Thursday, October 31, 2013

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው


ከደቡብ ጎንደር : ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም : ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው :: ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::

ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::

በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::

እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ
ሰሜን ጎንደር

Wednesday, October 30, 2013

ኢትዮጵያ- የፖሊስ መንግስት ያንሰራፋባት ሀገር

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገመንግስት በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል፡፡“በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል፡፡ ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም፡፡ ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡“ ይላል አንቀጽ 19(2)(5)፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለዉም፡፡

ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች “HRW“ የተባለው ዓለም ዓቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ መንግስት “የፌዴራል ፖሊስ ማዕከላዊ ምርመራ” እየተባለ በሚጠራው የፖሊስ ጣቢያ የሚፈጸሙትን አስደንጋጭና አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ዘገባ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ይህ የፖሊስ ምርመራ ማዕከል በጥርጣሬ የተያዙ ዜጎችን በማሰቃየት ይታወቃል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በቁጥጥር ስር ባሉ እስረኞች ላይ በተለይም ያለው መንግስት ይቃወሙኛል በሚላቸው የፖለቲካ እስረኞች ላይ ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም እልህ አስጨራሽ የምርመራ ሂደት በማድረግ እስረኞችን በግድ ወንጀል ሰራን ብለው አንዲአምኑ በማስገድድ፣ እንደሚያሰቃይና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ“ እየፈጸመ እንደሆነ በማረጋገጥ በዘገባው ይፋ አድርጓል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በማያያዝም “ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው ተቋም ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች፣ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች፣ መንግስት የብሄር ግጭት ተንኳሾች ናቸው በሚላቸውና ሌሎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በጅምላ ተይዘው የሚሰቃዩበት የምርመራ ማዕከል” ነው ብሎታል፡፡
ገጣሚው ዊሊያም ኤርነስትን አባባል በመዋስ “ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል” የሰቆቃ መደብር በለቅሶና በሰቃይ የታጠረ የጭለማ ቤት ነው :: የገዥው መንግስት ተቃዋሚዎች፣ አመጸኞች፣ የሚላቸዉን የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እስረኞች በሙሉ በምርመራ ጊዜ ሰቆቃ ተጠቅሞ አራሳቸዉን አንዲወነጅሉ ያስገደዳቸዋል:: እንዲሁም ብዙዎቹ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች አባባል ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም “አስቀያሚው የአካልና የስነ ልቦና ማሰቃያ እንዲሁም አስገድዶ የማሰመኛ ምሽግ” መሆኑን በመጠቆም በማዕከሉ ከሚፈጸሙ የማሰቃየት ወንጀሎች እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ መሆናቸውን በአጽንኦት ገልጿል፡፡ አኔም በግሌ ከአስፈሪው ማአከላዊ ምርመራ መዳፍ የተረፉ የቀድሞ እስረኞችን አነጋገሬ አውቃለሁ::

እ.ኤ.አ. በ2011 የአሜሪካ መንግስት መምሪያ በዓመታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዘገባው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ለማሳየት የሚከተለውን ማጠቃለያ አስፍሯል፡፡
  • ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት እ.ኤ.አ. በ2009 በአዲስ አበባ የሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የፖሊስ ምርመራ ማዕከል ፖሊስ ኃይልን በመጠቀም አስረኞችን አስገድዶ ለማሳመን የአካል ማሰቃየት ሰቆቃ ድርጊት ሲፈጽም ነበር፡፡ ይህ ዓይነት የማሰቃየት ዘዴ በአሁኑ ጊዜም በተግባር ላይ እየዋለ ያለ መሆኑን ዜጎች ያላቸውን ሰፊ እምነት አጽንኦት በመስጠት እየገለጹ ነው፡፡ ባለስልጣናቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ማዕከላዊ ምርመራን ለመጎብኘት የሚያቀርቡት ጥያቄ አሁንም በመንግስት በኩል አዎንታዊ ምላሽ እንዳላገኘ ይታወቃል፡፡“ በማለት ድርጅቱ ያለውን ሀሳብ ቋጭቷል፡፡


የ15ኛው ክፍለ ዘመን የሰቆቃ ስልት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ!
በአዲስ አበባ እምብርት ላይ የሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የማሰቃያ ምርመራ ተቋም በመካከለኛው (15ኛው) ዘመን በአውሮፓ የሰብአዊ መብት ረጋጮች በንጹሀን ዜጎች ላይ ይደረግ የነበረውን አስፈሪ፣ አስደንጋጭና ተስፋቢስ የማሰቃየት ስልት ገጽታ መለስ ብለን እንድናስታውስ ያስገድደናል፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች መግለጫ “የማዕከላዊ ምርመራ ፖሊሶች በህግ ጥላ ስር የተያዙ የህግ አስረኞችን እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ በግድ ለማሳመን፣ መግለጫ እንዲሰጡና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት ሲሉ በእስረኞች ላይ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የማስገደጃ ዘዴዎችን እና ልዩ ልዩ ኢሰብአዊ ድርጊቶቸን ይፈጽማሉ፡፡ እንደ መካከለኛው የአውሮፓ ዘመን መብት ረጋጭ ተቋሞች ሁሉ የኢትዮጵያው የምርመራ ማዕከልም እንደመርማሪዎቹ ፍላጎትና አመችነት ሁኔታ እስረኞችን በአራት ዋና ዋና ክፍሎች መድቧቸዋል፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል በተለያዩ የእስረኞች አያያዝና እያንዳንዳቸው ባላቸው ቅጽል ስም የሚታወቁ አራት አይነት የማጎሪያ እስር ቤቶች አሏቸው፡፡ እነርሱም፣ 1ኛ) ጨለማ ቤት፣ ይህ እስር ቤት በጣም አስቸጋሪና ብርሀን የማይገኝበት የማጎሪያ ክፍል ነው፡፡ በዚህ እስር ቤት እስረኞቹ የፀሐይ ብርሀን እና የመጸዳጃ ቤት የማግኘት ዕድላቸው በጣም ጠባብ ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ለብቻ የመታሰር ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል፣ 2ኛ) ጣውላ ቤት፣ ይህ እስር ቤት በክፍል ውስጥ እንደልብ መዘዋወር የማያስችል ሲሆን ክፍሎቹም በቁንጫ ተባይ የተወረሩ ናቸው፡፡ 3ኛ) ሸራተን፣ በቅርብ ጊዜ ከእስር ቤት የማይለቀቁ ብዙዎቹ እስረኞች ወደዚህ የማጎሪያ ቤት እንዲዛወሩ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባለው ሆቴል ስም የተሰየመው እስር ቤት እስረኞቹ የተሻለ የአካል እንቅስቃሴ የማድረግና በህግ አማካሪዎቻቸውና በዘመዶቻቸውም መጎብኘት እንዲችሉ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ፈቃድ የላላበት ነው፡፡ 4ኛ) የተፋፈገው የሴት እስረኞች ማጎሪያ፣ ይህ እስር ቤት በገፍ ሴት እስረኞችን አጭቆ የያዘ ነው፡፡”

ገዥው የኢትዮጵያ አስተዳደር ከተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች መረጃዎችን፣ መግለጫዎችን እና ተገደው የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ የተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎችን ይጠቀማል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች አንደጠቀሰው: “እስረኞች በተደጋጋሚ በጥፊ ይጠናገራሉ፣ በእርግጫ ይመታሉ፣ በቦክስ ይደለቃሉ፣ በዱላና በጠብመንጃ ሰደፍ ይደበደባሉ፡፡ አንዳንዶች እንደተናገሩት በሚያስጨንቅ ሁኔታ [በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው ‘እጅን በገመድ አስሮ ገልብጦ ከጣራ ወደ ታች በማንጠልጠል እንዲወድቁ በማድረግ የማሰቃየት’] ወይም ሁለት እጆችን ወደ ላይ ከእራስ በላይ ከፍ አድርጎ በገመድ አስሮ በማቆም ለበርካታ ሰዓታት በማቆየት በተደጋጋሚ ያሰቃዩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ አሁንም [በመካከለኛው ዘመን ይደረግ እንደነበረው ሁሉ] በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምርመራ ማዕከልም የእስረኞችን እጆች በካቴና በማስገባት ለበርካታ ጊዜ ታስረው እንደሚቆዩ እንዲያውም አንድ እስረኛ ከአምስት ተከታታይ ወራት በላይ እጁ በካቴና ታስሮ እንደቆየ እና ማቋረጫ በሌለው የቃል ጥያቄ ምርመራ በታሳሪዎቹ ዘንድ ፖሊስ ተደጋጋሚ ዛቻ እንደሚያደርግ ተረጋግጧል፡፡” በጥንት ጊዜ ‘በእስፓኞች ይደረግ እንደነበረው አሰቃቂ የምርመራ ሂደት‘ አንዳንዶቹ እስረኞች ለበርካታ ጊዜ ተገልለው ለብቻቸው እስራታቸውን እንዲገፉ ተበይኖባቸዋል፡፡ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን የእስር ቤት ማጎሪያዎች ይደረግ እንደነበረው ሁሉ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እስረኞቹ የፀሐይ ብርሃን የማግኘት መብታቸውን ይከለከላሉ፣ በደካማ የንጽህና አያያዝና በውሱን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ይሰቃያሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በተለይም በመጀመሪያ ለምርመራ የቀርቡትን ተጠርጣሪዎች ላይ የበለጠ አሰቃቂ ይሆናሉ፡፡”

የእነዚህ ሁሉ የማሰቃየት ተግባራት ዋና ዓላማው በእስረኞች ላይ ታላቅ ጫና በመፍጠር ትክክል ይሁንም አይሁን ለቀረበባቸው የወንጀል ክስ ፈጻሚ መሆናቸውን እንዲያምኑ በማስገደድ መግለጫ፣ የእምነት ቃልና መረጃ እንዲሰጡ ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህን በማስገደድ የተሰጡ መግለጫዎችና በግዳጅ የተገኙ የእምነት ቃሎችን አንዳንድ ጊዜ ተወንጃዮቹ ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ያለውን መንግስት ተገደው እንዲደግፉና ጉዳያቸው በፍርድ ቤቶች በሚታይበት ጊዜም መንግስት እንደ ማስረጃ ለመጠቀም ስለሚፈልጋቸው ነው፡፡

በማዕከላዊ እስር ቤት እስረኞች ለደረሱባቸው የአለአግባብ መታሰርና መንገላታት የሚጠየቅም ሆነ የሚገኝ ካሳ የለም፡፡ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የማየት ነጻነት የላቸውም፡፡ ፍርድ ቤቶች የማዕካላዊ ምርመራ ፖሊስ በምርመራ ጊዜ በእስረኞች ላይ የማሰቃየትና ህገወጥ ድርጊቶችን ፈጽሟል የሚል ውንጀላ ለፍርድ ቤቶች ቢቀርብ ተገቢውን የማጣራት ሂደት በማከናውን እርምጃ ለመውሰድ አይችሉም፡፡ በሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ መሰረት የቀድሞ እስረኞች የማዕከላዊ ምርመራን የበቀል እርምጃ በመፍራት በምርመራ ወቅት የደረሱባቸውን በደሎች ለፍርድ ቤቶች ለማቅርብ ስለሚፈሩ ዝምታን እንደሚመርጡ ጠቁሟል፡፡ አንዳንዶቹም ከፍርድ ቤቶች ችሎት በፍጹም ደርሰው እንደማያውቁ ይናገራሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በጁላይ 2008 በዓለም በደህንነት ሙያ ታዋቂ የሆኑት እንግሊዛዊው ጡረተኛ ኮሎኔል ሚካኤል ዴዋርስ የኢትዮጵያን የእስር ቤቶች አያያዝ ሁኔታ አጥንተው የመፍትሄ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተዋውለው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እስር ቤቶችን ከጎበኙ በኋላ በተጨባጭ የተመለከቱትን የእስር ቤቶችን ሁኔታ እንደሚከተለው አቅርበዋል፡፡ እንደዚህም ይተርኩታል፡፡
  • “እስረኞቹ ወዳሉበት ግቢ ውስጥ እንድገባ ጥያቄ አቀረብኩ፣ ይህ ግቢ ረዥም የሆነ በአንድ ጎኑ በኩል መጠለያ ሊሆን የሚችል ዳስ ይዟል፣ ግቢው በግንብ አጥር የታጠረ ሲሆን ለአካባቢው ጥበቃ እንዲያመች ሆኖ የተሰራ የጥበቃ ማማና ጥበቃዎች አሉት፡፡ በግቢው ውስጥ ከ70 እስከ 80 የሚሆኑ እስረኞች በተጎሳቆለ ሁኔታ ይታያሉ፡፡ ለሁሉም እስረኞች በምንጣፍ ለመጋደም የሚያስችል በቂ ክፍል የለም፣ መብራት የሚባል ነገር የለም፣ ቦታው በአይነምድርና በሽንት በሚሰነፍጥ ሽታ ታውዷል፣ በግቢው ውስጥ ምንም ዓይነት ውኃም ሆነ የመጸዳጃ ፋሲሊቲ የለም፣ በግቢው ውስጥ ለሴት እስረኞች ተብሎ ትንሽ የሳር ጎጆ ተቀልሳ በቅርብ እርቀት ትታያለች፣ ሆኖም ግን ግቢውን ለማሻሻል ተብሎ በግቢው ውስጥ የተሰራ ምንም ነገር የለም፣ አብዛኞቹ እስረኞች በትናንሽ ወንጀሎች በተለይም በሌብነት ወንጀል እየተያዙ ወደ እስር ቤቱ በተደጋጋሚ የሚመጡ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹ ለወራት በዚሁ እስር ቤት የቆዩ ናቸው…፡፡”

ኮሎኔል ዴዋርስ በእስር ቤቱ የተመለከቱትን በሚከተለው መልክ አጠቃለዋል፣ “የእስረኞቹ አያያዝ በሚያሳፍር ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም ሁኔታ ፌዴራል ፖሊስን ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትችት እንዲጋለጥ አድርጎታል፣ ማንም ቢሆን እስር ቤቶች እንደ ሂልተን ሆቴል መሆን አለባቸው ብሎ ሀሳብ የሚያቀርብ የለም ነገር ግን ማንም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ላይ ተገኝቶ ቅኝት ቢያደርግ እኛ ያደረግነውን ጥረት የሚደግፉ መረጃዎችን ማውጣት ይችላል… የዚህ ሁሉ የመጨረሻ ውጤቱ ሁከት፣ የእስረኞች ፍትህ አልባነትና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብና በሰብአዊ መብት ተሟጋች ደርጅቶች መወገዝ ነው፡፡”

እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 2013 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባቀረበው ዘገባ መሰረት “ባለፉት አስር ዓመታት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ማለትም በዘፈቀደ ማሰርና ማጋዝ፣ ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ ድርጊት እና ማሰቃየት በተለያዩ ህጋዊና ህጋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ውስጥ መፈጸማቸውን በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጠው ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡

ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል ቤት: ኢትዮጵያ እስር ቤት መሆኗን ይመሰላል
ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የእስር ቤቶችን አያያዝ ሁኔታዎች በተመለከተ ገንቢ ትችት ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 2012 ባቀረብኩት ትችት የኢትዮጵያ መንግስት በየፖለቲካ እስረኞች ማጎሪያዎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ ሁኔታ ለማጋለጥ ሞክሪያለሁ፡፡ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 2013 ኢትዮጵያን “በአፍሪካ የፖሊስ ረጋጭ መንግሥት ተምሳሌትነት በመፈረጅ ጠንካራ ትችት አቅርቢያለሁ፡፡ የክርክር ጭብጤንም እንደሚከተለው አቅርቢያለሁ፡፡
  •  “የሌባ ፖሊስ መንግስት ብቸኛ መለያው -- ልዩ መታወቂያው -- በማያቋርጥና በየቦታው የሚፈጽማቸው የዘፈቀደ እስሮች፣ ዜጎችን ማደንና ወደ እስር ቤት ማጋዝ ናቸው፡፡ ማንም ሰው በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣን ስሜታዊ ትዕዛዝ በቀጥጥር ስር ውሎ የሚታሰር ከሆነ ይኸ የፖሊስ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ ከህግ አግባብ ውጭ የዜጎች መብት የሚጣስ ወይም የሚረገጥ ከሆነ ያ በጣም አስቀያሚ የፖሊስ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ የህግ የበላይነት ከህግ በላይ በሆነ ፖሊስ አዛዥ የሚተካ ከሆነ ያ የሌባ ፖሊስ መንግስት ተምሳሌት ነው፡፡”

በዚያ ባቀረብኩት ትችት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ከህግ አግባብ ውጭ የፍተሻ ወረቀት ሳይዙ በሌሊት በግልሰቦች ቤት በመሄድ በሚያካሂዱት ህገወጥ ፍተሻ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በአንዱ ህገወጥ የቤት ፍተሻ ላይ የተደረገው የሚቆጠቁጥ ድርጊት ግን የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊዎች በሙስሊም ዜጎች ቤቶች በመግባት የፈጸሙት የገንዘብ፣ የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ የሃይማኖት መጻህፍትና ሌሎች የግል ቁሳቁሶች ላይ የተደረገው ዝርፊያ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ለሆነ ሰው የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ፕሮግራም ጋዜጠኛ ጠንካራ ጥያቄዎችን በማንሳት ቃለመጠይቅ ሲያቀርብለት እንዲህ የሚል አሳፋሪ ማስፈራሪያ ሰጥቷል፣ “ዋሽንግተንም ሆነ በሰማይ ቤት ብትኖር ደንታዬ አይደለም፣ ከቁብ አልቆጥረውም፣ነገር ግን አዚያው ድረስ መጥቼ አንጠልጥልዬ አመጣሀለሁ፣ ይህን ልታውቅ ይገባል” ብሎ ዛተበት፡፡

እ.ኤ.አ. ጁላይ 2012 ኤርን በርኔት የተባለቸው የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ኢትዮጵያን ከጎበኘች በኋላ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥታለች፡፡
“ባለፈው ወር ኢትዮጵያ በነበርኩበት ጊዜ የፖሊስ መንግስት ምን እንደሚመስል ለመመልከት ችያለሁ… አውሮፕላን ማረፊያው በቆየሁበት ጊዜ የጉምሩክ የስራ ሂደቱን ለማጠናቀቅ አንድ ሰዓት ወስዶብኛል፣ ይህም በሰልፉ መብዛት ምክንያት አይደለም ነገር ግን በፍተሻና በሚቀርቡት ጥያቄዎች መንዛዛት ምክንያት ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣኖች ብዙ ጊዜ በመንግስት መኪናዎች እንድንንቀሳቀስ ይፈልጋሉ፣ ይህም ወዴት እንደምንሄድ ለማወቅ ስለሚፈልጉ ነው፡፡ በመቶሺዎች የሚቆጠር ዶላር ዋጋ ያላቸው የቴሌቪዥን መሣሪያዎች በአውሮፕላን ማሪፊያው ከተውን በኋላ ብቻ ነው ቁጥጥራቸው በመጠኑም ቢሆን መላላት የቻለው፡፡”

የፖሊስ መንግስት ቃለመጠይቅ አንዴት አይነት አንደሆነ በቪደኦ ማየት ይቻላል!?
ሂዩማን ራይትስ ዎች በተቃዋሚ ፖለቲካ እስረኞች ወይም መብታቸውን ለማስከበር በሚጠይቁ ዜጎች ላይ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ዘገባ በማረጋገጥ በየጊዜው ዘገባዎችን እያዘጋጀ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ የሙስሊሙን አመጽ መርቷል በሚል ውንጀላ ተከሶ የተያዘ ወጣት ግለሰብ ቃለ መጠይቅና የእምነት ቃሉን በቪዲዮ በመቅረጽ ህዝብ እንዲያየው ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ከሁለት ዓመት በላይ ጀምሮ መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም በማለት ተቃውሞውን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡

ከታወቁ የዜና ምንጮች መረዳት እንደተቻለው በቪዲዮ የተቀረጸው ቃለ መጠይቅ በማዕከላዊ ምርመራ በአንደ ፖሊስ ወይም ደህንነት ባለስልጣን ቢሮ ውስጥ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በቃለመጠይቅ መስጫው ክፍል ውስጥ ሌሎች ሰዎች የነበሩ ሲሆን የሚሰማው የዋናው ቃል ጠያቂ ድምጽ ነበር፣ (የሌላ ሰው ድምጽ መስማማቱን ለመግለጽ ዋናውን ቃለ መጠይቅ አድራጊ ሲያቋርጠው ለተወሰነ ጊዜ ይሰማ ነበር፡፡)

የቃለ መጠይቅ ማድረጊያው ክፍል ባለመስታወትና ባለፋሽን በር ያለው ነው፡፡ በመሰረቱ ላይ ባለ ነጭ ቀለም መጋረጃ ይታያል፡፡ በጣም ውድ የሆኑ ከውጭ ኢምፖርት ተደርገው የገቡ ባለ ረዥም መደገፊያ በቆዳ የተለበዱ የባለስልጣን ወንበሮች እና ግማሹ የቃለ መጠይቅ ማድረጊያ ክፍል በሶፋዎች ተሞልቶ በካሜራ ሌንሱ ይታያል፡፡ ከተጠርጣሪው ጎን የኢትዮጵያ ካርታ ተሰቅሎ ይታያል፡፡ ቃለ መጠይቁ በጨለማው የማዕከላዊ ምርመራ ክፍል ውስጥ አለመደረጉን ያሳያል፡፡ እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከሆነ ቃለ መጠይቁ የተካሄደው በማዕከላዊ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ቢሮ ውሰጥ እንደሆነ ይገመታል፡፡

በቪዲዮ ቴፑ እንደሚታየው ተጠርጣሪው ሰው ሁለት እጆቹን በካቴና ታስሮ ለጸሎት እንደሚተጋ ሰው መዳፎቹን ከወዲያ ወዲህ ሲያወራጭ ይታያል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለወጣቱ ተጠርጣሪ ዝርዝር ቃለመጠይቅ ሰጠ፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የሚያስጠላ አዛዣዊ ድምጽ የሚያስተላልፍ መሆኑን ያሳብቅበታል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የማስገደድ ዝርዝር ቃለ መጠይቅ ሁኔታ ይታይበት ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በፍርሀትና በለሆሳስ ድምጽ የሚናገረውን ተጠርጣሪ ስለእምነቱና ሌሎችም ጉዳዮች በጥያቄ ያዋክበው ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በሚያስፈራ መልክ ስለሰለፊያ እምነት ምንነትና ስለእስላም አክራሪነት እንዲሁም በሌሎች ላይ ሰለሚኖረው መልካም አስተሳሰብ አደገኛነት ሲጠይቀው ተስተውሏል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን በአሽሙር በመሸንቆጥ ሲያስጨንቀው ታይቷል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን የሙስሊም ትምህርት ቤቶችን ሽፋን በማድረግእሱ እና መሰሎቹ በኢትዮጵያ የእስላም መንግስት ለማቋቋም ጥረት እንደሚያደርጉ ወንጅሎታል፡፡ የተጠርጣሪው ድርጀት የገንዘብ ምንጩ ከየት እንደሆነ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ደጋግሞ በመጠየቅ ሲያባሳጨው ታይቷል፡፡ በቃለ መጠይቅ ሂደቱ ሁሉ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በተጠርጣሪው ላይ ሲያፌዝ፣ ንቀት ሲያሳይ፣ ሲቀልድና በንቀት ሲሳለቅ ታይቷል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪው እንዲናገር ዕድሉን ከሰጠ በኋላ ተጠርጣሪው በማስተባበል መናገር ሲጀምር ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወዲያውኑ በማቋረጥ ያስቆመዋል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወጣቱ ተጠርጣሪ በተስፋቢስነት በረዥም የባለስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጦ ሁለት እጆቹን በካቴና ታስሮ ቃለ መጠይቅ አድራጊውን በአክብሮት ዓይን እያየ በለሆሳስ ቅላጼና በጉልህ በማይሰማ ድምጽ በሚናገርበት ጊዜ የበላይነት ስሜት ያንጸባርቅበታል፣ ይረብሸዋል፣ እንዲሁም በተለየ መልኩ ያንቋሽሸዋል፡፡

እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከሆነ በቪዲዮው ላይ የተደበቀ ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል የተቀረጸው የቪዲዮ ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ለመደብደብ ወደ ኋላ በማይሉ ዝቅተኛ የፖሊስ ባለስልጣኖች በማለሳለስና ተገድዶ ላመነው የቪዲዮ ቀረጻ ተባባሪ እንዲሆን በማድረግ ሙሉ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ነበር፡፡ የቪዲዮ ቀረጻ ቃለ መጠይቁ በሚደመጥበት ጊዜ ሌሎች የፖሊስ አባላትና የሲቪል ሰራተኞች እንዲገኙ ተደርጓል፡፡ እንዲገኙ የተደረገበት ዋና ዓላማም ጉዳዩ ለፍርድ ቤት በሚቀርብበት ጊዜ ተጠርጣሪው ግለሰብ ያለምንም ተጽዕኖ በእራሱ ፈቃድ አምኖ የተናገረው መሆኑን መመስከር እንዲችሉ ለማመቻቸት ነው፡፡ (በቪዲዮ የተቀረጸውን ቃለ መጠይቅ ቅጅ ለተከላካይ ጠበቆችም ሆነ ለፍርድ ቤቱ የተሰጠ ነገር የለም፡፡) ቃለ መጠይቁ የተቀረጸው የፖሊስ ማስፈራሪያነት በሌለበትና ከጣልገብነት ነጻ በሆነ መልኩ በተረጋጋና በጥሩ የንግግር ቅላጼ መሰረት ተደርጎ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በመስክ ላይ እንደሚፈነዳ ደማሚት ተደርገው በዘዴ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ጥያቄ አቅራቢው ተጠርጣሪው የየትኛው ድርጅት አባል እንደሆነ፣ ምን ፍልስፍና እንደሚከተል፣ እነማን ደጋፊዎቹ እንደሆኑ፣ የገንዝብ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ፣ የተከሰሰበት ወንጀል ምን እንደሆነና የመሳሰሉት አጠቃላይ ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ተጠርጣሪው ድርጊቱን ለመፈጸሙ ሊያሳምን በሚችል መልኩ ተያያዥነት ያላቸው በሚመስል መልኩ ሌሎች ሁለተኛ ዙር ጥያቄዎች ይከተላሉ፡፡ ለምሳሌም ተጠርጣሪውን ለምንድን ነው የዚህ ድርጅት አባል የሆንከው? አባል ሆኖ ምን ሚና እንደተጫወተ እንዲሁም እነዚህን የተወነጀለባቸውን ድርጊቶች ለምን ሪፖርት እንዳላደረገና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ይጠየቃል፡፡ የቪዲዮ ቃለ መጠይቁ ተጠርጣሪው የወንጀል ድርጊቱን መፈጸሙን ለማመኑ ትክክለኛ መረጃና ለእራሱ መስቀያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ዋና የፖሊስ መርማሪዎች ጭካኔና አስገዳጅነት የተሞላበትን በቪዲዮ የተቀረጸ ቃለ መጠይቅ ያለበት የምርመራ ውጤት ማስቀረት አይፈልጉም፡፡ የውስጥ አዋቂ ምንጭች ተጠርጣሪው ወጣት እጆቹን በካቴና ታስሮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ መደነቃቸውን ይገልጻሉ፡፡ እጁን በካቴና ታስሮ ለአንድ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣን ቃለመጠይቅ የሚሰጥ ተጠርጣሪ የጥያቄና መልስ ሂደት በቪዲዮ ቴፕ ተቀርጾ ማየት በጣም አስደንጋጭ ከመሆኑም በላይ እንደ አንዳንድ የውስጥ ምንጮች ተጠርጣሪውን ወጣት በካቴና አስሮ ቃለ መጠየቅ ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ እንዲሁም የቪዲዮ ቀረጻ ቃለ መጠይቁ መንግስት በተቃዋሚ የፖለቲካ ደርጅቶች ላይ የስነ ልቦና ጦርነት በማካሄድና በማስፈራራት ረገድ ጠቀሜታ ያስገኝለታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ ሁኔታ ተጠርጣሪዎችን በማስፈራራትና በማሸማቀቅ ለተቃዋሚ ኃይሎችና ለአመጸኞች ማዳከሚያ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ በጥንካሬና በጽናት የተሞሉ ወጣት የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል መዳፍ ስር ወይም መንጋጋ ከገቡ ፍርሀትና መደናገጥ አንደሚታይባቸው ለሕዝብ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የተቃዋሚ ድርጀት መሪዎች ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል ከደረሱ እንደሚሰባበሩ፣ እንደሚደቆሱ፣ እንደሚታኘኩና እንደሚበጣጠሱ የማያዳግም መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴ ነው፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ከሆነ ተገዶ ማመን አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ሳይወዱ በግድ መንግስትን እንዲደግፉ የሚደረጉበት ዘዴ ነው፡፡

ይህም ሆኖ በቪዲዮ የተቀረጸውን የቃለ መጠይቅ አድራጊውን ሙሉና የተጠርጣሪውን መብት በመጣስ ለእይታ የበቃውን ድራማ መመልከት “በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች በፍርድ ቤት ወንጀለኛነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ናቸው፣ እንዲሁም ተገደው በእራሳቸው ላይ ምስክርነት አይሰጡም“ የሚለውን ህገመንግስታዊ መብት የጣሰ የማይታመንና አስደንጋጭ ሁኔታ ነው (አንቀጽ 20(3) ፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የወጣቱን ተጠርጣሪ ህገመንግስታዊ መብት በኮርማ እንደተናደ የሴራሚክ ቁልል ደፍጥጦታል፡፡ ወጣቱ ተጠርጣሪ “ያለመናገር መብት“ እንዳለው በግልጽ የተቀመጠውን ህገመንግስታዊ መብት ቃለ መጠይቅ አድራጊው ከቁብ የቆጠረው አይመስልም (አንቀጽ 19(2)(5) ፡፡ “በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ያለመናገር መብት አላቸው፡፡ በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ተገደው የእምነት ቃል እንዲሰጡ አይደረግም ተገደው የሰጡትም ቃል ለማስረጃነት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማንኛውም ማስረጃ በህግ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡” ቃለ መጠይቁ በሚደረግበት ጊዜ የተጠርጣሪው የህግ ጠበቃ እንዲገኝ አለመደረጉ ቃለ መጠይቅ አድራጊውን የሚያሳስበው አይመስልም (አንቀጽ 20(5)፣ አንቀጽ 21(2) ፡፡ “የተከሰሱ ሰዎች የህግ ጠበቃቸው የመጎብኘትና… ከህግ ጠበቃቸው ጋር የመመካከር መብት አላቸው፡፡“ “ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ጥላ ስር የዋለው ተጠርጣሪ ስለቀረበበት ክስ አስቀድሞ በቃለ መጠይቅ አድራጊው አልተገለጸለትም፡፡“ አንቀጽ 20(2) “የተከሰሱ ሰዎች ስለቀረበባቸው ክስ ዝርዝር መረጃ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀና ይህም በጽሁፍ ሊደርሳቸው ይገባል፡፡“

ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን ከየትኛው የእስልምና እምነት ክፍል እንደሆነ በማስፈራራት መረጃ ለማግኘት ሞክሯል፣ ለማስረዳትም ጥረት አድርጓል፣ አክራሪነት የየትኛው የእስልምና አስተምህሮ እንደሆነና ተጠርጣሪው ይህንን አውግዞ መንግስት የሚፈልገውን እንዲመርጥ በመጠየቅ የተጠርጣሪውን መብት ደፍጥጦታል፡፡ አንቀጽ 27(1)(3) “እያንዳንዱ ሰው የራሱ የእምነት ነጻነት አለው… ይህ መብት ግለሰቡ የመረጠውን ኃይማኖት በግሉ ወይም ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ የመከተልና የማራመድ መብትን ጭምር ያጠቃልላል… (3) ማንም የመረጠውን የራሱን እምነት ለማራመድ የሚያግደው ወይም የሚከለክለው የለም፡፡“ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለተጠርጣሪው ስለኃይማኖት እንቅስቃሴውና ስለእምነት ምርጫው ሲጠይቅ “ተጠርጣሪው በግል ወይም ከሌሎች ጋር በጋራ በመሆን የመሰብሰብ፣ የጦር መሳሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና አቤቱታ የማቅረብ መብት” (አንቀጽ 30(1) እንዳለው የተረዳ አይመስልም፡፡ በአጭሩ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የተጠርጣሪውን መብት የደፈጠጠው ህገመንግስቱ ያጎናጸፈውን የኢትዮጵያን ህገመንገስት በመጣስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ደንቦችን በመናድ ጭምር ነው፡፡

ጥፋተኝነትን ለመከላከል የአሜሪካ ህገመንግስት 5ኛ ማሻሻያ
ጥፋተኝነትን መከላከል ወይም ያለመናገር መብት የአሜሪካ ህገ መንግስት ለዜጎቹ ያጎናጸፋቸው ዋነኛ የመብት ስብስቦች ናቸው፡፡ ማንም ሰው “በማንኛውም የወንጀል ጉዳይ ተገዶ ምስክርነት እንዲሰጥ አይደረግም“ በማለት አምስተኛው የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያ ይደነግጋል፡፡ ከእንግሊዝ ተሰደው አሜሪካንን በቅኝ ግዛትነት የያዟት የስነምግባር ሰዎች ናቸው ይህንን የተገበሩት፡፡ ምክንያቱም በእምነታቸው ሰዎች ሲጠየቁ ዝም የማለት ወይም በጌቶቻቸው ስቃይ ተገድደው መልስ ያለመስጠት መብት እንዳላቸው የጸና እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡ የበላይ ጠያቂ ጌቶች ብዙውን ጊዜ ደጋጎቹን የእምነት ሰዎች የያዙት እምነት ምን እንደሆነ እንዲያምኑ ያስገድዷቸውና ያሰቃዩአቸው ነበር፡፡ ዝም ካሉና ካልተናገሩ ጥፋተኛ ብለው ይፈርጇቸው ነበር፡፡ የእንግሊዝ ህግ በ1600ዎቹ አጋማሽ ጥፋተኝነትን የመከላከል መብት ለዜጎቹ አጎናጽፏል፡፡

ይህ እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል የተቀደሰ መብት የአሜሪካ የወንጀል መከላከል ህግ መሰረት ነው - ማንም የተከሰሰ ሰው ጥፋተኝነቱ ባስተማማኝ ሁኔታ ከጥርጣሬ ባለፈ መልኩ በመንግስት እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ነው፡፡ ጥፋተኛ መሆን አለመሆኑን የማረጋገጡ ተግባር ደግሞ የመንግስት፣ የአቃቢያን ህግና የፖሊስ ነው፡፡ የተከሰሰን ሰው ጥፋተኝነት ለማረጋጥ የተከሰሰው ግለሰብ ምንም ነገር ማድረግ የለበትም፣ በተለይም ከፖሊስ ወይም ከአቃቤ ህግ ጋር መነጋገር ወይም መተባበር ግዴታ የለበትም፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትም ሆነ የአካባቢ ፖሊስ የአሜሪካንን ዜጋ በማስገደድ ለጥፋተኝነታቸው ማስረጃ የሚሆኑ መግለጫዎችን እንዲሰጥ/እንዳይሰጥ ወይም እንዲያምን/እንዳያምን ማድረግ አይችሉም፡፡

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርደ ቤት የፖሊስን አስገዳጂ የምርመራ ቃለ መጠይቅ ተግባር ያቆመው እ.ኤ.አ. በ1966 ነው፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የህግ መብት ማስጠንቀቂያ“ ለተባለ ቀላል የአሰራር ሂደት ኃላፊነት ሰጥቷል፡፡ በተግባር ሲታይ ይህ የፖሊስ ምርመራ የህግ መብት ፖሊስ ምርመራ ሊያደርግ በሚፈልግበት ጊዜ ተጠርጣሪውን/ዋን በቢሮው ወይም የተጠርጣሪውን/ዋን ነጻነት ሊያውክ በማይችል ሁኔታ መሆን እንዳለበት፣ ተከሳሹ/ሿ ዝም የማለት መብት እንዳላቸው፣ በተጠርጣሪው/ዋ የተሰጠው ምስክርነት ለተጠርጣሪው/ዋ ማስረጃነት ሊውል እንደሚችል፣ተጠርጣሪው/ዋ ከመጠየቁ/ቋ በፊት ከህግ አማካሪው/ዋ ጋር የመምከር መብት እንዳለው/ላት እና ተጠርጣሪው/ዋ የህግ ጠበቃ ለማቆም አቅም ከሌለው/ላት መንግስት ምርመራ ከመጀመሩ በፊት ጠበቃ እንደሚያቆም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ሆኖም ግን ድርጊቱ ሆን ተብሎ በማወቅ የተፈጸመ ከሆነ፣ ወይም ከስለላ ስራ ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ ወይም አንድን ዓላማ ለማሳካት መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ከሆነ ወይም በፖሊስ ህገወጥ የምርመራ ዘዴ የተገኘ መረጃ ከሆነ እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል መብት ወይም የህግ የምክር አግልግሎት የማግኘት መብትን ያስነሳል፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን “ሚራንዳህ ወይም በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የህግ መብት በቀን ተቀን የፖሊስ ምርመራ ተግባራት ሁሉ እንዲካተት አውጇል፣ ማስጠንቀቂያዎቹም አገር አቀፋዊ ባህል ሆነው እስኪሰርጹ ድረስ ይሰራል”፡፡

በአሜሪካ ህገ መንግስት አምስተኛ ማሻሻያ የተሰጠውን እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል መብት መከላከል እንድችል የህግ ባለሙያነቴ የሰጠኝ መብት በኩራት እንድሞላ አድል ደርሶኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1998 በህዝብና በፒቪ መካከል በነበረው ጉዳይ የሚራንዳህ የህግ ስርዓት ታስቦበትና ሆን ተብሎ የምስክርነት ማስረጃው (ጥፋተኝነትን አስገደድዶ መቀበል፣ በግዳጅ ማሳመን) በመጣሱ በካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቤ ሽንጤን ገትሬ በመከራከር ማስቀየር በመቻሌ ልዩ ክብርና ሞገስ ይሰማኛል፡፡ በዚያን ወቅት በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኙ የፖሊስ መምሪያዎች ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ ያለመናገርና የህግ ባለሙያ የማናገር መብት እንዳላቸው እየታወቀ ፖሊስ አፋጥጦ በመጠየቅ መረጃን የማግኘት ጥረቱ በጊዜው በነበረው አሰራር ተቀባይነት ነበረው፡፡ ይህ በተወሰኑ የፖሊስና አቃብያነ ህጎች ክልል ወስጥ ይደረግ የነበረው ህገወጥ የአጠያየቅ ስርዓት “ከሚራንዳህ ህግ ውጭ” በመባል ይታወቅ ነበር፡፡

በካሊፎርኒያ ግዛት በፒቪ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት “ከሚራንዳህ ምርመራ ውጭ“ የሚደረግ የምርመራ አሰራር በፍፁም አንዲቆም ተደረገ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2000 ዘጠነኛው የተዘዋዋሪ ችሎት በሲኤሲጀ እና በሳንታ ሞኒካ ከተማ ተካሂዶ ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ ያለመናገር መብት እንዳላቸው እየታወቀ ይህንን ጥሰው ከሚራንዳህ የምርመራ ህግ ውጭ አስገድዶ ለማሳመን እና ጥፋተኝነትን እንዲቀበሉ ብለው የሚፈጽሙ ፖሊሶች በህገ መንግስቱና በሲቪል ህዝቡ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በግል ተጠያቂና ተከሳሽ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

በማስገደድና በማሰቃየት የተገኘ የእምነት ቃል ፍትሀዊም ተዓማኒነትም የለውም
በወንጀል መከላከል ህግ ተጠርጣሪውን/ዋን አስገድዶ በማሳመን ጥፋተኛ በማድረግ የተገኘ መረጃን ያህል ትኩረትን የሚስብ ነገር የለም፡፡ ፖሊስ ምርመራ የሚያደርግበት ዋና ዓላማ እውነታው ላይ ለመድረስ ወይም ተጠርጣሪው ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ አይደለም፡፡ ብቸኛውና ዋናው ዓላማ የጥፋተኝነት መግለጫዎችን እና የእምነት ቃል ከተጠርጣሪው አንደበት ለመስማትና ይህንን መሰረት በማድረግ በተከሳሹ/ሿ ላይ ክስ ለመመስረት እንዲቻል ነው፡፡ በማስገደድ የፖሊስ ምርመራ ሂደት ጊዜ ተጠርጣሪው ከጥፋተኝነት ነጻ መሆኑን በራሱ አንደበት መግለጽ ይጠበቅበታል፣ ወይም ደግሞ ጥፋተኛ ተብሎ እንዲወሰንበት መንግስትን በማገዝመተባበር ይጠበቅበታል፡፡ “የፖሊስ የበላይነት” በተንሰራፋበት አካባቢ እራስን ጥፋተኛ አድርጎ ማቅረብ ሜዳውን ለእብሪተኛና ለመሰሪ ፖሊሶች ምርመራ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ዜጎችን ለፍትህ እጦት ሰለባ ያደርጋል፡፡

የተጠርጣሪው ወይም የተከሳሹ በፖሊስ ምርመራ ሂደት ዝም የማለት መብት የጥፋተኝነትና የቅጣት ሰለባ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት አንጻር ብዙ አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ ዋናው ጠቃሚ ነገር ፍትሀዊነት ነው፡፡ በሙያው የሰለጠነ የምርመራ ፖሊስ የህግ ጥሰት ፈጽሟል ባለው ተጠርጣሪ ዜጋ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያቀርብ በመፍቀድ የግዳጅ የእምነት ቃል ማግኘት በምንም መልኩ ፍተሀዊነትን አያሳይም፡፡ የማስገደድ የምርመራ ዘዴ ፍትሀዊነት በጎደለው መልኩ ሕገመንግስታዊ የማስረጃ ማቅረብን ግዴታ ከመንግስት ከሳሽ አጅ ወደ ተጠርጣሪው እንዲዞር ያደርጋል፡፡ ተጠርጣሪው ፍትህን በአግባቡ ማግኘት እንዲችል ከተፈለገ በፖሊስ የምርመራ ሂደት ጊዜ ተጠርጣሪው የምክር አግልግሎት እንዲያገኝ የህግ ባለሙያ እንዲያገኝ የማድረጉ ሂደት ጠቃሚነቱ የጎላ ነው፡፡ የተጠርጣሪውን የህግ ጉዳይ ፍሬ ነገሩን የተጠርጣሪው የህግ አማካሪ ሳያየው ተጠርጣሪውን ወይም ተከሳሹን በፖሊስ እንዲመረመር ማስገደድ ተገቢነት የለውም፡፡ ለማንኛውም የምርመራ ጥያቄ ተጠርጣሪው ምን መልስ መስጠት እንዳለበትና መልስ መስጠት የሌለባቸውን ጉዳዮች የህግ ባለሙያው ካጠናው በኋላ የተጠርጣሪው የህግ አማካሪ መንግስት ምን መረጃ እንደሚፈልግና ምን መከላከያ ማስረጃዎች እንዳሉ ማወቅ አለበት፡፡

በማሰቃየት ወይም ማንኛውንም የሰብአዊ መብት ረገጣ ዘዴዎች በመጠቀም የተገኘ የእምነት ቃል በምንም ዓይነት ሁኔታ አስተማማኝ መረጃ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ተጠርጣሪዎች በመርማሪ ፖሊሶች የሚደርስባቸውን የአካልና የአዕምሮ ስነ ልቦና ስቃይ ለማቆም ሲሉ ያልሰሩትን ነገር እንደሰሩ አድርገው የእምነት ቃል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ምግብ፣ ውኃና የመኝታ አገልግሎት የተነፈጉ ተጠርጣሪዎች ግራ በመጋባትና ስቃዩን በማስቀረት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሲሉ የእምነት ቃል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ነጻ የሆኑ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ምርመራ ጊዜ ሲጠየቁ ከክሱ ነጻ የሚያወጣቸው እየመሰላቸው ስለእውነት ብቻ ይናገራሉ፡፡ በመሰሪ ፖሊሶች የሚዘረጉላቸውን አሽክላዎች አይገነዘቡም፡፡ እውነቱን መናገር ነጻ የሚያደርጋቸው ይመስላቸዋል፣ ሆኖም ግን ብዙውን ጊዜ እውነታው በተቃራኒው በሰለጠኑ የፖሊስ መርማሪዎች ተጠምዝዞና ተፐውዞ ተጠርጣሪውን ለማዳካም ሲባል ፖሊስ አደናጋሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ፣ በማስፈራራት፣ በመዛትና በማታለል ዓላማውን ለማሳካት ጥረት ያደርጋል፡፡ ነጻ የሆኑ ሰዎች የማያቋርጥ ለሰዓታት የዘለቀ የፖሊስ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ያልሰሩትን ወንጀል እንደሰሩ (የሀሰት የእምነት ቃል) የሚያያረጋግጡ ብዙ ማህበራዊና ሳይንሳዊ ጥናቶች አሉ፡፡ በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የተጠርጣሪው ዝምታ በዓለም ላይ ከወርቅ፣ ፕላቲኒየም፣ የተከበረ ድንጋይ ወይም አልማዝ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡

ማስመሰል ለምን? ጨካኔንና ተያቂ አልባነትን መፍጠር
በ15ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ አገር በተራ ፍርድ ቤቶች ሊከሰሱ የማይችሉና በጣም ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ የሚያይ ተጠያቂነት የሌለው ፍርድ ቤት (በፍርድ ቤቱ ጣሪያ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበት) ተመሰረተ፡፡ ይህ ፍርድ ቤት በሚስጥርና የህግ ሂደትን ሳይከተል ምስክሮቸን ሳይሰማ ብይን ይሰጥ ነበር፡፡ በመጨረሻም ንጉሱ ይህን ተጠያቂነት የሌለው ፍርድ ቤት ተፎካካሪያቸውን፣ ተቃዋሚዎቻቸውን እና ትችት የሚያቀርቡባቸውን አካላት ጸጥ ለማድረግና ለማስወገድ ሲሉ ወደ ማጥቂያ ህጋዊ መሳሪያነት አሸጋገሩት፡፡ ገዥው የኢትዮጵያ አስተዳደርም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የራሱን ተጠያቂ አልባ የፔንታጎን ቅርጽ ያለው ፍርድ ቤት በማቋቋምና በጣራው ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን ባንዲራ በመስቀል ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ህግ የማያከብር መንግስት የማስገደድ እምነት፣ ለህግ ንቀትን የሚፈለፍል ገዥ
የራሱን ህገመንግስት መረን በለቀቀ አኳኋን የሚደፈጥጠውን አገዛዝ ሁኔታ ሁልጊዜ ባሰብኩ ቁጥር እንቆቅልሽ ይሆንብኛል፡፡ ሁልጊዜ ህገመንግስታችን እየተባለ በመንግስት መሪዎች የሚለፈፈው እርባናየለሽ ዲስኩር ከማሳቁም በላይ ምንም እውቀቱ ሳይኖረው ከቅዳሳን መጽሐፍት እየጠቀሰ የሚያነበንበውን የኃይማኖት ደቀመዝሙር እና ምን እንደሚልና ምን እንደሚያደርግ ትርጉም ያለው እውቀት ሳይኖረው በዘልማድ ባህላዊ ባላትን ለማክበር ሽርጉድ የሚለውን ባተሌ እንዳስታውስ ያደርገኛል፡፡ “ሰይጣን ለዓላማው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል“ የሚለውን የሸክስፒርን ስንኝ እንዳስታውስም ያደርገኛል፡፡ የስርዓቱ ገዥዎች ህገመንግስቱን ከአደጋና ከተቃዋሚዎች ጥቃት ለመጠበቅ ከነፋስ የፈጠኑ ናቸው፣ የራሳቸውን ህገመንግስት እራሳቸው በመጣስ ዋጋውን እንዲሚያሳንሱት በውል የተረዱት አይመስልም፡፡ ለዓመታት ደጋግሜ እንደተናገርኩት ለኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች ስለህገ መንግስት ወይም የህግ የበላይነትን መስበክ ለተሰበሰቡ አረማውያን (አህዛብ) መጽሐፍ ቅዱስን እንደመስበክ ወይም በጥቁረር ባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡ በቅርቡ የወጣው የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ገዥው ስርዓት ስለ የህግ የበላይነት ያለውን ጥልቅ ንቀት በጉልህ ያሳያል፡፡

በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚገኙ ታላላቅ የህግ ዳኞች አንዱ የሆኑት ሌውስ ብራንዴስ እንዳመለከቱት “ህግ ባለበት መንግስት አገር መንግስት ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ የህግ ጥበቃ ካላደረግ የመንግስት ህልውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ መንግስታችን ጠንካራና በየትም ቦታ የሚገኝ መምህር ነው፡፡ ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ነገር እራሱን ምሳሌ አድርጎ ለህዝቡ ያስተምራል፡፡ ወንጅል ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ መንግስት እራሱ ህግ የሚጥስ ከሆነ ለህግ ያለውን ንቀት ይፈለፍላል፣ እያንዳንዱ ዜጋ እስከ እራሱ ድረስ ህግ እንዲጥስ ይጋብዘዋል፣ ስርዓተ አልበኝነት እንዲነግስ ይገፋፋል፡፡ የወንጀል ህግን ከማስተዳደር አንጻር ዓላማው ፍጻሜውን ሊያሳምር ይገባል፡፡ የግል ወንጀለኛን ለመዳኘት ሲል መንግስት እራሱ ወንጀልን የሚፈጽም ከሆነ አደገኛ በቀልተኝነት ይሆናል፡፡“ ብራንዴስ “በመንግስት በኩልየግል የስልክ መስመሮችን በመጥለፍ የስለላ ስራ በማካሄድ የእራስን የጥፋተኝነት መረጃ ለማቅረብ የሚደረግ አሰራር ህገወጥ ነው“ በማለት ሀሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

ገዥው አስተዳደር ህግን የሚጥስ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? ህገመንግስት ደፍጣጭ ሲሆን? ገዥው አስተዳደር ለህግ የማይገዛ ወንበዴ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? ህግን የማያከብርና የሚደፈጥጥ ገዥ አስተዳደር ህግን በሚያከብር መንግስት መተካት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ መንግስት ይቃወሙኛል የሚላቸውን ከህግ ውጭ እያስገደደና እያሰቃየ በማሳመን የሚያገኘው የእምነት ቃል ሳያውቀውና ሳይገነዘበው ቀስ በቀስ እራሱ ህግ አልባ ለመሆኑ የእምነት ቃል መስጠቱን ይመሰክርበታል፡፡

“ጤናማ ሰው ሌሎቹን አያሰቃይም- በአጠቃላይ ሲሰቃዩ የነበሩ ወደ አሰቃይነት ይቀየራሉ፡፡” ካርል ጁንግ

Saturday, October 19, 2013

Ethiopia: Political Detainees Tortured


                                                          
Police Abuse Journalists, Opponents to Extract Confessions
(Nairobi) – Ethiopian authorities have subjected political detainees to torture and other ill-treatment at the main detention center in Addis Ababa. The Ethiopian government should take urgent steps to curb illegal practices in the Federal Police Crime Investigation Sector, known as Maekelawi, impartially investigate allegations of abuse, and hold those responsible to account.

The 70-page report, “‘They Want a Confession’: Torture and Ill-Treatment in Ethiopia’s Maekelawi Police Station,” documents serious human rights abuses, unlawful interrogation tactics, and poor detention conditions in Maekelawi since 2010. Those detained in Maekelawi include scores of opposition politicians, journalists, protest organizers, and alleged supporters of ethnic insurgencies. Human Rights Watch interviewed more than 35 former Maekelawi detainees and their relatives who described how officials had denied their basic needs, tortured, and otherwise mistreated them to extract information and confessions, and refused them access to legal counsel and their relatives.

“Ethiopian authorities right in the heart of the capital regularly use abuse to gather information,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Beatings, torture, and coerced confessions are no way to deal with journalists or the political opposition.”

Since the disputed elections of 2005, Ethiopia has intensified its clampdown on peaceful dissent. Arbitrary arrest and political prosecutions, including under the country’s restrictive anti-terrorism law, have frequently been used against perceived opponents of the government who have been detained and interrogated at Maekelawi.

Maekelawi officials, primarily police investigators, have used various methods of torture and ill-treatment against those in their custody. Former detainees described to Human Rights Watch being slapped, kicked, and beaten with various objects, including sticks and gun butts, primarily during interrogations. Detainees also described being held in painful stress positions for hours upon end, hung from the wall by their wrists, often while being beaten.

A student from Oromiya described being shackled for several months in solitary confinement: “When I wanted to stand up it was hard: I had to use my head, legs, and the walls to stand up. I was still chained when I was eating. They would chain my hands in front of me while I ate and then chain them behind me again afterward.”

Detention conditions in Maekelawi’s four primary detention blocks are poor but vary considerably. In the worst block, known as “Chalama Bet” (dark house in Amharic), former detainees said their access to daylight and to a toilet were severely restricted, and some were held in solitary confinement. Those in “Tawla Bet” (wooden house) complained of limited access to the courtyard outside their cells and flea infestations. Investigators use access to basic needs and facilities to punish or reward detainees for their compliance with their demands, including by transferring them between blocks. Short of release, many yearn to be transferred to the block known as “Sheraton,” named for the international hotel, where movement is freer.

Detainees held in Chalama Bet and Tawla Bet were routinely denied access to their lawyers and relatives, particularly in the initial phase of detention. Several family members told Human Rights Watch that they had visited Maekelawi daily but that officials denied them access to their detained relative until the lengthy investigation phase was over. The absence of a lawyer during interrogations increases the likelihood of abuse, and limits the chances for documenting abuse and obtaining redress.

“Cutting detainees off from their lawyers and relatives not only heightens the risk of abuse but creates enormous pressure to comply with the investigators’ demands,” Lefkow said. “Those in custody in Maekelawi need lawyers at their interrogations and access to their relatives, and should be promptly charged before a judge.”

Human Rights Watch found that investigators used coercive methods, including beatings and threats of violence, to compel detainees to sign statements and confessions. These statements have sometimes been used to exert pressure on people to work with the authorities after they are released, or used as evidence in court.

Martin Schibbye, a Swedish journalist held in Maekelawi in 2011, described the pressure used to extract confessions: “For most people in Maekelawi, they keep them until they give up and confess, you can spend three weeks with no interviews, it’s just waiting for a confession, it’s all built around confession. Police say it will be sorted in court, but nothing will be sorted out in court.”

Detainees have limited channels for redress for ill-treatment.  Ethiopia’s courts lack independence, particularly in politically sensitive cases. Despite numerous allegations of abuse by defendants, including people held under the anti-terrorism law, the courts have taken inadequate steps to investigate these allegations or to protect defendants complaining of mistreatment from reprisals.

The courts should be more proactive in responding to complaints of mistreatment, but that can happen only if the government allows the courts to act independently and respects their decisions, Human Rights Watch said.

Ethiopia has severely restricted independent human rights investigation and reporting in recent years, hampering monitoring of detention conditions in Maekelawi. The governmental Ethiopian Human Rights Commission has visited Maekelawi three times since 2010 and publicly raised concerns about incommunicado detention. However, former detainees told Human Rights Watch that Maekelawi officials were present during those visits, preventing them from talking with commission members privately, and questioned their impact.

Improved human rights monitoring in Maekelawi and other detention facilities requires revision of two repressive laws, the Charities and Societies Proclamation and the Anti-Terrorism Proclamation. These laws have significantly reduced independent human rights monitoring and removed basic legal safeguards against torture and ill-treatment in detention.

Ethiopia’s constitution and international legal commitments require officials to protect all detainees from mistreatment, and the Ethiopian authorities at all levels have a responsibility both to end abusive practices and to prosecute those responsible. While the Ethiopian government has developed a three-year human rights action plan that acknowledges the need to improve the treatment of detainees, the plan does not address physical abuse and torture; it focuses on capacity building rather than on the concrete political action needed to end the routine abuse.

“More funds and capacity building alone will not end the widespread mistreatment in Maekelawi and other Ethiopian detention centers,” Lefkow said. “Real change demands action from the highest levels of government against all those responsible to root out the underlying culture of impunity.”

Wednesday, October 16, 2013

ዓረና ትግራይንና አንድነት ፓርቲን በመደገፋቸው የከተማዋን ኗሪ ቀስቅሳችሃል በሚል በጽጥታ ሃይሎች የተያዙ ወጣቶች ያሉበት አድራሻ እስካሁን ድረስ አልታወቀም

ወጣቶቹ የፈጸሙት ምንም ዓይነት ወንጀል ባይኖርም ዓረና ትግራይንና አንድነት ፓርቲን በመደገፋቸው የከተማዋን ኗሪ ቀስቅሳችሃል በሚል መስከረማ 27,2006 ዓ/ም በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው የተወሰዱ ዜጎች እስካሁን ድረስ ያሉበት አድራሻ በትክክል ካለመታወቁም በላይ የቀረበባቸው ክስ የለም፣ ከታፈኑት ዜጎች መካከል መምህር ስዓረ ፤ እንጂነር ነጋሲ ገብሩ፤ አቶ አንገሶም ተስፋይና ወ/ሮ ቅዱሳን ኣብርሃ (ነባር ታጋይ) ይገኙበታል፣ ይህ በእንዲህ እያለ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 03 ከጀርመን የህክምና ማEከል አከባቢ ዓረና ትግራይ አዲስ መስከረም 24,2006 ዓ/ም ጽ/ቤት የከፈተ ሲሆን በስነስርዓቱ በርካታ የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ተገኝቶ እንካን ደህና መጣችሁ በማለት በጽ/ቤት በከፍተኛ ክብር የባንዴራ ማውጣት ስነስርዓት ተሳትፋል፣ በመክፈቻው ስነስርዓት አምባገነኑ የIህአዴግ መንግስት ይውረድ ! ፤ ሙስና ይወገድ! ህጋዊና ዴሞካሲያዊ ስርዓት ይመስረት! የሚሉ ወቅታዊ መፈክሮች በጽ/ቤት በግልጽ ይታዩ ነበር::

Monday, October 14, 2013

Dictatorship prisoners



The film about journalists Martin Schibbye and Johan Persson, who was imprisoned in Ethiopia and was sentenced to eleven years in prison here.


The Swedish journalists Martin Schibbye and Johan Persson was shot and arrested when attempting to illegally enter the Ogaden region of Ethiopia to report on conditions there. For four days, they were kept in the desert where they were forced to participate in a film that would be used as evidence against them. The interrogations were harsh and they suffered, among other things, a mock execution. They eventually sentenced by an Ethiopian court to eleven years in prison but was released after just over a year ago they asked the government for clemency.

Abdullahi Hussein was the regional president's adviser and head of the Ogaden TV channel Cakaara News. He had responded to the abuses and atrocities against civilians and for a few years he copied the president's secret video files. Files included the internal meetings where individual officers and soldiers in the regional militia testify arbitrary arrests, torture, murder, extortion and rape.Abdullahi Hussein planned to escape from Ogaden and share its evidence to the international media and human rights organizations.
Abdullahi was with the president when John and Martin were arrested and he was able to follow the course of events in the desert from the "other side". When he got the film material from the desert in his hand, he decided that it was time to leave the Ogaden.
In the documentary film Dictatorship prisoners, directed by Andreas Rocksén , gives John, Martin and Abdullahi a frightening picture of the Ogaden, a region that has become increasingly attractive for international oil and mineral companies, among them the Swedish Lundin Group.

Friday, October 11, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወሰዱ

በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

ጉዳዩ እንደዚህ ነው መንግስት ነኝ ባዩ በስራው ግን ከማፍያ ቡድን እምብዛም የማይለየው ህወሀት/ኢህአዴግ በተለየም የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ አጠናክረው የቀጠሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ስጋት ውስጥ ጥሎታል።
“ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ይህን ህዝብ ውስጥ በፍጥነት እየሰረጸ የመጣውን እንቅስቃሴ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ለማዳከምና ብሎም ለማምከን ህወሀት/ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ስልት ቡድኑ ምን ያህል “የሞራል የበታችነት” እንደተላበሰ የሚያሳይ ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ የተከራየውን ጽህፈት ቤት ለመረከብ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም በቦታው ይገኛል። ይሁንና ቀድመው በቦታው የተገኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ሰዎች ቤቱን እኛ ቀደም ብለን የተከራየነው ስለሆነ የሚገባው ለኛ ነው በማለት ወዝግብ ያነሳሉ… እንግዲህ አንባብያን እራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራው ሀይል የሰፈር “ጢቦ” ሆኖ መጣ ማለት ነው…
ይህ በዚህ እንዳለ ነው አሁን በቅርቡ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን ኢንጅነር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችችን ወደ ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዷቸው።
የሰማያዊ ፓርቲ ሁኔታውን እንዲህ በማለት በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ ጠቅሶታል፣
የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር) 
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ) 
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል) 
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)

አንዷለም አራጌ ለህገ ወጥ ድርጊት ባለመተባበሩ ጎብኚ እንዳይኖረው ተደረገ

በሽብርተኝነት ተከስሶ ዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖበት በቃሊቲ ቅጣት ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ በጎብኚዎች እንዳይታይ መደረጉ አንድነት ፓርቲን አሳስቧል፡፡አንዷለም ፍርድ ከተላለፈበት በኋላ በማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ከጨረሱ እስረኞች ጋር መቀላቀል ይገባው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ሆን ተብሎ እርሱን ለመጉዳት ጊዜያዊ እስረኞች በሚገኙበት ‹‹ቅጣት ቤት ››ውስጥ እንዲታሰር መደረጉም ህገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል፡፡
993428_527514320666840_1681692550_n
አንድነት መስከረም 19/2006 ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለተገኙ ሰዎች በደብዳቤ መልእክቱን በሰደደው አንዷለም የተበሳጩ የሚመስሉት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ‹‹አንዷለምን መጠየቅ የሚችሉት ቤተሰቦቹ ብቻ ናቸው በማለት ጠያቂዎችን ሲያጉላሉ ከቆዮ በኋላ ከትናንትና መስከረም 29/2006 ጀምሮ በይፋ ማንንም አናስገባም ማለት ጀምረዋል፡፡

ከማረሚያ ቤቱ ባገኘነው መረጃ መሰረት የእስር ቤቱ ሃላፊዎች አንዷለምን ወደ ቢሮ በመጥራት ‹‹እንዲጠይቁህ የምንፈቅደው ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው፣ስለዚህ በጣም ቅርቤ የምትላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር በመጻፍ ስጠን›› ይሉታል፡፡ሰላማዊው ታጋይ በበኩሉ በጠያቂዎች መጎብኘት ህገ መንግስታዊ መብቱ መሆኑን በመጥቀስ የማንንም ስም ጽፎ እንደማይሰጣቸው በመንገር ወደ ማረፊያው ተመልሷል፡፡
የአንዷለምን ምላሽ የሰሙ ሃላፊዎችም ማንኛውም (የአንዷለም) ጠያቂ ከበር እንዲመለስ የሚያደርግ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ታውቋል፡፡በጉዳዮ ዙሪያ የፓርቲውን አቋም ያንጸባረቁት የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራ ‹‹ድርጊቱ የመጀመሪያቸው አይደለም፣ የሆነ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር እንዲህ አይነት እርምጃዎችን ይወስዳሉ፣ሽብርተኛ በማለት ያሰሩት ሰው ምን ያህል ህገ መንግስታዊ መብቶቹን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑንም እግረ መንገዱን አሳይቷቸዋል፡፡የአንዷለም ቁርጠኝነትና መብቴን አላስነካም ማለቱ እንደሁልግዜው አርአያችን ሆኖ ይቀጥላል ››ብለዋል፡፡ የእስር ቤቱ አስተዳደር በበኩሉ እንዲህ አይነት ውሳኔ የተላለፈው ለእስረኞች ደህንነት ተብሎ ነው ብሏል፡፡አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም በእስር ቤቱ ውስጥ ደረቅ ወንጀል በመፈጸም በታሰረ እስረኛ መደብደቡ አይዘነጋም፡፡

ሰላም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር በኖርዌ በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ከተለያዩ ድርጅቶች ባለሞያዎችን በመጋበዝ የተዘጋጀ ሴሚናር ኦስሎ ኦክቶበር 05, 2013


የልጆች አስተዳደግን በሚመለከት በኖርዌ ዋና ከተማ  ኦስሎ  P hotell በተደረገው ሴሚናር ከሃገር ቤት በሚመጡ ልጆች የሚደርሰውን የባህል ልዩነት አስቸጋሪነቱንና በውጪ ሐገር በሚወለዶ ልጆች ያለውን  አስተዳደግ ዘርዘር ባለ መልኩ እንዲቀርብና  እንዲሁም የተለየዩ ጉዳዩችን አንስተው በመነጋገርና በህብረተሰቡ ዘንድ ጠቃሚነቱ እንዲጎለበት ለማድረግ ሰላም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር በኖርዌ  ሦስት ባለሞያዎችን በመጋበዝ የተዘጋጀ ሴሚናር። ምስሉን ይመልከቱ
  
                                                                     ክፍል አንድ
  
ክፍል ሁለት

Sunday, October 6, 2013

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍ ላይቀጥል ይችላል አሉ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያደርጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች ተደጋጋሚና መንግስት አቋም የያዘባቸውን ጉዳዮች የሚያነሱ እንደሆኑ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ መንግስት ለእያንዳንዱ ሰልፍ ጥበቃ ማድረግ ስለማይችል ሰልፎቹ በተለመደው መልኩ ላይቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የራሳቸው የፓርቲዎቹ ሳይሆኑ የሌሎች ሃይሎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ሰልፍ ማካሄድ ህገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትሩ፤ መንግስት በተደጋጋሚ ጥበቃ ሲያደርግ ቢቆይም፣ በሰልፎቹ የሚነሱት ጥያቄዎች ፋይዳ ቢስ ከመሆናቸውና ከፓርቲዎቹ ብዛት አንፃር መንግስት በቀጣይ ለሰልፎች ጥበቃ ለማድረግ የሚቸገርበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ መንግስት በተደጋጋሚ ምላሽ የሰጠባቸውን ጥያቄዎች መላልሰው የሚያቀርቡት በመንግስት ላይ ጫና በመፍጠር አቋሙን ለማስቀየር በማሰብ ሊሆን ይችላል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ይሄ ግን በፍፁም የማይሳካ ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡ “ግንቦት ሰባት” በቅርቡ መንግስትን ለመጣል ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ በይፋ መግለፁን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱም፣ የፓርቲው አመራሮችና ደጋፊዎች ተጨባጭ ያልሆነ ህልም ውስጥ ሆነው የተናገሩት ነገር እንደሆነና ከህልማቸው ሲነቁ እውነታውን እንደሚገነዘቡት ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ መከፋፈልና የሃይል መጠባበቅ አለ የሚለውን መረጃ በተመለከተም “ይህ የአንዳንድ አፍራሽ ሃይሎች ከንቱ ምኞትና ተጨባጭ ያልሆነ አሉባልታ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ 

Thursday, October 3, 2013

ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማፈንና አደባባይ በመከልከል መገደብ በህግም በታሪክም ያስጠይቃል!!! -



አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)              
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
UDJ (2)
በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በመላ ኢትዮጵያ በማካሄድ የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆኖ በብቃት ማከናወን ችሏል፡፡
የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል ሰኔ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ይፋ ስናደርግ በሰጠነው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳረጋገጥነው የዕቅዳችን ዋና አላማ ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነንነትን እያስፋፋ፤  ዴሞክራሲዊና ሰብዓዊ መብትን እየገፈፈ፣ ዜጎችን በፍርሃት ተዘፍቀው በምንደኛነት እንዲኖሩ ያደረገውን ስርዓት ላይ ሕዝቡ ጫና ፈጥሮ መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ስልጣን የህዝብ እንዲሆን፣ ግለሰቦች በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ በዕምነታቸውና ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው የማይታሰሩባት ሃገር በመፍጠርና ፍትሃዊነትን ማስፈን ነው ብለን ነበር፡፡
ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የሚሊዮኖችን ድምፅ በመሰብሰብ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጨውንና ገዥው ፓርቲ ተቀናቃኞችን ለማሸማቀቅ የሚጠቀምበትን የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ እንዲሰረዝ ማድረግ፤ ሚሊዮኖች የፀረ ሽብር አዋጁን በመቃወም የሚፈርሙበት ሰነድም በማዘጋጀት ድጋፍ ማሰባበሰብና በአጠቃላይም ህዝቡ ከሚሊዮኖች አንዱ የሚሆንበትንና የሀገሬ ጉዳይ የእኔ ጉዳይ ነው የሚል ትውልድ መፍጠር ነው፡፡ ይህንን ከግብ ለማድረስም በአመራር ደረጃ፣ አባላትና ደጋፊዎች ዋጋ ለመክፈል ካሳዩት ቁርጠኝነት በተጨማሪ የመታሰር፣ የንብረት ማጣትና የሞራል መጎዳት ዋጋ የተከፈለበት ነው፡፡
አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዥ ሀይል ዴሞክራሲያዊ ባለመሆኑና ዴሚክራሲያዊ ባህሪ ስለሌለው በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄዎቹ አስተጋቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ቢሆን ህዝባችን ጋር ለመድረስና ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሰማት ችለናል፡፡ ትግላችንንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት ዋጋ የከፈለለት የነፃነቱ ባለቤት እስከሚሆንና የህግ የበላይነት እስከሚረጋገጥ ከዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን የሚቀጥል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን
በሦስት ወር ህዝባዊ ንቅናቄያችን በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባምንጭ፣ በጅንካ፣ በአዳማ፣ በፍቼ አባሎቻችን ታስረውና ተደብድበውም ቢሆን በተሳካ ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን በመቀሌና ባሌ ሮቤ በከፍተኛ ጫናና ህገ-ወጥነት ሳይካሄዱ ቀርተዋል፡፡ በወላይታ ሶዶና አዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከናውነዋል፡፡ በአፋናና በጫና ያላካሄድንባቸው ቦታዎች ላይ ሕዝቡን የሚያስተዳድሩትን የስርዓቱ ሰዎችና ስርዓቱን ያጋለጥንበት፣ ሕዝቡም በቁጭት ከጎናችን እንዲቆም ያደረግንበትና ለቀጣይ የተደራጀ ትግል እንድንዘጋጅ ያነሳሳ ሁነት ነበር፡፡
አዲስ አበባን ጨምሮ ከላይ በጠቀስናቸው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ደብድበዋል፣ አዋክበዋል፣ ሜጋ ፎኖች ተነጥቀዋል፡፡ በአዲስ አበባም  ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የቅስቀሳ መኪኖቻችንን እስከነ ሞንታርቦና ጀነሬተሮች ጠኋት አስሮ ማታ በመፍታት የተሳካ ቅስቀሳ እንዳናደርግ ተደርጓል፡፡ በራሪ ወረቀቶችን እንዳናሰራጭና ፖስተሮችን እንዳንለጥፍ በፖሊስ ተከልክለናል፣ ታስረናል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ደግሞ  የተለጠፉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ 99.6 ፐርሰንት እንዳሸነፈ ቢነግረንም በተግባር ያረጋገጥነው ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅ እንደሆነ ነው፡፡
የመጀመሪው ዙር የሶስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄችን ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባው ጽ/ቤት መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሠላማዊ ሠልፉን በመስከረም 19 ቀን ማድረግ እንደምንችል  የሚገልፅ የዕውቅና ደብባቤ ቢሰጠንም   በእጅ አዙር ሠልፉን በመስቀል አደባባይ እንዳናደርግ ከመከልከሉም በላይ ከሕግ ውጨ በመከላከያ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ እንድንሰለፍ ለማስገደድ በመሞከርና  ቅስቀሳ እንዳናደርግ በመከልከል ነው፡፡ ፖሊስም ህገ መንግስቱንና ህዝቡን መጠበቅ ሲገባው ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀቶችን ለማሰራጨት ፈቃድ ያስፈልጋል ትዕዘዝ አልደረሰንም በሚል ተልካሻ ምክንያት ህገ-መንግስታዊ መብታችንን በመጣስ የፓርቲያችንን ሊቀመንበር ጨምሮ በአጠቃላይ 101 (አንድ መቶ አንድ) አባላትን ከማክሰኞ እስከ እሁድ አስሮብናል፡፡ ፖሊስ ለህግ የበላይነት መቆም ሲገባው በድብቅ ለተሰጠው ትዕዛዝ ተገዥ በመሆኑ ከማዘናችንም በተጨማሪ ወደ ህግ በመሄድ የደረሰብንን ህገ-ወጥ የእስር መንገላታት፣ ካላግባብ ስለደረሰብን የንብረትና የገንዘብ ጉዳት እንዲሁም የሞራል ካሳ የአዲስ አበባ ፖሊስን፣ የአዲስ አበባ መስተዳድርን   በሕግ የምንጠይቅ  መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!
የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች
መስከረም 23 ቀን 2006
አዲስ አበባ

Wednesday, October 2, 2013

እምቢ በል


ለስምንት አመታት በሐገራችን ምንም አይነት ተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ በገዢው መንግስት ተከልክሎ የነበረ ቢሆንም እገዳውን ሰብረው ህገ መንግስቱ በሚፈቅድላቸው መብት መሰረት  ተጠቅመው ብሶታችንን ላሰሙልን ለጀግኖች ወገኖቻችን ይሆን ዘንድ  ይህንን ምስል ማስታወሻ   አዘጋጅቼዋለሁ።
እምቢ እምቢ እምቢ በል
እስክንድር

መስከረም 19 ቀን 206 ዓ.ም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በጠራው ሕዝባዊ ሠላማዊ ሠልፍ በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የተደረገ ንግግር

የተከበራችሁ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች፤
የተከበራችሁ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤
የተከበራችሁ የሚዲያ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች፤
ክቡራንና ክቡራት!

አስቀድሜ የማክበር ሰላምታየን እያቀረብኩ መብታችንን አደባባይ ወጥተን ለምንጠይቅበት፣ ያልተሸራረፈ ነፃነታችንን ለማረጋገጥ ጉዞ ወደቀጠልንበት ታሪካዊ ቀን ሁላችንንም እንኳን አደረሰን፡፡ 

በመቀጠልም ለዚህ ዝግጅት መሳካት የተባበሩንን፣ የረዱንን፣ ያገዙንንና በቅስቀሳ ወቅት መስዋዕት ከፍለው ለዚህ ላደረሱን የአንድነትና የ33ቱ አባላት፣ አመራሮችና ደጋፊዎቻችን ከፍ ያለ ምስጋናየን ከአክብሮት ጋር ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማከናወኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ ነገር ግን ሕጋዊ መብቱን ሳያስነካ፤ መከፈል የሚገባውን መስዋዕትነት በመክፈልና በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት ከአባላቱና አመራሩ ጋር በመሆን በማከናወን ለኢትዮጵያ ሕዝብ መመኪያ መሆኑን አስመስክሯል፡፡

ዛሬ የተሰለፍንበት ዋና ምክንያትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የተሰለፈለትን፣ የሞተለትን፣ በአጠቃላም አንድ ትውልድ ትልቅ ዋጋ የከፈለለትን ግን ደግሞ እስካሁን መረጋገጥ ያልቻሉትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለምንም መሸራረፍ የሰፈነባት የሁላችን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሲደረግ የቆየውን ትግል በማያዳግም መልኩ ከህዝቡ ጋር በመሆን እውን ለማድረግ ነው፡፡ 

የምንታገለው ለመብታችን መከበር፣ ለነፃነታችን መረጋገጥ፣ ለሀገር ሉዓላዊነታችን፣ ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ የታሰሩ የፖለቲካና ህሊና እስረኞች እንዲፈቱና ማንም ሰው በፖለቲካ አመለካከቱ፣ በእምነቱና ሃሳቡን በነፃነት ስለገለፀ የማይታሰርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው፡፡ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ህጉ መሰረታዊ ዜጎችን መብቶችና ሕገ-መንግስቱን በግልፅ የሚንድ በመሆኑ የሚሊዮኖችን የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ እንዲሰረዝ ለማድረግ ነው፡፡

ዛሬ የተሰለፍነው ኢህአዴግና የኢህአዴግ መንግስት እንደሚከሰን ሁከት ለመፍጠር አይደለም፣ ሽብር ለመፍጠር አይለም፣ አሸባሪዎች ስለሆንን አይደለም፣ የአሸባሪዎች መደበቂያ ስለሆንንም አይደለም፣ የሻዕቢያ መልዕክት አድራሾች ስለሆንን አይደለም፣ በአቋራጭ የመንግስት ስልጣን ለመያዝም አይደለም፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በገዥው ፓርቲ የተነጠቅናቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስመለስ ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በአመለካከታችን የማንታሰርባት ኢትዮጵያ ስለምታስፈልገን ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በጉልበትና አፈና መግዛት እንዲበቃና እንደሌሎች ሀገሮች ሀገራችን ዴሞክራሲ የሰፈነባት እንድትሆን ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት!
ፓርቲያችን አንድነት ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የሚገባትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ በሰላማዊ የትግል መስመር ለማረጋገጥ ትግል ከጀመረ አምስት ዓመቱን ይዟል፡፡ በነዚህ ዓመታትም ፓርቲያችን ወደ ፍፁም አምባገንነት እየሄደ ያለውን ገዥ ፓርቲ የፖለቲካ አካሄድ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ነጠቃ እንዲቆም አጥብቆ ታግሏል፣ እየታገለም ይገኛል፡፡

በትግሉ ሂደትም ስርዓቱ በግልፅና በስውር ፓርቲያችን ላይ ጥቃት ፈፅሟል፤ እየተፈፀመም ይገኛል፡፡ አመራሮቻችንና አባሎቻችንም ስለ ቁርጠኛ ዓላማቸው ያለምንም ማፈግፈግ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲና ነፃነት ሲሉ ጨለማ ክፍል የተጣሉትን ወጣት የፖለቲካ አመራሮች፣ ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እስር ቤት የተጣሉ ጋዜጠኞችና የዕምነት ጣልቃ ገብነትን የተቃወሙ የሙስሊም ወገኖች መፍትሄ አፈላላጊ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቀለን፡፡ ዜጎችን ለማሰር እያገለገለ ያለው የጸረ-ሽብር አዋጅም በአስኳይ እንዲሰረዝና በሀገራዊ ጉዳይ ላይ እየሰሩ ያሉ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የፖለቲካ ሃይሎችን ያሳተፈ ሀገር አቀፍ ውይይት እንዲጀመርና በሀገራችን ጉዳይ ላይ መፍትሄ እየሰጠን እንድንሄድ፤ ለዚህም ገዥው ፓርቲ ፈቃደኛም፤ ቁርጠኛም እንዲሆን ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 

የሀገራችን ፖለቲካ በኢህአዴግ ብቻ አይፈታም፡፡ በሌላ አንድ ፓርቲ ብቻም ይፈታል ብለንም አናምንም፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በመተባበር፣ በመቀናጀትና ውህደት በመፍጠር ትልቅ የፖለቲካ አቅም መፍጠር ተገቢ ነው፡፡

የተከበራችሁ ሰላማዊ ሰልፈኞች!

አሁንም ገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ለውጥና ማሻሻያ ለማድረግ ፍላጎትም አቅምም የለውም፡፡ በ3 ወር ህዝባዊ ንቅናቄችን ያረጋገጥነው ይሄንኑ ነው፡፡ ምክንቱም አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዥ ሀይል በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ አሁንም ለጥያቄ አቅራቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ቢሆን ህዝባችን ጋር ለመድረስና ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሰማት ችለናል፡፡ ይሄው በማሰማት ላይም እንገኛለን፡፡ ሰላማዊ የተቃውሞ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል አምባገነኖችን በሚያንቀጠቅጥ የተቃውሞ ትግል እንደምናሸንፍ አልጠራጠርም፡፡

በጎንደርና ደሴ ከተማ በ7/11/2005 የጀመርነው የተቀውሞ ሰልፎች በባህርዳር፣ በአርባምንጭ፣ በጅንካ፣ በአዳማ፣ በፍቼ በተሳካ ሁኔታ የተካሄዱ ሲሆን በመቀሌና ባሌ ሮቤ በከፍተኛ ጫናና ህገወትነት ሳካሄዱ ቀርተዋል፡፡ በወላታ ሶዶና አዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከናውነዋል፡፡ ከላይ በጠቀስናቸው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ደብድበዋል፣ አዋክበዋል፡፡ ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የተለጠፉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅና በጉልበት ብቻ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን!

ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ተቋምና የፍትህ ስርዓት ያስፈልገናል፡፡ ነፃና ገለልተኛ የሆነ የፖሊስና የደህንነት ተቋምም ያስፈልገናል፡፡ ነፃና ገለልተና የዴሞክራሲ ተቋማትም መፈጠር አለባቸው፡፡ እነዚህና ሌሎች ተቋማት የሚፈጠሩት ግን በልመና አይደለም፡፡ እነዚህን ተቋማት ነጻ ሆነመው እንዲፈጠሩ የምታደርጉት እናንተ ናችሁ፡፡ ነፃነት ከፍርሀት አይገኝምና፣ በሀገር ጉዳይ አይፈራምና ነፃነታችንንና መብታችንን የሚነጥቁንን እምቢ ማለት አለብን፡፡ አትችሉም ማለት አለብን፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሕዝብ ገዥዎችን የምንፈራብ ዘመን ማብቃት አለበት፡፡ ገዥ ህዝቡን ይፈራል እንጅ ሕዝብ ገዥዎችን አይፈራም፡፡

ከላይ የተናገርኩትን የሚያጠናክር መረጃ ላቅርብ፡፡ ዜጎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይያዛሉ፣ አስገድው በአካል ፈሳሽና ናሙና በመውሰድ ምርመራዎች ይካሄዳሉ፣ በተጠርጣሪዎች ላይ በውሸት ማስመስከርና አስገድዶ መረጃ ማውጣጣት፣ ቶርቸር፣ ዜጎች በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ ማስገደድና ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎች አገዛዙ ፍርሃት እንዲፈጠር ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም ስርዓቱ ዜጎች ካላግባብ ከየመኖሪያ ቀያቸው በገጠርም ሆነ በከተማ በግፍ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄው ሀገራዊ ይዘት ያለው ማፈናቀል ሦስት አይነት መልክ ያለው ሲሆን በዘር ላይ ተመሰረተ ማፈናቀል፣ በልማት ስም ማፈናቀልና ለመሬት ወረራ ማፈናቀል ናቸው፡፡ ዘርን መሰረት ያደረገው ማፈናቀል በቅርቡ ብቻ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፣ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ክልሎችና ሌሎችም አካባቢዎች የተከሰተው ነው፡፡ በልማት ስም የሚከናወነው ማፈናቀል በአብዛኛው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ዋናው መሰረቱ የገዥው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ ነው፡፡ መሬት በባለቤቱ ፈቃድ የሚሸጥና የሚለወጥ ባለመሆኑ ያለበቂ ካሳና ማስጠንቀቂያ ለማህበራዊ ትስስር ቁብ ሳይኖረው ልማት የሚል ስም ብቻ በማንሳት ዜጎች የሚፈናቀሉበት ነው፡፡ ሌላው የማፈናቀል አይነት ደግሞ ከመሬት ወረራ ጋር በእጅጉ የተቆራኘና በእርሻ መሬት ሰበብ ዜጎች እየተፈናቀሉ ለውጭና ሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በጥቂት ሳንቲም የሚሰጥ ነው፡፡ ይሄም በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በስፋት የታየና እየታየ ያለ ነው፡፡ ሀገራቀፉን ማፈናቀል አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ በአስቸኳይ እንዲቆምም እንጠቃለን፡፡

ከመፈናቀሉ በተጨማሪም ቅጥ ያጣ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት በሰፊው ተንሰራፍቷል፡፡ የኑሮ ውድነቱን ጣሪያ ያስነካው የዋጋ ግሽበት ዋና መንስኤው ስርዓቱ የሚከተለው የተሳሳተ አጠቃላይ ፖሊሲ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ የወለደው ነገር ቢኖር ሀገራችን በታሪኳ አይታ የማታውቀው ስደት ነው፡፡ ዜጎች ከፊት ለፊት ሞት እንደሚጠብቃቸው እያወቁ ተጋፍጠው ለስደት የመነሳታቸው መንስኤ ስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ነው፡፡ ከዚህ ጋር የነፃነት እጦት ሲታከልበት የችግሩን መልክ ውስብስብ አድርጎታል፡፡ 

የንግዱን ማህበረሰብም ስንመለከት ከመቼውም በባሰ ሁኔታ ነጋዴ መሆን ወንጀለኛ መሆን የሚል ትርጉም ይዟል፡፡ በተጨማሪም አንድ ፓርቲ ነጋዴና አንድ ፓርቲ ህግ አውጭ በሆነበት ሁኔታ ፍትሀዊ የንግድ ውድድር የሚታሰብ አይደለም፡፡ ስለዚህ የግሉ ሴክተር የልማት ሚና አይኖረውም ማለት ነው፡፡ ካላግባብና በግምት የሚጣል ታክስ መክፈል ሃገራዊ ግዴታ የመሆኑን ለዛ አሳጥተውታል፡፡ አንዳንዱ በብልጣብልጥነት ስርዓቱን እንደመታወቂያና ከለላ በመጠቀም፣ ከባለስልጣናት ጋር በመሻረክ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሀብት ማማ ላይ ሲወጣ እንመለከታለን፡፡ ይሄም በንፁህ ንግድ ላይ ያልተመሰረቱ ለበርካታ ዜጎች አደጋ ነው፡፡ ከዚያም ልቆ ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ስለዚህ ፍትሃዊ የንግድ አሰራር እንዲኖር እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ማስገንዘብ የምወደው በሀገራችን የስልጣን ሽግግር ታሪክ እንዱ እንዱን በአፈሙዝ እየገደለ፣ መንድም ወንደሙን ጠላት እያደረገ ነው፡፡ ይህም የርስ በርስ የጦርነት ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ትውልድ ብቻ ሁለት አብዮቶች ተካሂደዋል፡፡ በአገራችንንና በትውልዱ ላይም በገንዘብ የማይተመን ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ ዛሬም በተለይም ወጣቱ ትውልድና ዋጋ የከፈሉ አባቶች ፍፁም ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ምኞታችን ከፍተኛ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ እየዘጋው ያለው ዴሞክራሲያዊ መንገድና ዜጎች እየደረሰባቸው ካለው ስቃይ አንፃር ወደ ሕዝባዊ አመፅ ተቀይሮ ወደ ሶስተኛው አብዮት ቢገፋ ተጠያቂው መንግስት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ለወጣቶች የማስተላልፈው መልዕክትም ምንም እንኳ የወረሳችሁድ ዕዳ ብዙ ቢሆንም በቁርጠኝነት ታግላችሁ ሀገራችንን እንደሰለጠኑት ሀገሮች እንደምታደርጉ ተስፋ አለኝ፡፡ ከ50 ዓመት በላይ ዋጋ የተከፈለበት ዴሞክራሲ እውን እንድታደርጉ አደራ እያልኩ እንደምታሳኩትም ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

መስከረም 19 ቀን 206 ዓ.ም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በጠራው ሕዝባዊ ሠላማዊ ሠልፍ በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የተደረገ ንግግር

የተከበራችሁ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች፤
የተከበራችሁ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤
የተከበራችሁ የሚዲያ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች፤
ክቡራንና ክቡራት!

አስቀድሜ የማክበር ሰላምታየን እያቀረብኩ መብታችንን አደባባይ ወጥተን ለምንጠይቅበት፣ ያልተሸራረፈ ነፃነታችንን ለማረጋገጥ ጉዞ ወደቀጠልንበት ታሪካዊ ቀን ሁላችንንም እንኳን አደረሰን፡፡ 

በመቀጠልም ለዚህ ዝግጅት መሳካት የተባበሩንን፣ የረዱንን፣ ያገዙንንና በቅስቀሳ ወቅት መስዋዕት ከፍለው ለዚህ ላደረሱን የአንድነትና የ33ቱ አባላት፣ አመራሮችና ደጋፊዎቻችን ከፍ ያለ ምስጋናየን ከአክብሮት ጋር ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማከናወኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ ነገር ግን ሕጋዊ መብቱን ሳያስነካ፤ መከፈል የሚገባውን መስዋዕትነት በመክፈልና በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት ከአባላቱና አመራሩ ጋር በመሆን በማከናወን ለኢትዮጵያ ሕዝብ መመኪያ መሆኑን አስመስክሯል፡፡

ዛሬ የተሰለፍንበት ዋና ምክንያትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የተሰለፈለትን፣ የሞተለትን፣ በአጠቃላም አንድ ትውልድ ትልቅ ዋጋ የከፈለለትን ግን ደግሞ እስካሁን መረጋገጥ ያልቻሉትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለምንም መሸራረፍ የሰፈነባት የሁላችን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሲደረግ የቆየውን ትግል በማያዳግም መልኩ ከህዝቡ ጋር በመሆን እውን ለማድረግ ነው፡፡ 

የምንታገለው ለመብታችን መከበር፣ ለነፃነታችን መረጋገጥ፣ ለሀገር ሉዓላዊነታችን፣ ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ የታሰሩ የፖለቲካና ህሊና እስረኞች እንዲፈቱና ማንም ሰው በፖለቲካ አመለካከቱ፣ በእምነቱና ሃሳቡን በነፃነት ስለገለፀ የማይታሰርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው፡፡ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ህጉ መሰረታዊ ዜጎችን መብቶችና ሕገ-መንግስቱን በግልፅ የሚንድ በመሆኑ የሚሊዮኖችን የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ እንዲሰረዝ ለማድረግ ነው፡፡

ዛሬ የተሰለፍነው ኢህአዴግና የኢህአዴግ መንግስት እንደሚከሰን ሁከት ለመፍጠር አይደለም፣ ሽብር ለመፍጠር አይለም፣ አሸባሪዎች ስለሆንን አይደለም፣ የአሸባሪዎች መደበቂያ ስለሆንንም አይደለም፣ የሻዕቢያ መልዕክት አድራሾች ስለሆንን አይደለም፣ በአቋራጭ የመንግስት ስልጣን ለመያዝም አይደለም፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በገዥው ፓርቲ የተነጠቅናቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስመለስ ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በአመለካከታችን የማንታሰርባት ኢትዮጵያ ስለምታስፈልገን ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በጉልበትና አፈና መግዛት እንዲበቃና እንደሌሎች ሀገሮች ሀገራችን ዴሞክራሲ የሰፈነባት እንድትሆን ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት!
ፓርቲያችን አንድነት ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የሚገባትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ በሰላማዊ የትግል መስመር ለማረጋገጥ ትግል ከጀመረ አምስት ዓመቱን ይዟል፡፡ በነዚህ ዓመታትም ፓርቲያችን ወደ ፍፁም አምባገንነት እየሄደ ያለውን ገዥ ፓርቲ የፖለቲካ አካሄድ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ነጠቃ እንዲቆም አጥብቆ ታግሏል፣ እየታገለም ይገኛል፡፡

በትግሉ ሂደትም ስርዓቱ በግልፅና በስውር ፓርቲያችን ላይ ጥቃት ፈፅሟል፤ እየተፈፀመም ይገኛል፡፡ አመራሮቻችንና አባሎቻችንም ስለ ቁርጠኛ ዓላማቸው ያለምንም ማፈግፈግ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲና ነፃነት ሲሉ ጨለማ ክፍል የተጣሉትን ወጣት የፖለቲካ አመራሮች፣ ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እስር ቤት የተጣሉ ጋዜጠኞችና የዕምነት ጣልቃ ገብነትን የተቃወሙ የሙስሊም ወገኖች መፍትሄ አፈላላጊ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቀለን፡፡ ዜጎችን ለማሰር እያገለገለ ያለው የጸረ-ሽብር አዋጅም በአስኳይ እንዲሰረዝና በሀገራዊ ጉዳይ ላይ እየሰሩ ያሉ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የፖለቲካ ሃይሎችን ያሳተፈ ሀገር አቀፍ ውይይት እንዲጀመርና በሀገራችን ጉዳይ ላይ መፍትሄ እየሰጠን እንድንሄድ፤ ለዚህም ገዥው ፓርቲ ፈቃደኛም፤ ቁርጠኛም እንዲሆን ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 

የሀገራችን ፖለቲካ በኢህአዴግ ብቻ አይፈታም፡፡ በሌላ አንድ ፓርቲ ብቻም ይፈታል ብለንም አናምንም፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በመተባበር፣ በመቀናጀትና ውህደት በመፍጠር ትልቅ የፖለቲካ አቅም መፍጠር ተገቢ ነው፡፡

የተከበራችሁ ሰላማዊ ሰልፈኞች!

አሁንም ገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ለውጥና ማሻሻያ ለማድረግ ፍላጎትም አቅምም የለውም፡፡ በ3 ወር ህዝባዊ ንቅናቄችን ያረጋገጥነው ይሄንኑ ነው፡፡ ምክንቱም አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዥ ሀይል በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ አሁንም ለጥያቄ አቅራቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ቢሆን ህዝባችን ጋር ለመድረስና ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሰማት ችለናል፡፡ ይሄው በማሰማት ላይም እንገኛለን፡፡ ሰላማዊ የተቃውሞ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል አምባገነኖችን በሚያንቀጠቅጥ የተቃውሞ ትግል እንደምናሸንፍ አልጠራጠርም፡፡

በጎንደርና ደሴ ከተማ በ7/11/2005 የጀመርነው የተቀውሞ ሰልፎች በባህርዳር፣ በአርባምንጭ፣ በጅንካ፣ በአዳማ፣ በፍቼ በተሳካ ሁኔታ የተካሄዱ ሲሆን በመቀሌና ባሌ ሮቤ በከፍተኛ ጫናና ህገወትነት ሳካሄዱ ቀርተዋል፡፡ በወላታ ሶዶና አዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከናውነዋል፡፡ ከላይ በጠቀስናቸው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ደብድበዋል፣ አዋክበዋል፡፡ ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የተለጠፉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅና በጉልበት ብቻ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን!

ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ተቋምና የፍትህ ስርዓት ያስፈልገናል፡፡ ነፃና ገለልተኛ የሆነ የፖሊስና የደህንነት ተቋምም ያስፈልገናል፡፡ ነፃና ገለልተና የዴሞክራሲ ተቋማትም መፈጠር አለባቸው፡፡ እነዚህና ሌሎች ተቋማት የሚፈጠሩት ግን በልመና አይደለም፡፡ እነዚህን ተቋማት ነጻ ሆነመው እንዲፈጠሩ የምታደርጉት እናንተ ናችሁ፡፡ ነፃነት ከፍርሀት አይገኝምና፣ በሀገር ጉዳይ አይፈራምና ነፃነታችንንና መብታችንን የሚነጥቁንን እምቢ ማለት አለብን፡፡ አትችሉም ማለት አለብን፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሕዝብ ገዥዎችን የምንፈራብ ዘመን ማብቃት አለበት፡፡ ገዥ ህዝቡን ይፈራል እንጅ ሕዝብ ገዥዎችን አይፈራም፡፡

ከላይ የተናገርኩትን የሚያጠናክር መረጃ ላቅርብ፡፡ ዜጎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይያዛሉ፣ አስገድው በአካል ፈሳሽና ናሙና በመውሰድ ምርመራዎች ይካሄዳሉ፣ በተጠርጣሪዎች ላይ በውሸት ማስመስከርና አስገድዶ መረጃ ማውጣጣት፣ ቶርቸር፣ ዜጎች በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ ማስገደድና ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎች አገዛዙ ፍርሃት እንዲፈጠር ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም ስርዓቱ ዜጎች ካላግባብ ከየመኖሪያ ቀያቸው በገጠርም ሆነ በከተማ በግፍ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄው ሀገራዊ ይዘት ያለው ማፈናቀል ሦስት አይነት መልክ ያለው ሲሆን በዘር ላይ ተመሰረተ ማፈናቀል፣ በልማት ስም ማፈናቀልና ለመሬት ወረራ ማፈናቀል ናቸው፡፡ ዘርን መሰረት ያደረገው ማፈናቀል በቅርቡ ብቻ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፣ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ክልሎችና ሌሎችም አካባቢዎች የተከሰተው ነው፡፡ በልማት ስም የሚከናወነው ማፈናቀል በአብዛኛው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ዋናው መሰረቱ የገዥው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ ነው፡፡ መሬት በባለቤቱ ፈቃድ የሚሸጥና የሚለወጥ ባለመሆኑ ያለበቂ ካሳና ማስጠንቀቂያ ለማህበራዊ ትስስር ቁብ ሳይኖረው ልማት የሚል ስም ብቻ በማንሳት ዜጎች የሚፈናቀሉበት ነው፡፡ ሌላው የማፈናቀል አይነት ደግሞ ከመሬት ወረራ ጋር በእጅጉ የተቆራኘና በእርሻ መሬት ሰበብ ዜጎች እየተፈናቀሉ ለውጭና ሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በጥቂት ሳንቲም የሚሰጥ ነው፡፡ ይሄም በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በስፋት የታየና እየታየ ያለ ነው፡፡ ሀገራቀፉን ማፈናቀል አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ በአስቸኳይ እንዲቆምም እንጠቃለን፡፡

ከመፈናቀሉ በተጨማሪም ቅጥ ያጣ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት በሰፊው ተንሰራፍቷል፡፡ የኑሮ ውድነቱን ጣሪያ ያስነካው የዋጋ ግሽበት ዋና መንስኤው ስርዓቱ የሚከተለው የተሳሳተ አጠቃላይ ፖሊሲ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ የወለደው ነገር ቢኖር ሀገራችን በታሪኳ አይታ የማታውቀው ስደት ነው፡፡ ዜጎች ከፊት ለፊት ሞት እንደሚጠብቃቸው እያወቁ ተጋፍጠው ለስደት የመነሳታቸው መንስኤ ስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ነው፡፡ ከዚህ ጋር የነፃነት እጦት ሲታከልበት የችግሩን መልክ ውስብስብ አድርጎታል፡፡ 

የንግዱን ማህበረሰብም ስንመለከት ከመቼውም በባሰ ሁኔታ ነጋዴ መሆን ወንጀለኛ መሆን የሚል ትርጉም ይዟል፡፡ በተጨማሪም አንድ ፓርቲ ነጋዴና አንድ ፓርቲ ህግ አውጭ በሆነበት ሁኔታ ፍትሀዊ የንግድ ውድድር የሚታሰብ አይደለም፡፡ ስለዚህ የግሉ ሴክተር የልማት ሚና አይኖረውም ማለት ነው፡፡ ካላግባብና በግምት የሚጣል ታክስ መክፈል ሃገራዊ ግዴታ የመሆኑን ለዛ አሳጥተውታል፡፡ አንዳንዱ በብልጣብልጥነት ስርዓቱን እንደመታወቂያና ከለላ በመጠቀም፣ ከባለስልጣናት ጋር በመሻረክ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሀብት ማማ ላይ ሲወጣ እንመለከታለን፡፡ ይሄም በንፁህ ንግድ ላይ ያልተመሰረቱ ለበርካታ ዜጎች አደጋ ነው፡፡ ከዚያም ልቆ ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ስለዚህ ፍትሃዊ የንግድ አሰራር እንዲኖር እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ማስገንዘብ የምወደው በሀገራችን የስልጣን ሽግግር ታሪክ እንዱ እንዱን በአፈሙዝ እየገደለ፣ መንድም ወንደሙን ጠላት እያደረገ ነው፡፡ ይህም የርስ በርስ የጦርነት ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ትውልድ ብቻ ሁለት አብዮቶች ተካሂደዋል፡፡ በአገራችንንና በትውልዱ ላይም በገንዘብ የማይተመን ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ ዛሬም በተለይም ወጣቱ ትውልድና ዋጋ የከፈሉ አባቶች ፍፁም ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ምኞታችን ከፍተኛ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ እየዘጋው ያለው ዴሞክራሲያዊ መንገድና ዜጎች እየደረሰባቸው ካለው ስቃይ አንፃር ወደ ሕዝባዊ አመፅ ተቀይሮ ወደ ሶስተኛው አብዮት ቢገፋ ተጠያቂው መንግስት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ለወጣቶች የማስተላልፈው መልዕክትም ምንም እንኳ የወረሳችሁድ ዕዳ ብዙ ቢሆንም በቁርጠኝነት ታግላችሁ ሀገራችንን እንደሰለጠኑት ሀገሮች እንደምታደርጉ ተስፋ አለኝ፡፡ ከ50 ዓመት በላይ ዋጋ የተከፈለበት ዴሞክራሲ እውን እንድታደርጉ አደራ እያልኩ እንደምታሳኩትም ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!