Wednesday, January 2, 2013

የአረና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በዶዘር ፈረሰ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 


ኢሳት ዜና:-በሁመራ የሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት በዶዘር እንዲፈርስ ከተደረገ በሁዋላ የድርጅቱ ጽህፈት ቤትም ተዘርፎአል። በተመሳሳይ መንገድም የድርጅቱ አባል የሆኑት የአቶ ገብረእግዚ ናዩ ቤት ያለምንም ማስጠንቀቂያ እንዲፈርስ ተደርጓል።
በተንቤን የድርጅቱ አባል የሆኑት አቶ ጸጋየም መታሰራቸው ታውቋል። በአቶ ገብሩ አስራት በሚመራው አረና ፓርቲ ላይ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የሚወስዱት እርምጃ እየከፋ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

    Ethiopia finds 10 guilty of terror charges


    ADDIS ABABA, Ethiopia (AP) — Ten men were found guilty Tuesday by an Ethiopian court of plotting terror attackswith Islamist extremist rebels from neighboring Somalia.

    Judge Bahiru Darecha said the group was making plans and getting supplies to attack political and economic targets in Ethiopia. Eleven men were originally charged with the terror-related crimes but the judge acquitted one person. Six of the men found guilty were charged in absentia. Sentencing will be carried out on Jan. 15.



    Prosecutors said the suspects, who include one Kenyan national, formed a cell that worked with Somalia's Islamist radicals, al-Shabab. Al-Shabab is affiliated with al-Qaida.
    The verdicts come amid signs of increasing militancy in the East African nation. Ethiopian troops moved into Somalia last year to fight al-Shabab.
    Among those convicted is a Kenyan national, Hassan Jarso. When first charged in May, Jarso pleaded guilty to the charges but protested the assertion that he is a senior leader of the group.
    "We did plan the attacks and to open the (training) camp but none of it was realized," Jarso had told the court.
    He added that he was waiting for money from al-Qaida agents to establish the camp and start a militant group, based in Ethiopia's Oromia region.
    The other three convicts denied the charges. They are all religious teachers. In their defense they alleged that they were beaten by police to confess and sign documents and that exhibits were planted in their houses.
    Ethiopia's late Prime Minister Meles Zenawi in April told parliament that militants had formed al-Qaida cells in the country's southern Arsi and Bale areas.
    Ethiopia's military campaign against militants in Somalia from 2006-2009 angered al-Shabab.
    There are signs of rising Islamist militancy in Ethiopia. In late April four demonstrators were killed in a clash, after security forces arrested a Muslim religious leader in the Oromia region.
    Ethiopia's Federal Ministry on May 3 issued a statement accusing an unnamed group of trying to declare jihad against the government and working to incite violence in a number of mosques across the country. The statement said a dozen suspects were recruited by the group from the country's Oromia, Tigray and Amhara regions to carry out illegal activities.
    The government also expelled two Arabs who flew in from the Middle East on May 4. The government said the pair went to a mosque and tried to incite violence.

    http://www.diretube.com/ethiopian-news/ethiopia-finds-10-guilty-of-terror-charges-video_d0b097ae7.html



    ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አወዛጋቢ መልሶችን ሰጡ


    ኢሳት ዜና:-አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት መልስ በርካታ አወዛጋቢ ነገሮችን ተናግረዋል።
    በኤርትራ ዙሪያ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለምልልሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተተቹት አቶ ሀይለማርያም በዛሬው ንግግራቸው በተተቹበት ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። አቶ ሀይለማርያም ” አስመራ እሄዳለሁ ያልኩት በየትኛውም ቦታ እንደራደራለን የሚለውን የመንግስት አቋም አጽንኦት ለመስጠት ነበር” ሲሉ  ተናግረዋል።
    ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አስመራ ድረስ በመሄድ ከኤርትራ ጋር ለመደራደር እንደሚፈልጉ  ከገለጹ፣ ለእኛ ለተቃዋሚዎችም ያለምንንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋጋር ቢሮውን ክፍት ያድርጉልን” ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
    አቶ ሀይለማርያም በቅርቡ  የተሾሙትን ሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች  በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም ሁለቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ህጋዊ ጠቅላይ ሚኒሰትሮች ሳይሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የሚሰሩ ናቸው በማለት አንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ መኖሩን እሳቸውም አቶ ደመቀ መኮንን መሆናቸውን ተናግረዋል።
    አቶ ሀይለማርያም አንድ ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ መኖሩን መናገራቸው በህወሀት እና በኦህዴድ ውስጥ ቀደም ብሎ የነበረው ስሜት ተመልሶ ሊፈጠር እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
    አቶ ሀይለማርያም በኢትዮጵያ የተፈጠረው የጤፍ እጥረት ጤፍ በልቶ የማያውቀው ህዝብ  ጤፍ መብላት በመጀመሩ ነው ብለዋል።
    አቶ መለስ ዜናዊ የስኳር ዋጋ የተወደደው አርሶ አደሩ ስኳር መብላት በመጀመሩ ነው በማለት መናገራቸው ይታወሳል።
    በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ እስረኛ እንደሌለም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
    ሙሎ ዜናውን ይመልከቱት

    Published on Jan 1, 2013
    http://www.ethsat.com - Ethiopian Satellite Television (ESAT)
    ESAT is the first independent Ethiopian Satellite Television service and Radio Station who broadcast to Ethiopia and the rest of the world

    Tuesday, January 1, 2013

    ለታሠሩ የሻማ ሥነ-ሥርዓት ዋይት ሃውስ ደጅ ላይ ተካሄደ

    በዋሽንግተን ዲሲና አባባቢዋ ያሉ የተወሰኑ ትውልደ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ዕሁድ ታኅሣስ 21 / 2005 ምሽት ላይ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል፡፡

    http://amharic.voanews.com/content/march-for-freedom-vigil-white-house/1575559.html

    በአዲሱ የአውሮፓዊያን ዓመት መባቻ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለኢትዮጵያ ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጡ ለማሳሰብና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለአግባብ ታስረዋል ያሏቸው የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ ነው የሻማው ዝግጅት የተካሄደው፡፡

    ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ሲሆን ጠሪው ማርች ፎር ፍሪደም የሚባለው ድርጅት ነው፡፡

    ድርጅቱ ቀደም ሲል በበተነው ጥሪ “ወገኖቻችን በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰው ልጅ እኩልነትና ለሰብዓዊ መብቶች፣ ለእምነት ነፃነት መከበር ስለቆሙና ስለጠየቁ ብቻ በገዛ ሃገራቸው ተወልደው ባደጉባት ምድር ላይ እንደጠላት ተፈርጀው ከያሉበት ከየቤታቸው እየተለቀሙ ወደእሥር ቤት ወደ እሥር ቤት ከመወርወራቸውም በላይ በሕሊና እሥረኞቹ ላይ እየደረሰ ያለው ጭካኔ የተሞላበት አረመኔአዊ ድብደባና የሥነ-ልቦና ጥቃት በእጅጉ አሣዝኖናል” ይላል፡፡

    ከአዘጋጆቹና ከተሣታፊዎቹ መካከል አንዳንዶቹ “በእሥር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ብቻቸውን እንዳልሆኑ ለማስታወስም የጠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

    ሥነ-ሥርዓቱ በፀሎትና የሕሊና እሣቤም የታጀበ ነበር፡፡

    የኢትዮጵያ መንግሥት በእሥር ቤት የሚገኙት ሰዎች የታሠሩት በእምነታቸው፣ ወይም በመናገራቸው ወይም በመፃፋቸው ምክንያት ሣይሆን በሽብር አድራጎት በመሣተፋቸው ወይም በማሴራቸው ነው ይላል፡፡

    ፀረ-ሽብር ሕጉንና ሥርዓቱን የሚተቹ የሃገር ውስጥ ተቃዋሚዎች እና ዓለምአቀፍ ተቋማት የኢ4ትዮጵያን መንግሥት በሰብዓዊ መብቶች አያያዞቹ በየወቅቱ ሲወቅሱና ሲያወግዙ ይሰማሉ፡፡

    ዘገባውን ያዳምጡ