Tuesday, April 29, 2014

የማያዩ የማያነቡ የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ መድረክ ተዋናዮች (ሚሚ፤ መሠረት እና ፀጋሉል) !

        April 29,2014

የማያዩ የማያነቡ የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ መድረክ ተዋናዮች (ሚሚ፤ መሠረት እና ፀጋሉል) ለውንጀለ የሰላ አእምሮዋቸውን በዕለተ ሰንበት አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ለመንግስትና ገዢው ፓርቲ ቅረብ በሆኑ በመሶቦ እንዲሁም በብረታ ብረትና ኢኒጂነሪንግ ሰፖንሰርነት ለስድብ ሲጠቀሙበት ውለዋል፡፡ ከአንድ ሰዓት በላይ የፈጀ ፕሮግራም አይረባም ከንቱ ባሉት ፅሁፍ ላይ እና ገና ለገና ለምን እንዴት እንደታሰሩ በይፋ ባልታወቀ ዞን ዘጠኝ በሚባል በሚታወቁ የድህረ ገፅ ጦማሪዎች ላይ አባክነዋል፡፡ ለነገሩ ሙሉ ለሙሉ የባከነን ሬዲዮ ጣቢያ አንድ ሰዓት አባከነ ሊባል አይችለም፡፡

የተከበነሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
በመጀመሪያ ሰማችን ለመተነሳ የሚሉ ሰዎች የሰው ሰም እያነሱ አስተያየት መስጠት ለነሱ የተሰጠ መብት አሰመስለው ያዩታል፡፡ በእኔ አምነት በሰዎች ላይ እምነት ለመጣል እና ላለመጣል በማንም ሰው ላይ መብት አለኝ፡፡ ሚሚ እውነት እውነት እልሻለሁ እኔ ያለኝ ግምገማ እምነት እንደማይጣልብሽ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን የሚያምንሽ የለም ማለት አይደለም፡፡ የሚያምን ብቻ አይደለም የሚተማመኑብሽ እንደ መሠረትና ፀጋሉል ያሉ የመድረክ አጫፋሪዎች አሉሽ፡፡ እስኪ እነዚህ ሰዎች የኢቲቪን የቀለም አብዮት ዘጋቢ በመሪ ተዋናይነት የተሳተፍሽበትን ፊልም “አላየሁም” ስትይ ምን አለ ካላየሽው አይተሽው እንወያየ ለማለት ድፍረት ቢኖራቸው፡፡ 

አንቺስ ቢሆን እንደፈለግሽ ለመዘወር ካልሆነ “ለነገሩ አላነበብኩት” ያለውን ፅሁፍ ሊተች የሚገባን ሰው አሰራ አምሰት ደቂቃ የማይፈጅ ሁለት ገፅ ፅሁፍ አንዲያነብ ፀጋሉልን ብታስታውሸው፡፡ ለዚህ ነው የማያዩም የማያነቡም የጋዜጠኛ ክብ ጠረጴዛ ታዳሚዎች ልላችሁ የተገደድኩት፡፡ መሠረት (አታላይ ነው ያሉኝ መሰለኝ ያባቱን ስም)፡፡ ለነገሩ ለውይይት አይመጥንም ባለው ፅሁፍ ላይ ይህን ያህል ሰዓት ለመጎለት ክፍያው ስንት ነው ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን፡፡ እነዚህን ሰዎች በትክክል ሊገመግም የሚፈልግ ሰው ፅሁፌን አንብቦ በእርግጥ እምነት የሚጣልባቸው ወይም የማይጣልባቸው እንደሆነ ሊረዳ ይችላል፡፡



የእኔን ትክክለኛ አቋም ለመረዳት የሚፈልግ ሰው ካለ የፅሁፌን መደምደሚያ ማንበብ ጥሩ ነው፡፡ ለሚሚ እድምተኞች ሲባል ፅሁፉ ይህን ይላል “በአሁኑ ሰዓት ኢህአዴግ ከሚያቃዠው የቀለም አብዮት የሚገላግለውን መንገድ መምረጥ የግድ ይለዋል፡፡ አማራጭ አለን የሚሉ ፓርቲዎችም እነዚህን ወሳኝ እርምጃዎች በክብር ለመቀበል መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ዓይነት የሚመጣ ምንም ዓይነት ዝቅተኛ ውጤት ወደ ጎዳና ነውጥ ሳይሆን ችግርን መርምሮ ወደተሻለ ደረጃ ለመሸጋገር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት መዘጋጀት ነው፡፡ ይህችን ሀገር ከሶስተኛ አብዮት ለመጠበቅ ለሁሉም ልብና ልቦና ይሰጠው እላለሁ፡፡”

ፀጋሉል ያለነበበውን ፅሁፍ መሰረት አድርጎ ከእንግዲህ “በሀገር ጉዳይ ላይ ተለያይተናል” ብሎዋል፡፡ ላንተ ሀገር ማለት ምን እንደሆነ ስንስማማ ነው በመጀመሪያ መለያየት የሚባል የሚኖረው፡፡ በመጀመሪያ መች ተስማምተን ለመለያየት በቃን ጎበዝ፡፡ ሚሚ ደፋሯም “በህቡ መደራጀት ወንጀል ነው፡፡ ዲሞክራሲ ሰርዓት ባለበት ሀገር” ብላ በድጋሚ ልትሳለቅብን ትፈልጋለች፡፡ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር የለም፡፡ እኛ አሁን የምንፅፈው ለሰላማዊ ትግል የሚከፈል ዋጋ ነብስ ከሆነም ለመክፈል ስለወሰንን ነው፡፡ እነ ጋንዲ ዲሞክራሲ ስርዓት ስለነበር አይደለም በይፋ ስላማዊ ትግል የተከተሉት፡፡
ስላማዊ ትግል … በአጠቃላይ ትግል የሚባል ነገር ያለው … ዲሞክራሲ በሌለባቸው ሀገሮች ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያችን፡፡ ዲሞክራሲ ላለመኖሩ አንድ ምሳሌ ከሚሚ ጓዳ ማግኘት ከባድ አይደለም ለምሳሌ አስር ጊዜ የፖሊስ ምንጮቼ የምትይው ማን ነሽ እና ነው አንቺ በግል መረጃ የምታገኝው፡፡ ሌላው ይህ ምንጭ አለው፡፡ መረጃ የመንፈግ እና ለሚፈልጉት መስጠት የኢ ዲሞክራሲያዊነት መገለጫ ነው፡፡ ምን አልባት የፖሊስ ምንጮችሽ መረጃ የሚሰጡሽ በዓይነት ወይም በጥሬ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀሽ ነው፡፡ ወይም ሬዲዮ ጣቢያ የፖሊስ/የደህንነት ነው፡፡ እንዲያም ቢሆን የምንፈራ እንዳይመስልሽ፡፡ ሰላማዊ ትግል ብለን ስንገባ ፍርሃት የምትባለዋን ነገር አሰወግደን መሆኑን እንዳትዘነጉት፡፡
የቀለም በይ የፍራፍሬ አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ሊመጣ ይችላል? መልሱ አዎ ነው፡፡ ገፊ ምክንያቶቹ በገፍ አሉ፡፡ ፅዋው ሞልቶዋል፡፡ መቼ ይፈሳል አብዮት በእቅድና በፕላን አይመጣም ሲመጣ ደንገተኛ ደራሽ ጎርፍ ነው፡፡ ጠራርጎ የሚወስድ፡፡ እኔ ግን ይህችን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ከአብዮት ይጠብቃት፣ አብዮት እንዲመጣ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ገዢዎችም ልብና ልቦና ይስጥልን እላለሁ፡፡
ይህ ሃሳብ የግርማ ነው ምንጬም ነፃ አሰተሳሰቤ እንጂ የፖሊስ ምንጭ አይደለም፡፡

No comments:

Post a Comment