Tuesday, October 30, 2018

የብልሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) የመጀመርያ የአውሮፓ ጉዞ ለምን ወደ ፈረንሳይ ሆነ?

ጉዳያችን/Gudayachn
ጥቅምት 20/2011 ዓም (ኦክቶበር 30/2018 ዓም)


የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን(Emmanuel Macron)እና 
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር)


ኢትዮጵያዊውን ዕውቅ ዲፕሎማት የቀረፀች ፈረንሳይ! 


በ1904 ዓም በቡልጋ ከአለቃ ሀብተወልድ ካብትነህ እና ከወይዘሮ ያደግድጉ ፍልፈሉ የተወለዱት የኢትዮጵያጵያው ስመ ጥር ዲፕሎማት አክሊሉ ሀብተወልድ  አዲስ አበባ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አማርኛ ጠንቅቀው ከተማሩ በኃላ ዘመናዊ ትምህርት ለሶስት ዓመት ዳግማዊ ምንሊክ ትምህርት ቤት እንደተማሩ እና በመቀጠል ወደ ግብፅ እስክንድርያ ከተማ የሚገኘው የፈረንሳይ ሊሴ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ታሪካቸው ያስረዳል።ከግብፅ  ለከፍተኛ ትምህርት ያመሩት ወደ ፈረንሳይ ታዋቂው ዩንቨርስቲ ሶቦርን (Sorbonne) ነበር ።በሶቦርን  ዩንቨርስቲ የንግድ ሕግ እና የፖለቲካ ሳይንስ ተምረው ሲጨርሱ ዘመኑ 1928 ዓም ጣልያን ኢትዮጵያን የወረረችበት ወቅት ነበር። 


የፈረንሳይ ትምህርት ውጤት ታላቁ ዲፕሎማት አክሊሉ ሀብተወልድ በፈረንሳይ ሀገር በድፕሎማትነት በመቀጠል በጀኔቭ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ የነበሩት የፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተከለ ማርያም ልዩ ረዳት በመሆን በጣልያን ወረራ ወቅት በያኔው የዓለም ማኅበር ፊት የነበረውን የዲፕሎማሲ ውግያ ከንጉሰ ነገስቱ ጋር በመሆን የተፋለሙ  አክሊሉ ሀብተ ወልድ የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ትምህርት ውጤት ናቸው።የአክሊሉ ሀብተወልድ በሃያኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያ በነበራት ዲፕሎማሲ አሻራ ከሱማሌ ድንበር እስከ ኤርትራ ውህደት፣ከጋምቤላ የድንበር ጉዳይ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ውስብስብ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እስከ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ (የከተማ ይፍሩ ጥረት ሳይዘነጋ) የአክሊሉ ሀብተወልድ ምክር ያላረፈበት ቦታ የለም።


የብልሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የመጀመርያ የአውሮፓ ጉዞ ለምን ወደ ፈረንሳይ ሆነ? 


ፈረንሳይ በዲፕሎማሲ ትምህርት ማዕከል መሆን የጀመረችው በ18ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ነበር።ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ሲነሳ የፈረንሳይ አስተዋፅኦ መዘንጋት አይቻልም።ስለ ዓለም አቀፍ ሕግ ሲነሳ ከአውሮፓ ተሃድሶ ጋር የሚነሳው የፈረንሳይን አስተዋፅኦ ቸል ማለት ይከብዳል።ኢትዮጵያ ከጣልያን ወረራ በፊት የትምህርት ሥርዓቷን በፈረንሳይኛ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች እንደነበሩ እና ጣልያን ከኢትዮጵያ መባረር ተከትሎ ኢትዮጵያ የገቡት እንግሊዞች እና በመቀጠልም የአሜሪካ ልዕለ ኃያልነት መጉላት እንግሊዝኛ ቦታውን እንዳስለቀቀው ይነገራል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴም የፈረንሳይኛ ተናጋሪም ጭምር ነበሩ። የጣልያንን ወረራ ተከትሎ በጀኔቭ ለዓለም ማኅበር (አሁን የተባበሩት መንግሥታት የተሰኘው) ፊት ቀርበው አቤቱታቸውን ሲጀምሩ  '' ንግግሬን በፈረንሳይኛ ባደርገው በወደድኩ ነበር።ሆኖም ግን ሃሳቤን በሚገባ የማብራራው አማርኛ ስለሆነ በእዚሁ ንግግሬን አደርጋለሁ'' በማለት የጀመሩት ታሪካዊ ንግግርን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።


የዘመናችን ብልሁ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ (ዶ/ር) የመጀመርያ የአውሮፓ ጉዞ ያደረጉት ወደ ፈረንሳይ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታሪክ አዋቂ ናቸው።የፈረንሳይ ስረ መሠረትነት፣ታሪካዊ እና ባህላዊ ዳራ ሁሉ ሳይማርካቸው አልቀረም።ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በኃላ ለፈረንሳይ የተሰጠው  ያልሞቀ እና ያልደመቀ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ፍትሓዊ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ልታገኝ የምትችላቸው በርካታ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የባሕላዊ ዕሴት አጠባበቅ ጥበቦች ሁሉ በሚገባ አለመቀሰማቸው ሳይቆጫቸው የቀረ አይመስልም። ጠቅላይ ሚኒስትር የፈረንሳይ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጥቅምት 19፣2011 ዓም  ሲጀምሩ በሶስት መልኮች ኢትዮጵያ  ከፈረንሳይ የምታገኛቸው ጉዳዮች ላይ ማረጋገጫ ማግኘታቸውን ከፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ጎን ለጎን ሆነው በአማርኛ ለዓለም አቀፍ ሚድያ ፓሪስ ላይ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።  እነርሱም በቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት፣የኢትዮጵያ ጦር ማዘመን እና የቦሌ አየር መንገድን በመቶ ሚልዮን ኢሮ ወጪ ማዘመን የሚሉት ይጠቀሳሉ።


ዶ/ር አብይ ልዩ ሰው የሚይደርጋቸው አንዱ መገለጫ ዲፕሎማስን በግልብ ግንኙነት ላይ በተመሰረተ መልክ ሳይሆን የሚመሩት ታሪካዊ ግንኙነትን መሰረት አድርገው ነው።ቅድምያ የሚሰጡትን ከማይሰጡት የመለየት አቅማቸው እጅግ ድንቅ ነው።በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሲያቀርቡ እና ሲቆጡ እንዲሁም የኢትዮጵያን ግንኙነት በእኩል ልበ ሙሉነት እና ኩሩነት ሲመሩት ያስደምማሉ።ይህ ሁሉ ደግሞ ከድንቅ ፈጠራ ጋር ታክሎበት መሆኑ ሰውየውን ግሩም ዲፕሎማት ያደርጋቸዋል።ይህ አገላለጥ ለአንዳንዶች የተጋነነ መስሏቸው ከሆነ እስካሁን ካዩት የበለጠ ወድፊት ስለሚያዩት ያኔ ይረዱታል።ስልጣን እንደያዙ በሰአታት ውስጥ  ከክልል ከተሞች ወደ ጅጅጋ የሄዱበት እና ሁሉንም የጎረቤት ሀገሮች በመጎብኘት የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ ያረጋጉበት መንገድ መመልከት፣ ለአመታት ፈገግታ የራቃቸውን የኤርትራ መሪ አቶ ኢሳያስ ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት የዕርቅ ሂደት፣አሜሪካንን ያህል ሃያል ሀገር ሄደው ፕሬዝዳንቱን ሳያገኙ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻቸውን በአሜሪካ አደባባይ አዘምረው የዋሽንግተን ከንቲባን አስደምመው እና የኢትዮጵያን ቀን በእየዓመቱ ለማክበር ቃል እንዲገቡ አድርገው ሹልክ ብለው ዋይት ሃውስን ቁልቁል እያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ጳጳሳት ይዘው ወደ ሀገራቸው እብስ ያሉበት መንገድ ሁሉ ድንቅ ዲፕሎማሲ፣ድንቅ የአፈፃፀም ችሎታ ነው። ማድነቅ እና ማሞገስ ካለብን ዓብይ በሕይወት እያለ አለማድነቅ እና አለማመስገን አለመታደል ነው።ይህ ብቻ አይደለም የተባበሩት አረብ ኤምሬት ልዑል በክረምቱ ወራት ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ከቦሌ አየር ማረፍያ የቦሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲያስጎበኙ እራሳቸው መኪናቸውን እያሽከረከሩ ያስጎበኙበት ምላሽ ልዑሉ ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሀገራቸው በተመሳሳይ መንገድ እየነዱ ከወሰዷቸው በኃላ የኢትዮጵያን የሰላም ሀገርነት የገለጡበት ድንቅ እኩል ምላሽ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ።


ዶ/ር አብይ ወደ ፈረንሳይ የመጀመርያ ጉዞ ሲያደርጉ ታሪካዊ ዳራውን እና መጪውን የፈረንሳይ አካሄድ በሚገባ አላዩትም ማለት አይቻልም። ፈረንሳይ በኢትዮጵያ ያለፈ የአርባ ዓመታት የፖለቲካ ሹክቻ ውስጥ እጇ አልተነከረም።በ1830 ዓም ከአጤ ምንሊክ አባት ከንጉስ ኃይለመለኮት ጋር ግንኙነት የጀመረችው ፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በይፋ የጀመረችው በ1897 ዓም በአፄ ምንሊክ ዘመነ መንግስት ነው።የፓርስን ከተማ ከደብረ ብርሃን ከተማ ጋር  ታሪካዊ ቁርኝት የፈጠረችው ፈረንሳይ፣ ለኢትዮጵያ ከሰባት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የመጀመርያ የባቡር  መስመር ዝርጋታ ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ የተዘረጋው ከአንድመቶ ዓመት በፊት ነበር።በአሁኑ ወቅት ከሰላሳ በላይ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሥራ ላይ መሆናቸው ሲታወቅ በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ተጨማሪ ባለ ሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ይጠበቃል።



ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ እና አንጌላ ሜርክል 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቻይና ግሎባል ኔትዎርክ አፍሪካ የተሰኘው ቴሌቭዥን ማምሻውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት አስመልክቶ ሲዘግብ ፈረንሳይ ከእዚህ በፊት በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ ላይ አተኩሮ የነበረው ዲፕሎማሲ አሁን ወደ ምስራቅ አፍሪካ መዞር የመጀመር አዝማምያ መታየቱን ገልጧል።የዜና ዘገባው እንደገለጠው ፈረንሳይ ከሩዋንዳ ጋር የነበራት ግንኙነት በመቀዛቀዙ አሁን ትኩረቷን ለኢትዮጵያ እና ኬንያ ማድረግ መጀመሯን ምልክቶች መታየታቸውን ያብራራል።በእዚሁም መሰረት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን (Emmanuel Macron) በሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሚመጡ ዘግቧል።በዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እደሳ፣ከአንድ መቶ ሚልዮን ዩሮ በላይ የቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ለማዘመን፣የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ለማዘመን ስልጠና እና ትጥቅ እና የዓለም ባንክ ከሚሰጠው በተጨማሪ በሁለትዮሽ ግንኙነት ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚኖር ተሰምቷል።እነኝህ ስጦታዎች ዝርዝር ጉዳይ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ በቅርቡ በሚኖራቸው የኢትዮጵያ ጉብኝት ወቅት እልባት እንደሚያገኙ ይጠበቃል።


ከሃያ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሚታደሙበት የጀርመኑ ስብሰባ 


ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከፈርንሳይ በመቀጠል የሚጎበኙት የአውሮፓ ሀገር ጀርመን ነች።ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላት ሀገር ስትሆን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በቴክኒክ ትምህርት በቀዳሚነት እገዛ ከሚያደርጉ ሀገሮች ጀርመን ተቀዳሚ ነች።በቅርቡም በኢትዮጵያ የቮልስቯገን መኪና መገጣጠምያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመክፈት ጀርመን ፍላጎት እንዳላት የኩባንያው ኃላፊዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት አስታውቀዋል።


የጀርመኗ መራሂ መንግስት አንጌላ መርክል በኢትዮጵያ አሁን እየተካሄደ ላለው ለውጥ ከፍተኛ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት አላት።ጀርመን ከኢንዱስትሪ ልማት በተጨማሪ በንግድ ክህሎት (ኢንተርፕረነርሽፕ) ስልጠና እንዲሁም በቤቶች ግንባታ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ትገኛለች።እነኝህን ክህሎቶች ደግሞ በ''ጂ ቲ ዜድ'' እና የግል ድርጅቶቿ ወደ ኢትዮጵያ የማስተላለፍ ስራዎች በመጠኑ ጀምራለች።ከእዚህ በተጨማሪ በጀርመን የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ሙያ ለሀገራቸው እንዲያፈሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት አይነተኛ በር ይከፍታል።ከእዚህ ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የጀርመንን የቴክኒክ አቅም በጣና ሀይቅ ላይ ለተከሰተው የእንቦጭ አረም መላ ለመዘየድ የጀርመን ኩባንያዎችን ሊያነጋግሩ እንደሚችሉ ይገመታል። 


በመጨረሻም የጠቅላይ ሚንስትር የጀርመን ጉብኝት ትልቁ ቦታ የሚይዘው ከሃያ ሺህ በላይ ኢትዮያውያንን የሚያገኙበት የፍራንክፈርት ስብሰባ ነው።በእዚህ ስብሰባ ከመላው አውሮፓ የሚሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ሲታወቅ በስብሰባው ላይ  በርካታ ሃገራዊ ጉዳዮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚነሱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ማብራርያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።ወደጀርመን ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር  ጋር መገናኘት ለሚፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት የጋራ ስብሰባ ቀን፣ሰዓት እና የስብሰባው ስፍራ  ከእዚህ በታች ይመልከቱ።



የስብሰባ ቀን Date: 31st October 2018
የስብሰባ መጀመርያ ሰዓት Time: 13:00 (1:00pm)
የስብሰባው ቦታ እና አድራሻ  Venue: Commerzbank Arena, Morfelder Landstrasse 362, 60528 Frankfurt am Main, Germany
Skilde   ጉዳያችን/Gudayachn

Tuesday, June 12, 2018

በኦሮሚያ በጭናክሰን ዐስራ አራት ሰዎች በሶማሌ ልዩ ፖሊስ መገደላቸውን አምነስቲ አስታወቀ






ፎቶ፡ አምነስቲ ኢተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ካወጣው ሪፖርት ላይ የተወሰደ ነው።
ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ምላሽ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥበቃም እንዲደረግላቸው አሳስቧል።

በምስራቅ ሐረርጌ በጭናክሰን ወረዳ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በከፈቱባቸው ጥቃት የብዙ ሰው ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም አምነስቲ ኢንተናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫም ከአርብ ጀመሮ እስከዛሬ ድረስ በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ዐሥራ አራት ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
ድርጅቱ አርብ ዕለት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ምላሽ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥበቃም እንዲደረግላቸው አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ዘርን ያማከሉ ጥቃቶችና በተያያዥነት የሚፈጠሩ መፈናቅሎችን ለማስቆም እንዲሁም ዜጎችን ከጥቃት ለመከላከል መሥራት አለበት ብሏል።

Friday, February 2, 2018

Dr Abiy Ahmed comments on various socio-political issues

One Nation One Ethiopia : Ethiopia's Amhara state arrests civilians after de...

One Nation One Ethiopia : Ethiopia's Amhara state arrests civilians after de...: By Abdurahman Shaban, AfricaNews February 2, 2018 The Amhara regional state in Ethiopia says a number of civilians have been arrested for...

Ethiopia's Amhara state arrests civilians after deadly clashes with army

By Abdurahman Shaban, AfricaNews
February 2, 2018


The Amhara regional state in Ethiopia says a number of civilians have been arrested for their role in deadly violence that killed over 20 people in the state through last week.

The state-run FBC and privately owned Addis Standard news portals said the party governing the region, the Amhara National Democratic Movement (ANDM), disclosed the measure after a central committee meeting.

The region, the second largest in the country, is located in the north and was riled by anti-government sentiments in three town – Woldiya, Kobo and most recently in Mersa. The Woldiya incident sparked off what is seen as solidarity protests in Kobo and Mersa.


Even though the exact number of arrest is not known, political watchers are wondering why no security forces have been arrested over their use of undue force on unarmed civilians.

According to the United Nations, security forces deployed during the Epiphany celebrations in the region used gunfire to prevent young people from chanting anti-government slogans during the celebrations. Their action led to more protests and the burning of private and public properties.

The official casualty figures for Woldiya was put at seven whiles in Kodo activists mentioned three. The Addis Standard said: “at least eleven people possibly more were killed in the town of Mersa.”


Gedu Andargachew, leader of ANDM and president of the Amhara region in a televised address last Thursday admitted the death of civilians and property damages both in Weldiya and Kobo.

Amhara along with Oromia region were the main centers of anti-government protest that shook the country in 2015 and through the better part of 2016.

To quell the violent protests, Addis Ababa imposed a nationwide state-of-emergency in October 2016. The measure was lifted in August 2017. Parts of the country have been rocked by deadly protests since the measure was lifted.

Friday, September 22, 2017

Ethiopian pop star Teddy Afro's album launch stopped by police


Though Teddy Afro songs promote love and unity among the people, the government sees him as a threat because it is a government whose stay in power is based on promoting 'hate and division'
Authorities in Ethiopia have stopped singer Tewodros Kassahun, popularly known as Teddy Afro, from launching his much-acclaimed album, Ethiopia.
A BBC reporter says federal police showed up at the hotel in Addis Ababa hours before the party and stopped Teddy's sound team from setting up.
His manager told the BBC that they are yet to get official reasons why the launch party was cancelled.
Teddy's 15-track album is the fastest-selling album in the country's history.

Following its release in May this year the album topped the Billboard World Albums chart for weeks.
Ethiopia.
On his Facebook Page, Teddy Afro has termed the police demand for a permit as ridiculous.
His concert scheduled for the eve of Ethiopian New Year, which falls on 11 September, has also been cancelled in unclear circumstances.

Who is Teddy Afro?
By Emmanuel Igunza, BBC News, Addis Ababa
Teddy Afro is a huge figure in Ethiopia
He enjoys an almost cult-like following and his latest album - his fifth - has elevated him to legendary status.
The album is like a history lesson, with references to Emperor Tewodros II, seen as the father of modern-day Ethiopia, and it also calls for unity among Ethiopians.
Teddy is no stranger to controversy though.
In 2008, he was jailed for a hit-and-run accident. He has always maintained that the case against him was politically motivated.
He raised the ire of the authorities in 2005 when he released an album that was seen as critical of the authorities in the wake of disputed elections, but Teddy has tried to distance himself from politics.
He still enjoys a massive following among Ethiopians who adore and revere him.
Months after his album was released, his music is still being blasted out on public transport, in bars, local shops and homes.

Thursday, December 15, 2016

Olympian Feyisa Lilesa listed in FP's 2016 Top 100 global thinkers

WASHINGTON, DC - Ethiopian Olympic medalist Feyisa Lilesa has been listed as one of the 100 global thinkers in 2016.
The following story was released by the Foreign Policy:
"Given the fact that the Olympic Charter bans political propaganda, demonstrations are a rarity at the games. Nevertheless, Ethiopian runner Feyisa Lilesa snubbed the rulebook in order to call attention to the brutal actions of his country&rsquo;s security forces. As the marathoner approached the finish line in second place, he crossed his arms over his head - an attention-grabbing gesture to show solidarity with his Oromo tribe. In the weeks before the race, the Ethiopian government had cracked down on protests by the embattled indigenous group and killed dozens. &ldquo;If I would&rsquo;ve taken my medal and went back to Ethiopia, that would&rsquo;ve been the biggest regret of my life,&rdquo; Lilesa, who hasn&rsquo;t yet returned home, told the Associated Press. &ldquo;I wanted to be a voice for a story that wasn&rsquo;t getting any coverage.&rdquo;</p>

CBC RADIO: What was reported then

On the final day of the Rio Olympics, Ethiopian marathoner Feyisa Lilesabecame a silver medalist. Lilesa crossed the finish line with arms raised above his head, and crossed over each other, as in an "X" — a political gesture instantly recognized in Ethiopia.
Lilesa says the symbol of defiance was a peaceful protest against how the Oromo people of Ethiopia have been treated by the government. Close to 100 people were slaughtered in a protest just weeks before the Olympics.
Since his protest on the world's stage, Lilesa tells The Current's Anna Maria Tremonti through a translator that he's worried about his safety if he were to return home.
"Having done this, going back to Ethiopia means suicide. They will kill me. If not killing, they will imprison me and torture me," says Lilesa who is still in Rio.
Lilesa feels it is important to stand up publicly and expose the repression of the Oromo people by the Ethiopian government. He tells Tremonti that "people are dying, being killed, being sent to refugee camps… many thousands were in the red sea running away from the country. People were having peaceful demonstrations but being killed."

Ethiopia: detained journalist missing, denied access to family and medical care

EHRI News Release
December 13, 2016



Ethiopian authorities should immediately disclose the location of Temesgen Desalegn, who was jailed on spurious charges two years ago, and give him access to medical care, said the Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) and DefendDefenders (East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project) today.


Temesgen Desalegn is serving a three-year sentence in Ziway prison on charges of defamation, incitement, and false publication. However, relatives have attempted to visit him for seven consecutive days, and been told by Ziway prison administration officials that his location is unknown. His relatives reported that they had not seen him since 7 November.
On 12 December, a Ziway prison official speaking on the condition of anonymity told a journalist from Deutsche Welle’s Amharic service that Temesgen was at the prison.

 However, one relative who attempted to visit him today was told by prison officials that he was not there, and that they do not know his whereabouts.

One of Temesgen’s relatives told AHRE that they have been travelling 160km from the capital Addis Ababa to Ziway prison to visit him, and that since the State of Emergency was declared on October 8 their visiting time has been reduced from 40 to 8 minutes.

“It is unacceptable that after two years of detention in Ethiopia’s insalubrious and overcrowded prison system, authorities are unable or unwilling to provide Temesgen’s relatives with information on his whereabouts,” said Yared Hailemariam, Executive Director of AHRE.

 “We are extremely concerned about Temesgen’s poor health and urge the Ethiopian authorities to immediately disclose his location and give him access to medical care.”



The Information Minister at the time of his conviction, Redwan Hussien, told CPJ that the case was related to news articles discussing the peaceful struggle of Ethiopian youth movements and expressing criticism of the government.

“The situation of human rights defenders in Ethiopia has dramatically worsened since the protests broke out one year ago, and has been compounded by overarching restrictions imposed by the State of Emergency directives,” said Hassan Shire, Executive Director of DefendDefenders.

“The government’s extreme sensitivity to criticism has led to a ruthless and persistent crackdown on protesters, journalists, activists and ordinary citizens who attempt to express legitimate concerns and grievances.”

These include Abebe Wube, general manager of Ye Qelem Qend newspaper, who was arrested in Addis Ababa by security forces on 18 October and Befekadu Hailu, co-founder and member of the Zone 9 bloggers collective, who was arrested on 11 November 2016 at his home in Addis Ababa. Both are still currently detained

Wednesday, August 31, 2016

የመኢአድ ጋዜጣዊ መግለጫ

የድርጅቱ ባለሥልጣናት በንባብ ባሰሙት ባለ-ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ባስቸኳይ ካልተሟሉ ፓርቲያቸዉ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገል አስጠንቅቀዋል።
የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ትናንት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ለተቃዉሞ አደበባባይ በወጡ ሠላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱትን የሐይል እርምጃ የግፍ ጭፍጨፋ በማለት አወገዘዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-ወጥ በሚል ሽፋን የሠላማዊ ዜጎችን ቤት እያፈረሰ ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን እንዲያቆምም ድርጅቱ ጠይቋል።የድርጅቱ ባለሥልጣናት በንባብ ባሰሙት ባለ-ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ባስቸኳይ ካልተሟሉ ፓርቲያቸዉ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገል አስጠንቅቀዋል።
http://www.dw.com/am/የመኢአድ-ጋዜጣዊ-መግለጫ/a-19513038


ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ


 Audios and videos on the topic

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለወቅቱ ሁኔታ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ኢሕአዴግ ሲነሣ ከነበረበት ሁኔታ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የተለወጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አስታውቀዋል፡፡


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢሕአዴግን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የማዕከላዊ ምክር ቤቱን ጉባዔ ተከትሎ ለመንግሥታቸው መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ “ኢሕአዴግ ግዙፉን የደርግ ሥርዓት በሚደመስስበት ጊዜ ካስቀመጣቸው እሤቶች መካከል እራስን ለሕዝብ የመስጠትና ለሕዝብ የመኖር ጉዳይ ወሣኝ ጉዳይ ነው ተብሎ የተያዘ ነው፤ ነገር ግን ነባራዊ ሁኔታው ተቀይሯል” ብለዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “ነባራዊ ሁኔታው በተቀየረበት ሁኔታ አመራሩ የመንግሥትን ሥልጣን የሚያይበትና በተግባርም የሚፈፅምበት ሁኔታ በሚገባ ካልተቀየረ አሁን ባለንበት ደረጃ የጉዟችን እንቅፋትና መሠናክል የበዛበት ጉዞ ይሆናል” ብለዋል፡፡


ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡


http://amharic.voanews.com/pp/3487227/ppt0.html

Wednesday, August 17, 2016

የቨርጂኒያ ጉባኤ ውሳኔ መግለጫ





                   የቨርጂኒያ ጉባኤ ውሳኔ መግለጫ

           የህወሃት አጥፍቶ መጥፋት ፖሊሲ በተግባር ሲከሰት

ኢትዮጵያዊነት በተለያዩ ወቅቶች በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት የዜጎችን መሠረታዊ መብት ሲጥስ፤ የሙስሊሙን ወገኖቻችንን ድምጽ ሲያፍንና መብታቸውን በሀይል ሲከለክል፤ በአረብ ሀገር ስለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ብሶት፤ ስለአማራ ሕዝብ አላግባብ ከመሬታቸው መፈናቀልና ለሱዳን አላግባብ ስለሚሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ተክታታይ መግለጫዎችን አውጥቶአል። አሁን ደግሞ ለሀገራችን ህልውና አስጊ ሁኔታ በመፈጠሩ ለየት ያለ መግለጫ ለማውጣት ተገዶአል። ይኅውም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውና ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው "መንግሥት" ከዳር እስከ ዳር በተነሳበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊወድቅ የተንገዳገደበትና ተቃውሞውን በፍጹም አረመኔአዊ ጭካኔ በማዳፈን የፈጠረው ቀውስ ነው። በአሁኑ ወቅት ከዳር እስከ ዳር የሚታየውን የሕዝባችንን የእምቢተኝነትና፤ ለትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር አንገዛም ባይነት በጥንቃቄ ገምግሞ ይኅንን መግለጫ አውጥቶአል።

በዘርና በቅዋንቅዋ የተዋቀረ ፌደራላዊ አስተዳደር የመጨረሻ ውጤቱ በሕዝብ መሀከል አለመግባባትን ፈጥሮ የእርስ በርስ ማጋጨትን የሚያስከትል መሆኑ ግልጽ ነው። በተለይም በሀገራችን ለዘመናት ሲገነባ የኖረውን የሕዝቡን የባህል፤ የአንድነትና የስነ ልቦና ትሥሥር በማዳከሙ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ አድርሶታል። ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በተሻለ መልኩ የተገነባውን አስተዳደር፤ የመከላከያና የብሄር አቀፍና የአንድነት እሴቶች ሀላፊነት በጎደለው መልኩ አፈራርሶታል። ይልቁንም የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሚከተሉት የከፋፍለህ ግዛው መርህ መሠረት፤ በሀገሪቱ ያሉትን የሲቪል፤ የመከላከያ፤ የፀጥታና የኢኮኖሚ ቁልፍ መዋቅሮች እንዲቆጣጠሩ አድርጎአቸዋል። እንደዚሁም በአብዛኛው በሀገሪቲ ያሉትን የነጻ ገበያ ዘርፎች እንዲቆጣጠሩ ረድቶአቸዋል።

ዘረኛው መንግሥት ሕዝባችን ለሚያነሳቸው ሕጋዊና መሠረታዊ የመብት ጥያቄዎች ሁሉ እስካሁን የሚሰጠው ምላሽ የእሥር፤ የግድያና ከኖሩበት ቀየ ማፈናቀል ሆኖአል። በህዝባችን የሚቀርቡት የመብት ጥያቄዎች በዓለም መንግሥታት፣ በዓለም አቀፍ መብት ተኮር ድርጅቶች እንደዚሁም በዚሁ ዘረኛ የህወሃት/ኢህአዴግ ሕገ መንግሥት ላይ የሰፈሩና በሕግ የተደነገጉ መብቶች ናቸው። ሰሞኑን በጋምቤላ፡ በጎንደር፤ በባሕር ዳር፤ በኦሮምያ በአዲስ አበባ በኮንሶ በኦጋዴንና በመላው የሀገሪቱ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያሉት ሰላማዊ ሰልፎች በቂ ምስክር ናቸው። ግድያው፤ አፈሳና ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ የዚህ ዘረኛ አምባገነን መንግሥት ዓይነተኛ መገለጫዎች ናቸው።

የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ መረዳት ለመፍትሄው ወሳኝ እንደሆነ እናምናለን። የሥርዓቱ ደጋፊዎች አስተዳደሩ አንድ አንድ ጥገና ተደርጎለት ሊሻሻል እንደሚችል ሊሰብኩን ይሞክራሉ። 2

በዘር ላይ የተመሠረተ ፌድራሊዝምና አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለሀገራችን የሶሽያልና የኢኮኖሚ ችግር መፍትሄ ያስገኛሉ ብለው ይሰብካሉ። የሀገሪቱ ቸግር የመነጨው ይኅንን ፍልስፍና በመከተል መሆኑን የተረዱት አይመስልም። በዘር ላይ የተመሠረተ የፌድራል አስተዳደር የሚሻሻል ሳይሆን ሥር ነቀል ለውጥ የሚያስፈልገው ነው። አለ የሚባለው የወያኔ ሕገ መንግሥትም ሕዝብ ያልመከረበትና በመሠረቱ የሀገሪቱንና የሀዝቦችዋን አንድነት የሚፃረር በመሆኑ የዲሞክራሲ መሠረት ሊሆን አይችልም።

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ በተቃራኒው ሁለት መሠረታዊ መርሆዎችን ማለትም ሀ) ሁሉንም ዜጎች ያቀፈ ኢትዮጵያዊነትን ያራምዳል ለ) ዓለም አቀፍ እውቅናና ክብር ላላቸው ለመሠረታዊ የሰው ልጅ፤ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች መከበር ይታገላል። ድርጅታችን ባዘጋጀው " የዜጎች ቃል ኪዳን ለዲሞክሪያስያዊት ኢትዮጵያ" ሰንድ እንደተገለፀው ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተማማኝ መሠረት በሚጥሉና የዜጎችን ሁለንተናዊ መብቶች በሚያስከብሩ መርሆዎች መመራት ወሳኝነት አለው። እነሱም፤ የኢትዮጵያ ግዛትና የሕዝቦችዋ አንድነት፤ የግለስብ ነጻነት ከቡድን ነፃነት ቀዳሚነት፤ የሕይወትና የምግብ መብት መከበር፤ ቢያንስ የአንድ ብሄራዊ ቅዋንቅዋ አስፈላጊነት፤ ፍትሃዊ የፖለቲካ አስተዳደር፤ ሁሉን አቀፍ የሆነ ብሔራዊ ውትድርናና የሲቪል አገልግሎት፤ የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ፤ በሙሉ ነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክና የፓለቲካ ድርጅቶች፤ እንደዚሁም የመንግሥት ድርጅቶች አሠራር ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነብት መሆን ይኖርበታል።

በሀገራችን ያለው ሥር የሰደደ ችግር በመሠረቱ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ይጠይቃል። ሕዝብን በዘር በመከፋፈልና በአንድ ጠባብ ብሄርተኝነት ፖሊሲ ማስተዳደር ችግሩን የበለጠ ያብብሰዋል እንጂ ለዲሞክራሲና ለሀገር ብልጽግና መሠረት አይሆንም። እንደዚሁም ግልጽ ያልሆኑ ፕሮግራሞች፤ ከውጭው ዓለም የተቀዱ አይድኦለጂና ባዶና ፍሬ ቢስ ፕሮፓዳንዳ ለሀገራችን የሚያስገኙት ጥቅም የለም።

ኢትዮጵያዊነት ይኅንኑ በመገንዛብ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ በመመሥረት አሁን ያለው ዘረኛ ሥርዓት ሲወገድ ለችግሮቹ ሀገራዊ መፍትሄ ለማስገኘት ብቃት ባላቸው ምሁራንና ባለሞያዎች አማካኝነት ለሽግግሩና የቀጣዩን ሥርዓት አካሄድ የሚጠቁሙ አማራጮች ላይ የጥናት ጽሁፎች እንዲቀርቡ በ፤ማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊነት እስከአሁን ሁለት ጥናታዊ ጉባኤዎች አካሂዶአል። በእነዚህ ጉባኤዎችም 12 ምሁራኖች በተለያዩ አርዕስቶች ላይ ጥናታዊና የምርምር ጽሁፎች እየቀረቡ ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በ2015 የቀረቡት ጥናቶች አዲስ ሕገ መንግሥትን ፤ አዲስ የኢኮኖሚ ፖሊሲን ፤ የሽግግሩ ዋና ዋና ተሳታፊዎችን መለየትንና የሽግግር አፈፃፀሙ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። ዋናዎቹ የጥናት ጽሁፎች በዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዓውደ ጥናት መጽሄት (International Journal of Ethiopian Studies) ታትመው ወጥተዋል። የመክፈቻ ንግግሮቹም በኢትዮጵያዊነት ድህረ ገጽና (www.ethiopiawin.net) በዩ ትዩብ (youtube) ላይ ይገኛሉ። 3

ሰሞኑን የተጠናቀቀው የ2016 ጥናታዊ ጉባኤ ደግሞ የኢትዮጵያዊነትን ታሪካዊ አመጣጥና በአሁኑ ወቅት ከሚራገበው ጠባብ የማንነት አባዜ የሚገላግለን፤ ብሄራዊ መለያችንና መገለጫችን ሊሆን የሚችልና የሚገባ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን በማያሻማ ህኔታ ያረጋገጠ ነው። እንደዚሁም በሶስት አማራጮች ላይ ያተኮረ የመንግሥት አወቃቀር፤ ቀደም ሲል ከነበሩ የመንግሥታት አስተዳደር ዓይነቶች ልንማር ስለምንችለው ደካማና ጠንካራ ጎኖች ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል።

የህወሃት መንግሥት በተደጋጋሚ በተግባር እንደታየው ሕዝቡ የሚያነሳቸው የመብትና የነፃነት ጥያቄዎች የአገዛዙ ማብቂያ እንደሆነ ስለሚገነዘብ እስከ አሁን ለሕዝቡ ጥያቄዎች የሰጠው መልስ ግድያ፤ ማሰርና ማንገላታት ብቻ ሆኖአል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሐረር እስክ ጎንደር ከጋምቤላ እስከ ወለጋ በማያወላውል መልኩ በቃ በማለት በመላ ሀገሪቱ የክተት ጥሪ እያተስተጋባ ነው። የአምባገነንና የዘረኝነት አገዛዝ ይብቃ ብሎ የፍርሀት ሽባቡን በጣጥሶ በአንድነትና በእምቢተኝነት ገንፍሎ ወጥቶአል። የሕዝቡ የበላይነት ከመንግሥት የሚለገስ ስጦታ ሳይሆን በትግል የሚገኝ የመስዋዕትነት ዉጤት መሆኑን በሚገባ ተረድቶታል።

ወገኖቻችን ምሬታቸውን ለማሰማት ስላማዊ ስለፍ ቢወጡም አምባገነኑና ዘረኛው መንግሥት በአጋዚ ጦሩ አልሞ ተኮአሾች እስክ አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲገድል በሺዎቸ የሚቆጠሩ አቁስሎአል፤ አስሮአል። ስለዚህ፤ ኢትዮጵያዊነት የውድ ወገኖቻችንንና የሕዝባችንን ትግል፤ ብልሀትና ጥንቃቄ በተሞላበት መንግድ እንድንደግፍ እጥብቆ ያሳስባል። አምባገነኑና ዘረኛው መንግሥት መውደቁ አይቀርም። የኛ ተግባር በተቻለን አቅም የሀገራችንና የወገኖቻችን አንድነት እንዳይናጋ መከላከል ሲሆን በአንጻሩ ትግሉን የሚረዱ ጠቃሚ ሀሳቦችንና ለቀጣዩ ሥርዓት ጠንካራ አማራጮችን አጥንቶ ማቅረብና ማመቻቸት ሊሆን ይገባል።

በዚህ አንፃር፤ ኢትዮጵያዊነት የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል፤

1. "የዜጎች ቃል ኪዳን ለዲሞክሪያሲያዊት ኢትዮጵያ" ሰነድና ከፍ ብሎ ከተጠቀሱት ሁለት ጉባኤዎች የተገኙ የጥናት ውጤቶች፤ በሌሎች ድርጅቶች በኩል ከተከናወኑ ተመሳሳይ ጥናቶች ጋር ተዳምሮ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሰራጭና በዚህ ላይ የተቀነባበረ ብሔራዊ አጀንዳ በጋራ ለመቅረጽ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲደረግ፤

2. የፖለቲካልና የሲቪክ ድርጀቶች፤ እንዲሁም ሀገር ወዳድ ወገኖች በሙሉ የግለኝነት አዝማሚያቸውን ትተው "ዛሬ ትብበር ነገ ውድድር" በሚል መፈክር ሥር ትግላቸውን እንዲያቀነባብሩ፤

3. ከሀገር ውጭ የምንገኝ ወገኖች በሀገራችን በህወሃት/ኢህአደግ የሚካሂደውን ግድያ፤ እስራትና መጠን የለሽ የመብት ረገጣ ለምንኖርባቸው ሀገሮች መንግሥታቶች፤ የሕዝብ ተወካዮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በማሳወቅ እርምጃ እንዲውስዱ ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ጥረት እንድናደርግ፤

4. በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ንቅናቄዎች ጠባብና ግለኝነት አመለካክትና ፍላጎቶችን አስወግደው በብሔራዊ አንድነት ዓላማ ሥር እጅ ለእጅ ተያይዘው ሁሉን አቀፍ ሀገር የማዳን ትግሉን እንዲያፋፍሙ፤


4


በተጨማሪም ኢትዮጵያዊነት፤ ለአሜሪካ፤ ለካናዳ፤ ለቻይናና ለአውሮፓ ማህበር፤ የሚከተሉትን መልክቶች ያስተላልፋል፤


1. ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ስበብና የኤኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በህወሃት/ኢሀአዴግ በሕዝባችን ላይ የሚፈጸመውን ኢስብዓዊ በደል እያያችሁ እንዳላየ ማለፍና የሕዝቡን ሰቆቃ የሚያባብስ ድጋፍ መስጠታችሁን እንድታቆሙ እንጠይቃለን።

2. በተለይም ሕዝባችንን ለመግደያና ለማፈኛ የሚሆን የጦር ማሣሪያና የኢኮኖሚ ዕርዳታችሁን በአስቸክዋይ ማቆም አለባችሁ። የአፍሪካ ቀንድ ሌላ መንግሥት አልባ ሥርዓት አትሻም። የአንድ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ድምፅ መደመጥ ይኖርበታል።

የተባበረ ክንድ ያሸንፋል

የኢትዮጵያውያን የነፃነት ጩኅት በመላው ዓለም ያስተጋባል

ነፃነት ወዳዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእርግጠኝነት ያሸንፋል

ይህ የውሳኔ መግለጫ እ ኤ አቆጣጠር ኦገስት 7 ቀን፤ 2016 በተሰበስበው የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጠቅላላ ጉባኤ፤ በታይሰን፣ ቨርጂንያ፤ አሜሪካ የፀደቀ ነው።





Tuesday, May 24, 2016

59 political prisoners break out of a prison in Konso, south Ethiopia





ESAT News (May 23, 2016)
Reliable sources told ESAT that 59 political prisoners broke out of a prison in Konso, south Ethiopia on Friday.
A source who wish to remain anonymous told ESAT that the prisoners who broke out on Friday were detained by the regime’s forces following the protest few months ago by the people of Konso, who demanded for the Konso to be upgraded to a zonal administration status.
Witnesses told ESAT that the residents of Konso were giving covers to the prisoners as security forces were trying to arrest them.
Hundreds of people were arrested and incarcerated by the regime for demanding political and administrative rights in Konso two months ago.

Saturday, May 9, 2015

የብሄራዊ ደህንነት መረጃ ሃላፊዎች ጥብቅ ፍተሻ እንዲካሄድ አዘዙ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ ” ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ” ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት ጠባቂዎች ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር እንዲያደርጉ” ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
እንዲህ አይነት ትእዛዝ ተላልፎ እንደማያውቅ የሚናገሩት ምንጮች፣ ትእዛዙ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ረብሻ ሊፈጠር ይችላል ከሚል ስጋት ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች አስተያየታቸውን ቢሰጡም፣ ትእዛዙ በኢህአዴግ ባለስልጣኖች ላይ ሳይቀር መተላለፉ ውሳኔው ከመጪው ምርጫ ጋር ብቻ ያልተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል።
የደህንነት ሰራተኞች ለመስሪያ ቤት ሃላፊዎች ብቻ ሳይሆን ትእዛዙን ለጥበቃ ሃላፊዎችም እየሰበሰቡ በመናገር ላይ ናቸው።

Sunday, November 30, 2014

TV4 exposed Al Amoudi and H&M

Is H&M turning a blind eye to land grabs in Ethiopia? TV4 does an investigation into H&M’s cotton sourcing from Ethiopia and discovers the disturbing truth. The corrupt businessman Sheik Mohammed Al Amoudi the second richest man in the Arab world also badly exposed in this investigation
                           
             https://www.youtube.com/watch?v=5-ImoKhymL4



Tuesday, September 2, 2014