Monday, November 19, 2012

በሃገራችን ውስጥ የፍትህና የእኩልነት መጓደል ያንገበገበው ጀግናው የኔሰው ገብሬ እራሱን በእሳት አቃጥሎ መስዋት ያደረገበትን አንደኛ አመት እና በምርጫ 97 ወቅት በአስከፊ ሁናቴ በኢህአዴግ መንግስት ለተጨፈጨፉት ወገኖቻችንን የመታሰቢያ ቀን በኖርዌይ ኦስሎ ተከብሮ ዋለ



 በዛሬው እለት እሁድ  ህዳር 9,2005 ዓም የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ. በኢትዮጵያ የፍትህና የእኩልነት መዛባት  ያንገበገበው ጀግና የየኔሰው ገብሬ እራሱን በእሳት አቃጥሎ ለተተኪው ትውልድ መስዋት ያደረገበትን  የአንደኛ አመት እና በምርጫ 97 ዓም ወቅት በአስከፊ ሁኔታ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን መታሰቢያ በማድረግ  ቀኑን ያከበረ ሲሆን  የድርጅቱም ሊቀ መንበር አቶ ዳዊት መኮንን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። እንዲሁም ከተጋባዥ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮቻቸውም በየተራ  መልእክት አስተላልፈዋል ፡ 

 በዝግጅቱም ላይ አርቲስት አቶ ዳምጠው አየለ እና አርቲስት አቶ እንዳለ ጌታነህ አነቃቂና ቀስቃች የሆኑ ዜማዎችን አቅርበዋል በየመሃሉም ግጥምና በምርጫ 97 ዓም ወቅት በኢህአዲግ መንግስት ሰለባ የሆኑትን ወገኖቻችንን የሚያሳይ በቪዲዮና በድምጽ የተቀረጸ ምስክርነት ቀርቧል።

 በዚያም ወቅት በፕሮግራሙ ላይ ታዳሚ የነበሩ ሰዎች  ይታይና ይሰማ በነበረው የሃዘንና የይድረሱልን እሮሮ ከፍተኛ የሃዘን ስሜት የተሰማቸውና አንዳንዶቹም ያለቅሱ ነበር። ሁኔታውም ሕዝቡን ያስቆጨ በመሆኑ በቀጣይነት ይህን መንግስት ከሐገራችን በቶሎ ለማስወገድና የህዝቡን ሰቆቃ ለማስቆም በመተባበር አንድ ሆነው ለመስራትና አዲስቷን ኢትዮጵያን ለመፍጠር  መክረው ዝግጅቱን በኖርዌይ ሰአት ቆጣጠር  በ16:00 ጀምረው  ከምሽቱ 18፡ 00 ሰአት በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቀዋል ።

ምስሉን ይመልከቱ   3 ክፍል ነው 

መምህር የኔሰው ገብሬ እራሱን መስዋት አድርጎ ያለፈበትን የአንድ አመት መታሰቢያ ቀን አከባበር በ ኦስሎ 18,11,2012 ክፍል አንድ




መምህር የኔሰው ገብሬ እራሱን መስዋት አድርጎ ያለፈበትን የአንድ አመት መታሰቢያ ቀን አከባበር በ ኦስሎ 18,11,2012 ክፍል  ሁለት



ክፍል ሦስት

መምህር የኔሰው ገብሬ እራሱን መስዋት አድርጎ ያለፈበትን የአንድ አመት መታሰቢያ ቀን አከባበር በ ኦስሎ 18,11,2012 ክፍል ሦስት



                                                                                                                    
                                                                                      በእስክንድር አሰፋ ማሞ
                                                                                            18,11, 2012
                                                                                                ኦስሎ

No comments:

Post a Comment