013

Protest at Saudi Arabia embassy Tamagne Beyene Nov 14,11.2013



አንድ አንዳርጋቸውን መግደል የነፃነቱን ትግል ማስቆም አይቻልም


የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ በርግዶ ገባ። ግንቦት ሰባትን በተመለከተ እቅዳችንን ልነግርህ ነው የመጣሁት ሲል ነገሩን ጀመረ።

እሺ ምንድ ነው እቅዱ ?

የአንዳርጋቸውን፤ ጓደኞቹንና አንዳንድ የኤርትራ ባለስልጣኖችን ለመግደል ዝግጅቱ ተጠናቋል። ኤርትራ ድረስ ሂዶ “መስዋዕትነት” ለመክፈል የሚችል አንድ ሰው አግኝተን ልከናል። ግዳጁን ፈፅሞ ሲመጣ አንዳንድ ነገሮች እናደርግለታል። እርሱም ተስማምቷል።ጥቅምት 28 የምስራች እንሰማለን። እስከዛው ግን ፍተሻዎች እንዲጠናከሩ ወጥተህ ተናገር።

ሰውየው “already” ተልኳል ማለት ነው ?

አዎን ከተላከ አምስት ወር ሁኖታል።

የሚሳካ ይምስላችኋል ?

አዎን . . በሚገባ! እኛ ሞክረነዉ ያልተሳካ ምን ነገር አለ? . . . ጌታዬ። በደንብ ነው የሚሳካው። ዛሬ እዚህ መጥቼ የማሳስብዎት ይህ ጉዳይ ሲታቀድም ሲፈጸምም አልሰማሁም ብለዉ እንደ እግር ኳሱ እንዳያሳፍሩን ብዬ ነዉ።

አይዟችሁ እናንተም አታሳፍሩኝም እኔም አላሳፍራችሁም። እሺ ሰምቼያለሁ። አለ “አማኝ ነኝ ባዩ” ደሳለኝ ኃ/ማሪያም ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ የአገሪቷ ምርጥ ልጆች ደማቸው በከንቱ እንዲፈስ እየተስማማ።

“ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ንጣት በገደለው “ሲሉ አመሳጠሩ የሃገራችን ሰዎች።

“ቀፎው ነው እንጂ ሲም ካርዱ ከእኛ ነው” የተባለለትና እና በነፍሰ ገዳዮቹ ወንበር የተቀመጠውን የደሳለኝ ኃ/ማሪያምን ጉዳይ በዚህ እናበቃለን።

ህወሃቶች የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈሱ የኖሩ ነብሰ ገዳዮች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አሁንም ክብሬንና ነፃነቴን የሚሉ ዜጎችን ይዘው ደብዛቸውን ለማጥፋት ብዙ ዓይንና ብዙ ጆሮዎችን በየቦታው አቁመናል እያሉ ያቅራራሉ። ይሄን ሁሉ ዓይንና ጆሮ ይዘንስ የሚያሸንፈን ማን ነው ? ሲሉም ይደመጣሉ። እነርሱ እንደሚሉት ዓይኖቻቸው ማየት፤ጆሮዎቻቸውም መስማት የሚችሉ አይደሉም። የህወሃት ዓይኖች ማየት የተሳናቸው እውራን፤ ጆሮዎቻቸውም ማድመጥ የማያውቁ ደናቁርት እንደሆኑ የታወቀ ነው። ህወሃቶች ይህን የማይሰማ ጆሮና ፤ማየት የተሳነውን ዓይን ይዘው እየተደናበሩ፤ ይህን ለመደበቅ ህይዎት ያላቸው መስለው ይታያሉ። አዎን ህወሃቶች ጭው ባለ በርሃ ላይ ብቻችሁን እንደቆማችሁ እወቁ። የሚነገረው እና የሚሆነው በሙሉ ስለተሰወረባችሁ በብዙ ሚሊየኖች መሃከል ብቻችሁን እርቃናችሁን ቀርታችኋል። ብዙ ሚሊዮን ዓይኖች እና ጆሮዎች በእናንተ ላይ መተከላቸውን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄ እንደ ህወሃት-ኢህአዴግ ጆሮዉ የተደፈነና አይኑ የታወረ ድርጅት አይደለም። ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚያይ ዓይን፤ የሚሰማ ጆሮና የሚያስተዉል ልቦና ያለው ህያው ንቅናቄ ነው። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ ግልፅ ነው። ነፃነት ! ፍትህ ! እና ዲሞክራሲ ! ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ እንዲያገኙ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተነስተናል ጉዞ ጀምረናል፤ ሺ አንድአርጋቸውን ፈጥረናል። ልብ ይበሉ ነፃነት ፍትህ እና ዴሞክራሲ ለሰው ልጆች የተሰጡ ክቡር ስጦታዎች ናቸው። ህወሃት እነዚህን ክቡር ስጦታዎች ከዜጎች ላይ ነጥቆና ህዝብን ረግጦ መቀጠል የለበትም። ህወሃት የዜጎችን ነፃነት ነጥቆ ፤ ፍትህን አጓድሎና ህዝብን ረግጦ እንደከዚህ በፊቱ በሠላም እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ተሳስቷል። በህወሃት ቅዥት አገራችን ተጎድታለች። ህዝቧም ለማያባራ ጉስቁልናና ውርደት ተዳርጓል። ብዙዎችም አገር አልባ ሁነው በየሰው አገሩ መፃተኛ ሁነው እንዲኖሩ ተገደዋል። በእኛ እምነት በአገራችን ላይ እየደረሰ ላለው ውርደት በዋናነት ተጠያቂው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ዋነኛው ጠላት ነው የምንለውም ዜጎቻችንን ለጉስቁልናና ለውርደት ስላደረገም ጭምር ነው። እኛ ይህን አገር በቀል ጠላት ከሥሩ ነቅለን ለመጣል ተነስተናል። ከዚህ ትግል የሚያቆመን ምንም ዓይነት ምዳራዊ ኃይል እንደሌለ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን። ህወሃቶች አንገታችንን አስደፍተው አይገዙንም። ጥቁር ደም ያፈራቻቸው የቁርጥ ቀን ውድ ልጆቿ የነጻነት ታሪክ በጥቁር ቀለም ይጻፍ ዘንድ የሚያደርጉትን ሀገርን የማዳን ጥሪ እንዲህ በቀላሉ መግታት ከቶ አይቻልም። ወያኔዎች አትደናበሩ! ጋሬጣውን መለየትን ለእኛ ተውሉን።

ታዲያ ይህን ንቅናቄ አንድ አንዳርጋቸውን በመግደል ማስቆም የሚቻል የሚመስለው ጅላ ጅል ቡድን አገሪቷን እየገዛ በመሆኑ ተቆጭተናል። አንዳርጋቸውን መግደል ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊ አንዳርጋቸውን መፍጠርና ትግሉንም የሚያጠናክር እና የሚያፋፍም መሆኑን አልተረዱም። የኢትዮጵያ ህዝብ የእምቢተኝነት፣ የአልገዛም፣ የነጻነት ታሪክን ለማስከበር መሰዋእትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆንን ከአንዳርጋቸው ከተማረ ቆይቷል። መቆጨታችን ግን እንዲሁ በቁጭት ብቻ የሚቀር የሚመስለው ካለም ድግሞ ተሳስቷል። ይሄ ቁጭት በየደረሱበት የንፁሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ አገር መምራት የሚመስላቸውን ህውሃቶች ከተንጠለጠሉበት ዙፋን አውርደን በልካቸውና በአቅማቸው እንዲኖሩ ለማድረግ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ያደርገናል። ህወሃት ውስጥ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ግለሰብ ካለ አሁን ቆም ብሎ እንዲያስብ እናሳስበዋለን። ጀንበር ሳትጠፋባችሁ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገውን ትግል ተቀላቀሉ። እርግጥ ነው ለነፃነት የሚደረገው ትግል በየመስኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ህወሃትም የእጁን እንደሚያገኝ ምንም ዓይነት ብዥታ እንዳይኖራችሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን።

ግንቦት ሰባት የቆመበት መሠረት ፅኑ፤ ዓላማውም ህዝባዊ ነው። በዚህ በፀና መሠረት ላይ ህዝባዊውን ዓላማ አንግበው የተነሱ ሚሊዮኖች አሉ። እነዚህ ሚሊየኖች የሌሉበት ሥፍራ የለም። ከቤተ-መንግስት እስከ እርሻ ማሳ፤ ከስለላ ተቋማት እስከ አገሪቷ መከላከያ ኃይል፤ ከሃይማኖት ተቋማት እስከ መንግስት መሥሪያ ቤቶች፤ ከዘመናዊ ትምህር ተቋማት እስከ ተከበሩ ገዳማት ድርስ ለክብራቸው ዘብ የቆሙ ሚሊየኖች አሉ። እነዚህ ሚሊኖች የቆሙት መረቅ የበዛበትን ወጥ ዓላማ አድርገው ሳይሆን በፀናው መሠረት ላይ ለተተከለው ክቡር ዓላማ ነው። ይህ ክቡር ዓላማ ነፃነት፤ ፍትህ ፤እኩልነት እና የህግ የበላይነት እንጂ ሌላ አይደለም። እነዚህ ሚሊየኖች አትኩረው ማየት የሚችሉ ድንቅ ዓይኖች ያሏቸው፤ አጥርተው ማድመጥ የሚችሉ ክቡራን ጆሮዎች ያሏቸው መሆናቸውን ህወሃቶች እንዲያውቁት እንወዳለን።

ግንቦት ሰባት ማንንም ፍርሃት እና ድንጋጤ ውስጥ መክተት አይፈልግም።እንዲያውም ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚታገለው ዜጎች ሁሉ ከፍርሃት ነፃ ሁነው በደስታ እንዲኖሩ ለማስቻል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ካሁን ወዲያ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዓይንና ጆሮ የሚያመልጥ አንዳችም ነገር እንደማይኖር የሚያሳድደን ቡድን እንዲያውቀው እንፈልጋለን። ዓይንና ጆሯችን በሁሉም ሥፍራ በንቃትና በጥንቃቄ ነገሮችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ህወሃቶች ከትዕቢታችሁ ብዛት የተነሳ የህዝቡን ምክር መናቃችሁን እናውቃለን።የወገኖቻችንንም ድምፅ ጫጫታ እያላችሁ እንደምትሳለቁም እናውቃለን። ይሄ እንደማይጠቅማችሁ ብዙ ግዜ ነግረናችኋል። የህዝቡን ምክር ስሙ፤ የወገኖቻችሁንም ድምፅ አድምጡ ብንላችሁ በእምቢታችሁ ፀንታችኋል። ልቦናችሁ እንደ ፈርዖን ልብ ደንድኗል።ልብ ማደንደን እንኳን እናንተን ለመሠለ ደካማ ፍጡር ይቅርና በዘመኑ እኔ “እምላክ” ነኝ እሰከ ማለት ለደረሰው ለፈርዖንም አልበጀም። እንዲህ ዓይነት የልብ ድንዛዜ እናንተ በዚያ ጠባብ ዓላማችሁ ጣልነው ለምትሉት ለመንግስቱ ኃ/ማሪያምም አልረባውም። አሁንም የእኛ ምክር አጭርና ግልፅ ነው። የመዘዛችሁትን የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው መልሱ። የዘጋችሁትን በር ክፈቱ። የነጠቃችሁትን የዜጎች ነፃነት መልሱ። በህዝቡ ላይ ያወረዳችሁትን የፍርሃት ድባብ አስወግዱ። የተከላችሁትን የዘረኝነት እሾህ ንቀሉ። ከእውነት ጋርም ታረቁ። እንዲህ ብታደርጉ የዚያችን አገር በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን የሚበላችሁን እሳት ማጥፋት አይቻላችሁም። መጥተናል!!

እኛም ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክረናል። የትግል ዘርፋችን ሰፍቷል። በሁሉም አቅጣጫ መረባችን ተዘርግቷል። ከዚህ መረብ የትም አታመልጡም። ማምለጫ መንገዳችሁ አንድ ብቻ ነው። እርሱም የህዝቡን ድምፅ መስማት፤ እውነተኛ መልስ መስጠት እና ለህግ ተገዢ መሆን። አበቃን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

Tuesday, November 12, 2013

በወያኔ የደህንነት መስሪያ ቤት የታቀደው የግንቦት 7 አመራሮች ላይ ያልተሳካው የመግደል ሙከራ ፈጻሚው በምስል

እስክንድር አሰፋ
12.11.2013
ኖርዌ
በወያኔ የደህነት መስሪያ ቤት የታቀደው በግንቦት 7 አመራሮች ላይ የመግደል ሙከራ  ሊፈጽም አስቦ ሳይሳካለት የቀረው ተስፈኛ ሙልቀን መስፍን  የታቀደለትን ሽልማት እንዳይሸለም ያኮላሹበት  ለሐገራቸው ሲሎ እራሳቸውን መስዋትነት አድርገው  በሰጡት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የግንቦት 7 ንቅናቄና ሕዝባዊ ሐይሎች በቁጥጥር ስር የዋለው  የሴሜን ጎንደሩ  ጉብል ። ፕሮግራሙን ESAT ቁልጭ አድርጎ ስለተረከው ከታች ያለውን link በመክፈት ልትከታተሉት ትችላላችሁ በመጨረሻ ለማስተላለፍ የምፈልገው ነገር ቢኖር በስልጣን ላይ ያላችሁም እንዲሁም ማንኛውም የወያኔ ደጋፊም ሆንክ አሽከር ወይም አገርህን ለከርስህ መሙያ ብለህ  ለወራሪ ጠላት አሳልፈህ በመስጠትህም በማፈራረስህም ከነአስተዳዳሪዎችህ  የታሪክ ተወቃሹችናተጠያቂዎች ስለሆናችሁ እራሳችሁን አጥፉ ወይንም በመጣችሁበት መንገድ ሐገራችንን ጥላችሁ ውልቅ በሉልን  ያለበለዚያ የምትፈሩትና የምትሸበሩለት ጀግናው ብሶት የወለደው የግንቦት ሰባት ጦር ውስጣችሁ ስለላለ  ብታስቡበት ይሻላል   ።
 ልብ ያለው ልብ ይበል !!!    
    

                                             ሙልቀን መስፍን
                            

http://ethsat.com/video/esat-special-program-o-millenium-nov-11-messay/

                   

                                 http://ethsat.com/video/esat-news-analysis-12-november-2013/
                               
                                 

                                 

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን



በንቅናቄዓችን ፀሐፊ እና በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራር አባላት ላይ የተቃጣው ረዥም ጊዜ የወሰደ የግድያ ሴራ መክሸፉ አስደስቶናል። ይህ ሴራ የወያኔ የስለላና የግድያ ኃላፊዎች በሆኑት ጌታቸው አሰፋ እና ጸጋየ በርሄ የቅርብ ክትትል የተመራ፤ የአሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እውቅናና ይሁንታ የተሰጠው፤ ወያኔ ከፍ ያለ ተስፋ የጣለበት ሴራ ነበር።

“ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም” የተሰኘው ይህ በወያኔ የመጨረሻ ከፍተኛው አመራር የተመራው ሴራ ስለወያኔ ውስጣዊ አደረጃጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ሰጥቶናል። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ሹማምንት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት፤ ከአመት በኋላ ስለሚደረገው ምርጫ ውጤት፤ ለሰላዮቻቸው ስለሚሰጡት ጉርሻ መጠን፤ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተስፋ ከጣሉበት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳያቸው ጋር ካደረጉት የስልክ ንግግሮች ማድመጥ ይቻላል። ይህ ለበርካታ ጥናቶች በግብዓትነት ሊውል የሚችለውን በድምሩ ከስምንት ሰዓታት በላይ የሚፈጀው የስልክ ንግግር ቅጂ በሕዝባዊ ኃይሉ የመረጃ ክፍል አማካይነት ለሕዝብ በኢንተርኔት በነፃ ተለቋል። በአጋጣሚውም የወያኔ ገበና ተጋልጧል።
በአንፃሩ ደግሞ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተደራጀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም ምን ያህል ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳ ተጨባጭ ማስረጃ ሆኗል። ይህ ለነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ የስነልቦና ብርታት የሚሰጥ ነገር ሆኖ ተገኝቷል።
በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተቃጣበትን ጥቃት ከማክሸፍ በተጨማሪ የወያኔን ገበና ማጋለጥ በመቻሉ የመጀመሪያው ሁነኛ ድል ተቀዳጅቷል።
ግንቦት 7 : የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” አፕሬሽንን ላከሸፉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት ይገልፃል። ለወደፊቱም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊደርሱ የሚችሉ መሆኑን በመገንዘብ የመከላከል ብሎም የማጥቃት ኃይሉን እንዲያጠናክር ይመክራል።
የንቅናቀዓችን እና የሕዝባዊ ኃይሉ አመራርና አባላት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ናቸው። “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ትግላችን ይገታ ነበር ማለት አይደለም። ትግላችን መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። ጓዶች ሲወድቁ ሌሎች ሺዎች አርማቸውን አንስተው ትግሉን ይቀጥላሉ።
ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋትነት ከፍለን ወያኔን ከሥልጣን አስወግደን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሆነባት ኢትዮጵያ እንደምትኖረን እርግጠኞች ነኝ።

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን።

ድል ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን

በንቅናቄዓችን ፀሐፊ እና በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራር አባላት ላይ የተቃጣው ረዥም ጊዜ የወሰደ የግድያ ሴራ መክሸፉ አስደስቶናል። ይህ ሴራ የወያኔ የስለላና የግድያ ኃላፊዎች በሆኑት ጌታቸው አሰፋ እና ጸጋየ በርሄ የቅርብ ክትትል የተመራ፤ የአሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እውቅናና ይሁንታ የተሰጠው፤ ወያኔ ከፍ ያለ ተስፋ የጣለበት ሴራ ነበር።

“ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም” የተሰኘው ይህ በወያኔ የመጨረሻ ከፍተኛው አመራር የተመራው ሴራ ስለወያኔ ውስጣዊ አደረጃጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ሰጥቶናል። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ሹማምንት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት፤ ከአመት በኋላ ስለሚደረገው ምርጫ ውጤት፤ ለሰላዮቻቸው ስለሚሰጡት ጉርሻ መጠን፤ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተስፋ ከጣሉበት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳያቸው ጋር ካደረጉት የስልክ ንግግሮች ማድመጥ ይቻላል። ይህ ለበርካታ ጥናቶች በግብዓትነት ሊውል የሚችለውን በድምሩ ከስምንት ሰዓታት በላይ የሚፈጀው የስልክ ንግግር ቅጂ በሕዝባዊ ኃይሉ የመረጃ ክፍል አማካይነት ለሕዝብ በኢንተርኔት በነፃ ተለቋል። በአጋጣሚውም የወያኔ ገበና ተጋልጧል።
በአንፃሩ ደግሞ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተደራጀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም ምን ያህል ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳ ተጨባጭ ማስረጃ ሆኗል። ይህ ለነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ የስነልቦና ብርታት የሚሰጥ ነገር ሆኖ ተገኝቷል።
በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተቃጣበትን ጥቃት ከማክሸፍ በተጨማሪ የወያኔን ገበና ማጋለጥ በመቻሉ የመጀመሪያው ሁነኛ ድል ተቀዳጅቷል።
ግንቦት 7 : የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” አፕሬሽንን ላከሸፉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት ይገልፃል። ለወደፊቱም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊደርሱ የሚችሉ መሆኑን በመገንዘብ የመከላከል ብሎም የማጥቃት ኃይሉን እንዲያጠናክር ይመክራል።
የንቅናቀዓችን እና የሕዝባዊ ኃይሉ አመራርና አባላት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ናቸው። “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ትግላችን ይገታ ነበር ማለት አይደለም። ትግላችን መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። ጓዶች ሲወድቁ ሌሎች ሺዎች አርማቸውን አንስተው ትግሉን ይቀጥላሉ።
ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋትነት ከፍለን ወያኔን ከሥልጣን አስወግደን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሆነባት ኢትዮጵያ እንደምትኖረን እርግጠኞች ነኝ።

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን።

ድል ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!