Friday, January 31, 2014

የአማራው ክልል መሪ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቁ

ር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል።
ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ፕሬዚዳንቱ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት ብለዋል።
አማራው “በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው” ያሉት ምክትል አስተዳዳሪውና የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊው፣ ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው  የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት ያሉት አቶ አለምነው፣ ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም ሲሉ ድምድመዋል።
ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ምክንያቱንም ሲገልጹ ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው ብለዋል። ያንን ምግብ እየተመገበ እንደሚያቅራራም ገልጸዋል።
አንዳንድ የብአዴን አባላት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ንግግር እጅግ እንዳበሳጫቸው ለኢሳት ተናግረዋል።
የብአዴን ካድሬዎች አንቀጽ 39 ለምን አይወጣም በማለት ላነሱት ጥያቄ፣ እኝሁ ፕሬዚዳንት ሲመልሱ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ  ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር በማለት መልሰዋል ። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ መታየቱን ም/ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል
የድምጽ ማስረጃውን ቀርጸው ለላኩለን በስብሰባው ላይ የተካፈሉ የህክምና ባለሙያዎችን ለማመስገን እንወዳለን።

Thursday, January 30, 2014

ኢህአዴግ ልማቱን ለመጨረስ ከ40 እስከ 45 አመት ያስፈልገዋል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

በረከት ሲሞን
ር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት ለኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ነው። ለማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ዝግ በሆነው የካድሬዎች ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ወረቀታቸውን ያቀረቡት አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ የህዝቡን የነፍሰ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ  ቢያንስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

አቶ በረከት የወደፊቱ የህዳሴ መንገድ በሚል ባቀረቡት ጽሁፍ ፣ ግንባሩ የኢትዮጵያ ህዳሴ በስንት ዓመታት ሊጠቃለል ይችላል የሚለውን ከእነኮሪያና ታይዋን ልምድ በመውሰድ መስራቱን ተናግረዋል። አገሮች ከዝቅተኛ ወደ መካከለኛ ከዚያም ወደ ከፍተኛ ገቢ ለመድረስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት መውሰዳቸውን ገልጸዋል ።
አቶ በረከት መካከለኛ ገቢ የሚባለው ከገቢ አንጻር ሲሰላ ዝቀተኛው 1000 ዶላር ከፍተኛው ደግሞ 5 ሺ ዶላር መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለፈው 10 አመታት የጀመርነውን እድገት ከቀጠልን በሚቀጥሉት 10 አመታት የመካከለኛው ገቢ ዝቀተኛ ጣራ ከሆነው 1000 ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ደረጃ ላይ እንደርሳለን የሚሉት አቶ በረከት፣ የመካከለኛ ገቢ ከፍተኛ ጣራ ከሆነው 5 ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ለመድረስ እንደገና ተጨማሪ 15 ወይም 20 አመታት ይወስድብናል ብለዋል;፡
የከፍተኛው ገቢ የመጨረሻው ደረጃ ለሆነው የ10 ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ደረጃ ለመድረስ ሌላ ከ15-20  ተጨማሪ አመታት እንደሚያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል። ይህንን ጊዜ ለማሳጠር ብንፈልግ ልናሳጥረው አንችልም የሚሉት አቶ በረከት ፣ እድገቱ አንዳንዴም ልክ ቱኒዚያ፣ ታይላንዳና ማሌዢያ እንደተቋረጠባቸው ሊቋረጥ ይችላል ብለዋል።
ይህን እደገት ለማስቀጠል ፈተናዎች አሉ ያሉት አቶ በረከት፣ አንደኛው ፈተና  እድገቱን ህብረተሰቡ ሳይሰለች ማስቀጠል ይችላል ወይ  የሚለው ነው ሰሉ ተናግረዋል።
“ነባሩ አመራር  በእድሜ፣ በጤናና በመድከም ከሃላፊነት የሚወጣ በመሆኑ አዲሱ ትውልድ በተመሳሳይ ትኩረትና ፍጥነት እድገቱን ይዞት ሊሄድ ይችላል ወይ?’ የሚለው ጥያቄ ያልተመለሰና መመለስ ያለበት ነው ሲሉ ኢህአዴግ ያጋጠመውን ፈተና ገልጸዋል። ኢሳት የድምጽ መልእክቶችን በመላክ የሚተባበሩንን ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች ለማመስገን ይወዳል።

Monday, January 27, 2014

Professor Mesfin Woldemariam Speaks out on recent controversy of Ethio-Sudan border demarcation......

Professor Mesfin Woldemariam Speaks out on recent controversy of Ethio-Sudan border demarcation Issue and its historical context. The event was organized by Semayawi Party 


Saturday, January 25, 2014

Oslo; Ethiopian Muslims and Christians protest against the government (video)


               
Oslo Demonstration Jan 24,2014
በዛሬ እለት Jan 24 ,2014 በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ የሚገኙና ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችንና ያለፍትህ የታሰሩት ጋዜጠኞች፤ ፖለቲከኞች በእስር ላይ የሚደርስባቸውን እንግልትና ስቃይ በመቃወም ከእስር እንዲፈቱ እንዲሁም የእምነት ነፃነት በሐገራችን ላይ እንዲከበር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። ቪድዮውን ይመልከቱ  



                                                                                                              እስክንድር አሰፋ /ኖርዌይ

Tuesday, January 21, 2014

የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ


ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር።

ጥያቄውን ያነሱት በፌደራል ስር የሚገኙ የደህንነት ስራተኞች እና ቀደም ብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን በትግራይ ውስጥ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሽፋን የተቋቋመው ኤም አይ ቲ እየተባለ በሚጠራው ከመቀሌ ከተማ 9 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በተገነባው ተቋም ውስጥ ተመርቀው የወጡት የደህንነት ሰራተኞች ናቸው።

የደህንነት ሰራተኞቹ “የእኛ ሃለፊነት የአገር ደህንነትን ማስጠበቅ ነው የፖለቲካ ስርአቱን ?” በሚል ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ” የፖለቲካ ስራ የማይሰራ ደህንነት የለም፣ የደህንነት ስራ ሲጀመር ስርአት የማቆየት ስራ ነው፤ ስርአቱን የምናቆይበት ደግሞ ፕሮፌሽናል ነው፣ በስርአቱ ላይ እምነት ማሳደር የሚጠይቅ ተግባር ነው፣ የግንቦት7ትን አስተሳሰብ የሚያቀነቅንና ስርአቱ በጉልበት መፍረስ አለበት ብሎ የሚያስብ ሰው፣ የተስፋየ ወልደ ስላሴ አይነት የደህንነት ብቃት አለው ቢባል፣ ሞሳድ 20 አመታት አሰልጥኖታል ቢባል ስርአቱን ከማፍረስ ውጭ ደህንነቱን ሊያስጠብቅ አይችልም” ፣ ስለዚህ የደህንነት ስራ ለሚሰሩ ወገኖች የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ወሳኝ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል ።

“የደህንነት ተቋሙ ፣ ሰራዊቱና ሚዲያው በተቃዋሚዎች ዘንድ መቼውንም ቢሆን ገለልተኛ ተደርጎ አይቆጠርም” ያሉት እኝህ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ ገለልተኛ ማድረግ የሚባል አስተሳሰብ ያለው ካለ እንደዛ ሊሆን አይችልም፣ ሊሆን የሚችለው የተቃዋሚዎችን ሰዎች ደህንነት ውስጥ ማስገባት ነው ብለዋል። ” በተለይም በተቋም ደረጃ ፤በምህጻረ ቃል ኢንሳ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ደህንነት መስሪያ ቤት፤ የዜግነት እና ኤምግሬሺን ፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው የመከላከያ ደህንነት ፤የአስተዳደር እና ፀጥታ ፤ የፌደራል ፖሊስ ፤ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በእዝ ሰንሰለት በሚፈጠር ልዩነት እርስ በርስ እየተወዛገቡ ሲሆን፣ ተቋሞቹን በትክክል የሚመሩትን አካላት ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱና እርስ በርስ በሚፈጥሩት እሰጥ አገባ አንዱ አንዱ የሚሰራውን የማጠፋፋት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ በግምገማው ላይ ተነስቷል፡፡

የመንግስት ሚስጥሮች ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈው እየተሰጡ በመሆኑ ሚስጢሮችን መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ አንዳንድ ባለስልጣኖች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ለተነሱት አስተያየቶች መልስ የሰጡት ባለስልጣኑ፣ ኢንሳ የተቋቋመውም ይህን ለመስራት መሆኑን ገልጸው፣ “አገሮች ሙሉ በሙሉ ከሳይበር ስለላ ነጻ ባለመሆናቸው አቶ ሃይለማርያምም ነጻ ናቸው ብየ አላስብም” ብለዋል። “አሜሪካኖች የምንናገረውን ሁሉ ከፈለጉ ይሰሙታል” የሚሉት እኝሁ ባለስልጣን፣ “እኛም የአቅማችንን ያክል አሜሪካኖች የሚናገሩትን ለማዳመጥ እንሞክራለን” ብለዋል። የሳይበር ስለላ ለማካሄድ ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም፣ ያን ያክል የምንኩራራበት ግን አይደለም በማለት ኢነሳ ያለበትን ደረጃ አመላክተዋል ከኦሮሚያና ከደቡብ የመጡ የደህንነት ሹሞች ደግሞ “በመከላከያ የደህንነት ተቋሞች ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት ጎልቶ ይታያል” በሚል ቅሬታ ያነሱ ሲሆን ፣ ባለስልጣኑም “የሰራዊት ማመጣጠን ስራ በረጅም ጊዜ የሚሰራ ስራ ነው ” በማለት ለመመለስ ሞክረዋል።

” ትግሉን መርተው እዚህ ድረስ የመጡ ሰዎችና በመከላከያ ውስጥ ያለውን የመኮንኖች ቦታ የያዙት ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው የሚሉት ባለስልጣኑ፣ ያም ሆኖ ከትግራይ የመጡ በርካታ ጄኔራሎች ጡረታ እንዲወጡ ቢደረግም ሂደቱ ግን ረጅም ጊዜ የሚወሰድ ነው ሲሉ አክለዋል።

“የብሄር ተዋጽኦ ብቻ የአንድን ሰራዊት ጠንካራና ደካማ ጎን መገለጫ ተደርጎ መወሰድ ካለበት አደጋ አለው ” ያሉት ባለስልጣኑ፣ የአንድ ብሄር የበላይነት አለ ተብሎ በአጭር ጊዜ ለማመጣጠን ብቻ በአንድ አዳር ሁሉንም ነገር መቀየር እንደማይቻል መንግስት ያምናል ሲሉ ተናግረዋል አቶ መለስ ዜናዊ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል ይባላልና በምን እንደሞቱ በትክክል ይነገረን በሚል ባለስልጣናት ላነሱት ጥያቄም የደህንነት ባለስልጣኑ፣ “አቶ መለስ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል የሚል ትክክለኛ ማስረጃ የለም በማለት መመለስ የጀመሩት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው የሞቱት በስራ ብዛት ተዳክመው እና ህክምናውን መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ሲሉ ደምድመዋል።

በተያያዘ ዜናም የሃገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ከኢሳት ጋር በመሆን እየሰራችሁ ነው፣ ለኢሳትም መረጃ ታቀብላላችሁ ተብለው የተጠረጠሩ 5 የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል። ወጣት መብራቴ ታምራት ፤ወጣት ጀማል አወል ፤ወጣት ደጀኔ አድማስ ፤ ወጣት ሃይሉ ጨርቆስ ፤መቶ አለቃ አሰፋ አብርሃ ሰሞኑን በደህንነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሳት የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዜናም በሃገሪቱ በ28ቱ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የህወሃት አባላት ተማሪዎች እና የደህንነቶች ሃለፊዎች ግምገማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

በግምገማው ወቅት የኦህዴድ እና የብአዴን መሪዎች የተማሪዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል ባሰዩት ውጤት የተገመገሙ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት የአክሱም ፤ ደብረ ታቦር እና ደብረ ብርሃን የኒቨርስቲዎች ከፍተኛ የአመጽ እንቅስቃሴ የታየባቸው በመሆኑ ልዩ የደህንነት ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተወስቷል።