ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ ” ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ” ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት ጠባቂዎች ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር እንዲያደርጉ” ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
እንዲህ አይነት ትእዛዝ ተላልፎ እንደማያውቅ የሚናገሩት ምንጮች፣ ትእዛዙ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ረብሻ ሊፈጠር ይችላል ከሚል ስጋት ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች አስተያየታቸውን ቢሰጡም፣ ትእዛዙ በኢህአዴግ ባለስልጣኖች ላይ ሳይቀር መተላለፉ ውሳኔው ከመጪው ምርጫ ጋር ብቻ ያልተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል።
የደህንነት ሰራተኞች ለመስሪያ ቤት ሃላፊዎች ብቻ ሳይሆን ትእዛዙን ለጥበቃ ሃላፊዎችም እየሰበሰቡ በመናገር ላይ ናቸው።